የእለት ዜና

ህወሓትን ጨምሮ ህገ ወጥ መሳሪያ ታጥቀው የዜጎችን ህይወት በማጥፋት ላይ ያሉ ቡድኖች በሽብርተኝነት ሊበየኑ ይገባል ተባለ

Views: 409

ምክር ቤቱ ዛሬ በመደበኛነት ከያዛቸው አጀንዳዎች አስቀድሞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ጭፍጨፋ ላይ ውይይት አድርጓል።

ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገው ጭፍጨፋ ላይ የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ እና የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ መደበኛ ውይይቱን ሊያደርግ ቢያስብም አባላቱ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው የዜጎች ህይወት በመሆኑ ውይይቱ ከዚህ እንዲጀምር በሚል በጉዳዩ ላይ በስፋት ተወያይቷል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎ ምክር ቤቱ አጀንዳውን ቀድሞ ቀርፆ የተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በሚመለከት ትናንት ማምሻውን የምክር ቤቱ አመራር ምክክር አድርጎበት አስፈፃሚው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበት ውሳኔ ላይ መደረሱን አንስተዋል፡፡

ይህንን ተከትሎሞ በጉዳዩ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ሀሳብ እንዲሰጡበት ተደርጓል።

በዚሁ መሰረት ህወሓትን ጨምሮ ጥቃት የሚፈፅሙ ህገ ወጥ ቡድኖችን በሽብርተኝነት በመበየን የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚል ሀሳብ ቀርቧል።

ምክር ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ በስፋት ከተወያየ በኋላ አስፈፃሚው አካል ምክር ቤት ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ፣ ምህረት የሌለው እርምጃ እንዲወሰድ እና ችግሩ እንዳይደገም ምን መወሰን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ እንዲቀርብ አቅጣጫ አሳልፏል ሲል የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com