የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ጥቅምት ዘጠኝ እንዳይከፈቱ ሚኒስቴሩ አሳሰበ

Views: 143

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ጥቅምት ዘጠኝ እንዳይከፈቱ ሚኒስቴሩ አሳሰበ
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9 ቀን 2013 ትምህርት እንዳይጀምሩ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የተረከቡትን ጭምብል ለክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች አስረክበዋል።
በወረዳና ከዚያ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9 ቀን 2013 ትምህርት እንዲጀምሩ ይደረጋል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በቦታዎች ርቀትና በተለያዩ ምክንያቶች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዳይጀምሩ አሳስበዋል።
ሌሎች ዝግጅቶች እንደተጠበቁ ሆነው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንደደረሳቸው ግን ትምህርት መጀመር ይችላሉ ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com