ዓለም አቀፍ የመረጃ ተደራሽነት ቀን በኢትዮጵያ ተከበረ

Views: 61

የመረጃ ተደራሽነት በኮረና ወረርሽኝ ወቅት በሚል በኢትዮጰያ ዓለም አቀፍ የመረጃ ተደራሽነት ቀን ተከበረ፡፡ የኢትዮጵያ የሚዲያ ሰፖርት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህል፣ የትምህርትና የሳይንስ ድርጅት (ዩኒስኮ) ጋር በመተባበር ነው በኢትዮጵያ የተከበረው፡፡

ዪኒስኮ በኢትዮጵያ የመረጃ ተደራሽነትን ለማጠናከር ከኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋር እየሰራ መሆኑን በቨርችዋል በተከናወነው ዊብናሪ ላይ አስታውቋል፡፡

ዊብናሪው በኢትዮጵያ ሲከበር ለሦስትኛ ጊዜ ሲሆን በዓለም ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ ነው የተከበረው፡፡ በዊብናሪው ላይ አምስት ኢትዮጵያዊ የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ የመረጃ ነፃነት ለመንግስታቱ ድርጅት አንዱ የትኩረት አጀንዳ መሆኑን  በኢትዮጵያ የዩኒስኮ ቅርንጫፍ አስታውቋል፡፡ መረጃ በኮረና ወረርሽኝ ወቅት የመረጃ መዛባት ከቫይረሱ ባልተናነሰ ጉዳት አንደሚያደርስ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ በበኩሉ የመረጃ ነፃነትን ለማጠናከር በትኩረት አንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ በዚሁ ዌብናር ላይ ከፍተኛ የሚዲያ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ባደረጉት ውይይትም ላይ ወቅቱ መረጃን ወደ ሚዲያ ተቋማት እና ከሚዲያ ተቋማትም ወደ ሕዝብ የሚደርሰውን ፍሰት በተመለከተ ከፍተኛ ተግዳሮት ፈጥሮ እንደነበር እና አሁንም በሚገባው መጠን እንዳልተቀረፈ ተነስቷል። በውይይቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) የተሳተፉ ሲሆን የተነሳው ጉዳይ በእርግጥም ባለስልጣኑ የሚረዳው ጉዳይ እንደሆነ እና ይህንንም ለመፍታት ጥረቶችን እንደሚያደርግም ዳይሬክተሩ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com