በዕዳ ምክንያት ተይዘው የነበሩ 200 የባቡር ፉርጎዎች ወደ አገር ውስጥ ገቡ

Views: 78

ከዚህ በፊት ተገዝተው ነገር ግን በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት በዕዳ ተይዘው በጅቡቲ ወደብ ላይ የነበሩ 200 የባቡር ተጎታች ፉርጎዎች እየገቡ መሆናቸው የኢቲዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ገለፀ፡፡

ተገዝተው ከነበሩት 550 ተጎታች ፉርጎዎች መካከል 350ዎች ገብተው የነበረ ቢሆንም በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የቀሩት 200 የሚጠጉት ፉርጎዎች አሁን በመግባት ላይ ናቸው ሲሉ ኢንጅነር ጥላሁን ሳካ የኢቲዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ዳይሬክተር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

አጠቃላይ ከዚህ ቀደም የግዢ ውል ተፈፅሞ የነበረው 550 የባቡር ተጎታች ፉርጎዎች ሲሆኑ 350 የሚሆኑት ከገቡ በኋላ ቀጣዮቹ ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየታቸው የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ አሁን ባለው ሁኔታ የውጭ ምንዛሪውን መንግስት ፈቅዶ ሲደግፍ ማምጣት ችለናል ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳነሱት ከሆነ የአንዱ የባቡር ተጎታች ፉርጎ ዋጋ 100 ሺህ ዶላር ሲሆን አጠቃላይ ደግሞ 55 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዳስወጡም ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምከንያት ቅድሚያ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ከነበሩት 350 የባቡር ተጎታች ፉርጎዎች የተቀሩት 200 የሚሆኑት መግባት መጀመራቸውን አንስተው ነገር ግን አሁንም 156 ቱ ገብተው አሁንም 44 እንደሚቀር አንስተዋል፡፡

ወደ አገር ሳይገቡ የተቀሩትን 44 የሚሆኑትን ተጎታች ፉርጎዎች ደግሞ በዛ ቢባል ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ገብተው እንደሚያልቁ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአንድ ጊዜ ብዙ ጭነት እንደሚያነሳ እና በቀላሉ ዕቃዎችን ለማመላለስ ይጠቅማል የሚሉት ኢንጅነር ጥላሁን ጠፍጣፋ ፉርጎው በአንድ ላይ ተቀጣጥሎ መጎተት ያስችላል ይላሉ፡፡ ይህም ማለት አንዷ ፉርጎ ኹለት ባለ ሃያ ጫማ ኮንቴነር በረሷ ትጭናለች ማለት ነው ያሉ ሲሆን ፤ ይህ ማለት ደግሞ 55 በአንድ ላይ ሲሆን ደግሞ 106 ኮንቲነር ያነሳል ማለት ነው፡፡ አንጅነር ጥላሁን እንዳነሱት ከሆነ 550 ደግሞ አንድ ላይ ስራው ሲቀናጅ 11 ባቡር 53 የሚጎትት ባቡር መስራት ( ማደራጀት) ይቻላል ሲሉ አንስተዋል፡፡

ከዛም 11 ባቡሮቹን በየአቅጣጫው ቢላክ አንዱ 6 ኮንቲነር ቢያነሳ 11 ደግሞ 66 ኮንቲነር ማንሳት ይችላ ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንየት እቃ ጅቡቲ ወደብ ላይ ከስምንት ቀን ካለፈ መቁጠር እንደሚጀምር አንስተው እነዚህ ፉርጎዎች በመኖራቸው ደግሞ በስምንት ቀን ውስጥ ካልተነሳ የሚመጣውን ቅጣት ለማስቀረትም ይረዳል ብለዋል፡፡ ከዛም ባለፈ በባቡር አገልግሎት ብዙ ደምበኞች ቢጠቀሙ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ እንደሚያገኙ የገለፁት ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ ይህን ስራ ከሚሰሩ የጭነት መኪኖች የባቡሩ ዋጋ 30 በመቶ ዝቅ እንደሚል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

በባቡሩ ሰጠቀሙም ደምበኞች የሚያስገቡት ንብረት ላይ ጉዳት እይደርስም ( አይቀሸብም) ሲሉ ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ የኢቲዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን መሃበር ዋና ዳይሬክተር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ይበሉ እንጂ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ ድረስ ሚዘልቀው የባቡር ትራንስፖርት አዲስ ማለዳ ለመታዘብ እንደቻለችው በተለይም የሰው ማመላለሻ ባቡር ከግማሽ በታች በሆነ አቅም እንደሚጭን ታውቋል። በተለይም ደግሞ ከኢትዮ ጅቡቲ ነጋዳ ባቡር ጣቢያ ድረስ የሚዘልቁት መንገደኞች ቁጥራቸው ትንሽ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ የሚፈለገውን ያህል ገቢ ለማስገባትም ሳይችል መቅረቱን አዲስ ማለዳ ለመታዘብ ችላለች።

በዕቃ ጫኝ ባቡሮች ረገድም የባቡር ሀዲዱ በጅቡቲ ወደብ ድረስ ስለማይደርስ ወደ ላኪዎች ምርጫቸው እንደማያደርጉትም ለማወቅ ተችሏል።

 

 

 

This site is protected by wp-copyrightpro.com