አራት የብዙሀን መገናኛ ድርጅቶች 23 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባቸው

Views: 2090

በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን አራት መገናኛ ብዙሀን ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ተነገረ፡፡

በብሮድካስት ባለስልጣን የህግና ማስታወቂያ ተወካይ ዳይሬክተር  ዮናስ ፋንታዬ  በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን አራት መገናኛ ብዙሀን ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ቅጣቱ የተላለፈባቸው ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ማስታወቂያ በመልቀቃቸው  እንደሆነ ተጠቁሟል።

በዚህም ኃላፊነታቸውን ተወጥተው ባለመገኘታቸው በሚል በማስታወቂያ አዋጁ መሰረት ከ10 እስከ 23 ሚሊዮን ብር እንዲቀጡ ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይም ማስታወቂያውን በግድየለሽነት በመስራት ለመገናኛ ብዙሀኑ ሰጥተዋል የተባሉት የማስታወቂያ ድርጅቶችም ላይ ቅጣት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ዳይሬክተሩ ቅጣቱ የተላለፈባቸውን መገናኛ ብዙሃን ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com