ብርጋዴር ጀነራሉ ከስልጣን ተነሱ!

0
702

ከጥቅምት 2011 ጀምሮ ያለፉትን አምስት ወራት ገደማ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአስተዳርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ብርጋዴር ጄነራል ከማል ገልቹ ሰኞ መጋቢት 23 በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ ፊርማ ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቀድሞም ቢሆን ይህ እንደሚፈጠር እጠረጥር ነበር ያሉት ጄነራሉ በመንግሥትና በፓርቲ ሥራ መካከል መደበላለቅ በመኖሩ አልተስማማንም ነበር ብለዋል፡፡ በዚህም የክልሉ ገዥ ፓርቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ሰዎች በዕለት ከዕለት ስራቸው ጣልቃ ይገቡባቸው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ ጄነራሉ ደግሞ የሚመሩት የኦሮሞ አንድነትና ነፃነት ግንባር (ሰላማዊ ትግልን ከመረጠ ወዲህ ስሙን የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ በሚል ቀይሯል) የተሰኘ የፖለቲካ ድርጅት አላቸው፡፡

ኢትዮጵያ ለሰላማዊ ትግል ጥሪ ማቅረቧን ተከትሎ ከ13 ዓመት የኤርትራ ስደት ወደ አገራቸው የገቡት ብርጋዴር ጄነራል ከማል ከመንግሥት ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተከትሎ ነበር የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት፡፡ የእሳቸው ሹመት ግን በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች በኩል ጠንካራ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀድሞ ከግንባሩ ጋር የነበሩት ጄነራሉ ኤርትራ እያሉ ባለመስማማታቸው እስከመታሰር ደርሰው የነበረ በመሆኑ ‹‹አሁን ሥልጣን ሲሰጣቸው ቢበቀሉንስ›› ከሚል ስጋት እንደሆነም ብዙዎች ሲተነትኑ ነበር፡፡

መጀመሪያውኑ ኦዴፓ የፖለቲካ ቅቡልነትን ለማግኘት በሚል እሳቸውን እንደሾማቸው የሚገምቱት ጄነራሉ በቀጣይ የፓርቲያቸውን እንቅስቃሴ ለማጎልበት ጊዜያቸውን እንደሚያጠፉም ጠቁመዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ሰሞኑን የማኅበራዊ ትስስር ገፆች መነጋገሪያ ሆነው ከሰነበቱት መካከል ሆኗል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here