የኦሮሚያ ቤቶች እና ከተማ ልማት ግማሽ ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ

Views: 406

የኦሮሚያ ክልል ለቤቶች ልማት በሚል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው ብድር ለበርካታ ዓመታት መመለስ ሳይችል በመቅረቱ የዕዳው መጠን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ታወቀ።

ከ13 ዓመታት በፊት የክልሉ ቤቶች እና ከተማ ልማት ቢሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚል በተበደረው እና በክልሉ 17 ከተሞች ላይ 23 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት ከባንኩ ኹለት ቢሊዮን 136 ሚሊየን ብር ብድር ተበድረው፣ 21 ሺሕ ቤቶች ተሰርተው ከተጠናቀቁ በኋላ ንግድ ባንክ ብድሩን በማቋረጡ ምክንያት ኹለት ሺሕ 876 ቤቶች ሳይጠናቀቁ ቀርተዋል ሲሉ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የኦሮሚያ ክልል ቤቶች እና ከተማ ልማት ቢሮ ዳይሬክተር ባይሳ ሂርኮ አስታውቀዋል።

አክለዉም በጅምር ለቀሩት ቤቶች ባንኩ ሸጦ መጠቀም ወይንም ወደራሱ ማዞር ሲገባው ክልሉ ያለ አግባብ ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ በ ክልሉ ችግር ሳይሆን በ ባንኩ ምክንያት የ 12 አመት ወደ አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን እዳ አለበት መባሉን በ 2012 ከ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ሲሉ ባይሳ ተናግረዋል። ክልሉም ተሰርተው ካለቁት የ ጋራ መኖሪያ ቤቶች ኹለት ቢሊየን ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ሚሊየን ከፍሏል ይህም ከ ተበደረው 3 መቶ ሚሊየን ብር በላይ ነው ሲሉ ለ አዲስ ማለዳ ገልፀዋል።

በፌደራል መንግስት የ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባባሪነት የ ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ለ ክልል ከተሞች የ ቤት ልማት የሚያበድረው ብድር ኦሮሚያ ክልል ሰባት የሚሆኑ ከተሞች ላይ ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ከ 10 አመት በላይ ያስቆጠሩ የ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዳሉ ተናግረዋል።

እነዚህም ቤቶች ግንባታቸዉ በ 2000 በጀት ዓመት የተጀመሩ ሲሆኑ እስከ አሁን ግን ምንም መፍትሄ እንዳልተገኘላቸዉና የግንባታ መጠናቸው በ አማካኝ ወደ 44 በመቶ ብቻ የሚሆን ተሰርተው ባንክ ብድሩን በማቋረጡ ምክንያት ሳያልቁ እንደቀሩ ጠቁመዋለወ።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ክልሉ ለቤት ልማት ብሎ የያየዘው በጀት ስላልነበር ቤቶቹ ባሉበት የግንባታ ደረጃ በ መቆማቸው ስለ ጉዳዩ የ ፌደራል መንግስትን የ ከተማ ልማት ሚኒስትሩም ባንክም ጋር ብንሞክርም ምንም ለውጥ አላገኘንም ብለዋል።

የ ኦሮሚያ ክልል ከ 2010 እና 2011 ከ ዋናው አመታዊ ባጀት ላይ ቀንሶ በ 7 ከተሞች ላይ በ ድምሩ ለ 1382 ቤቶች መስሪያ ኹለት መቶ ሚሊየን ብር መድቦ ቤቶቹ እንዲሰሩ ማድረጉንና በዚህም ከ 7ቱ ከተሞች መካከል ሻሸመኔ በ አስተዳደር ድክመት ምክንያት ሳይሰሩ ቀርተዋል ብለዋል።

አንድ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የሚኖሩ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ በ ቀበሌ 10 በ ጅምር የቀሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ረጅም አመት በ ማስቆጠራቸው ምክንያት እየተሰባበሩ እና እየፈራረሱ ከ ጥቅም ውጪ እየሆኑ እንዳሉ ተናግረዋል ።

በ ጉዳዩ ላይ አዲስ ማለዳ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመደወል ከባንኩ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ያብስራ ከበደ ጋር ስለመረጃው እና ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግችው ሙከራ በተራዘመ ቢሮክራሲ መንገድ ሳይሳካ ቀርቷል። በቀጣይ ከባንኩ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እና ምላሾችን ይዘን እንደምናቀርብም ከወዲሁ እናስታውቃለን።

ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com