‹የጸጥታ ኃይሉ ለመተከል ዞን ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የተቀናጀ ስራ እያካሔደ ነው››

Views: 43

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጸጥታ ችግርን ለመፍታት የጸጥታ ሃይሎችን ኦፕሬሽን ጨምሮ በሀገር ሽማግሌዎች የተዋቀረ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡ ሰሞኑን በዞኑ ዳንጉር ወረዳ በንጹሃን ላይ ጥቃት በፈጸሙ 14 ጸረ-ሠላም ሃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱም ተገልጿል።

የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ  ጋሹ ዱጋዝ  እንደገለፁት የጥፋት ሃይሎች በዞኑ ዳንጉር ወረዳ መስከረም 26 / 2013  ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዙ የነበሩ የህዝብ ማመላሻ ሌሎች ሁለት ተሸከርካሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

በጥቃቱም አንድ ቻይናዊን የ14 ንጹሃን ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ስምንት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በፓዌ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። “የተደራጀው የጸጥታ አስከባሪ ሃይል በወሰደው የማጥቃት እርምጃ 14 የጥፋት ሃይሎች ሲደመሰሱ 2 ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል” ብለዋል፡፡

አምስት ክላሽንኮቭ እና 10 ኋላቀር የጦር መሣሪዎችም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አስረድተዋል፡፡ ከዚሁ ጥቃት ቀደም ብሎ ሌሎች ጉዳት ሊያስከትሉ የነበሩ ስድስት የጥፋት ሃይሎች በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከመካከላቸው አንዱ ሱዳናዊ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com