የቱሪዝም ዘርፉን ለማስጀመር አዲስ የፕሮቶኮል መመሪያ ይፋ ሆነ

Views: 141

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግም ለማስጀመር አዲስ የፕሮቶኮል መመሪያ ይፋ ሆኗል።
የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጥቅምት 05/2013 በኢትዮጵያ ለሚገኙ አገር ዐቀፍ አስጎብኚዎች የፕሮቶኮል መመሪያውን ይፋ አድርጓል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያደረሰውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ታሳቢ በማድረግ እና በቱሪዝሙ የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲኖር በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡ ጥንቃቄዎችን በመተግበር ወደ ሥራ እንደሚገባም ተገልጿል። በዚህም በተለይ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ አሽከርካሪዎች፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አና የመስህብ ስፍራዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ወደ ሥራ መግባት እንዳለባቸው በመመሪያው ተቀምጧል ሲል የዘገበው ፋና ነው።
አገልግሎት ሰጭዎቹ አስፈላጊውን ቁሳቁስ የማሟላት አቅም ባይኖራቸውም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመሥራት ታቅዷል ሲሉ፣ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የዓለም ዐቀፍ ቱሪዝም ፋሲሊቴሽን ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ደርበው ገልጸዋል። የፕሮቶኮል መመሪያውም ከአስጎብኚዎች በተጨማሪ ጎብኚዎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያዛል ተብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com