ከዲክኒል እስከ ዳጉሩ የሚገኘውን 80 ኪሎ ሜትር መንገድ ለማሻሻል ስምምነት ተደረገ

Views: 150

በኢትዮጵያና ጅቡቲ የፋላፊ መንገድ አካል የሆነውንና ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ ጅቡቲ ወደብ ከሚገኘው 220 ኪሎሜትር መንገድ ውስጥ ከዲክኒል እስከ ዳጉር የሚገኘውን አስቸጋሪ መንገድ ለማሻሻል ስምምነት ተደረገ። መንገዱ የተጎዳና ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ እንደነበርም ተጠቅሷል።

በዚህም ምክንያት ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የሚደረገው ጉዞ አስቸጋሪ፣ የተራዘመ፣ ጊዜ የሚወስድና ተሸከርካሪዎችን በተደጋጋሚ ለጉዳት የሚዳርግ እንዲሁም ለአደጋ የሚያጋልጥ ጭምር ነው። ችግሩን ለመፍታትም ኹለቱን አገራት በመወከል የጅቡቲ የወደብ ኮሪደር መንገዶች ዋና ዳይሬክተር አብዲ ኢብራሂም ፋራህ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አያሌው (ኢ/ር) ተፈራርመዋል።

በፊርማ ሰነስርአቱ ላይ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ እና የጅቡቲ ፖርትስ ፍሪዞን ባላሥልጣን አቡበከር ዑመር ሀጂ ተገኝተው ኹለቱን ወገኖች አፈራርመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የኹለቱ አገራት አምባሳደሮች የተገኙ ሲሆን፣ ከዲክኒል እስከ ዳጉሩ የሚገኘው 80 ኪሎ ሜትር ተለዋጭ መንገድ ጥገና እና መልሶ ግንባታ ወዲያውኑ የሚጀመር ሆኖ የዋናው መንገድ ግንባታ በቀጣይ ኹለት ወራት ውስጥ እንደሚጀመር በስምምነቱ ወቅት መግለጹን አዲስ ማለዳ ከመንገዶች ባለሥልጣን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com