የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት 560 አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት ሊገቡ ነው

Views: 79

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት 560 አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት እንዲገቡ መሰኑን አስታወቀ፡፡

ካቢኔው 28/2013  ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል የሚታየውን የነዋሪዎች አቤቱታ እና እንግልት ለመፍታት በቀረበ አማራጭ ሃሳቦች ዙሪያ በተወያየበት ወቅት ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡

በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት መካከል የሚታየውን ክፍተት ለሟሟላት የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ ተጨማሪ አውቶብሶችን በኪራይ ወደ ስምሪት በማስገባት የነዋሪውን ቅሬታ መፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ውሳኔ ማሳለፉን ነው የገለጸው።

አስተዳደሩ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ጀምሮ ተጨማሪ 500 የአውቶብስ ግዢ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም 125 አውቶብሶች እድሳት ተደርጎላቸው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉንም ታውቋል፡፡

የትራንስፖርት ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት ውሳኔውን በአፋጣኝ እንዲፈጸም እና የአውቶብሶቹ የኪራይ ውል እና ተያያዥ የአፈፃፀም መመሪያዎች በአንድ ሣምንት ጊዜ እንዲጠናቀቅም ካቢኔው አቅጣጫ ማስቀመጡንም ተቁሟል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com