ልዩ የፀረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ሀይል ሊቋቋም ነው

Views: 419

የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች  ሚንስትቴር ልዩ የፀረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ሀይል ሊቋቋም  መሆኑን አስታወቀ።

የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን በሚመለከት መግለጫ የሰጡት የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች  ሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ የሴቶችና ህፃናት ጥቃትን ብቻ የሚከታተልና የሚቆጣጠር ልዩ የፀረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ሀይል ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ጥቃት አድራሾች ድርጊቱን ከመፈፀማቸው በፊት ቆም ብለው እንዲያስቡ ለማድረግ ከህግ ቅጣት በተጨማሪ ብሔራዊ የፆታ ጥቃት አድራሾች ምዝገባ እንዲኖር እንደሚደረግም ሚንስትሯ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ጥቃት አድራሾች ከአንዳንድ ማህበራዊ አገልግሎት የሚገደቡበት ሁኔታ በመፍጠር ድርጊቱ ነውርና ፀያፍ መሆኑን እንዲሁም ሀገራችን የማትደራደርበት ጉዳይ መሆኑን ለህዝብና ለዓለም የማስገንዘብ ስራ ይሰራል።

ጥቃት የደረሰባቸው በቋሚነት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያገኙ ይሰራልም ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል።

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com