የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ  

Views: 32

የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮኔስ ሃግ ጋር በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ በበየነመረብ መክረዋል።

የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና በስደተኝነት የሚኖሩ ህፃናት ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የተማሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የመላክ ልምድ አላቸው ብለን እናምናለን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ የጎልማሶች ትምህርት በአዲስ ስልት ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩንም ነው ያብራሩት።

መደበኛ ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በሚገባ እንዲረዱት 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ላይ ልዩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት እንደሚሰጥ ገለፀው የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።

የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮኔስ ሃግም መንግስታቸው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ትምህርት መስክ የምትሰራቸው ስራዎችን ይደግፋል ብለዋል።

የእንግሊዝ መንግስት የትምህርት ዘርፉን ከሚደግፉ አገራት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን ለዚህ ድጋፉ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com