የእለት ዜና

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ጥቃት የብልጽግና ፓርቲን ተጠያቂ አደረገ

Views: 622

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በተለያዩ ጊዜያት እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ሞት፣መፈናቀል፣ስደትና ንብረት ውድመት የብልጽግና ፓርቲን ተጠያቅ አደረገ።

ጉባኤው ዛሬ ጥቅምት 24/2013 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተፈጸሙት ጥቃቶችም በአካባቢው የመንግሥት አስተዳደር ዝምታ፣ይሁንታ፣ኃላፊነት የገደለው ቸልተኝነት አልፎ አልፎ ተባባሪነት መሆኑንም አንስቷል።

‹‹ ያቀናብረው እና የፈጸመው ማን ምንም ይሁን ማን ፤ በአማራ ላይ ለተፈጸሙት ማንነትን መሰረት ላደረጉ አረመኔዊ ጥቃቶች የተፈጸሙባቸው የክልል መንግሥታት ፣የፌደራል መንግሥት እንዲሁም ገዢው የብልጸግና ፓርቲ ተጠያቂዎች  ናቸው›› ብሏል በመግለጫው

አክሎም ‹‹በይፋ ኃላፊነት መወሰድ እና  ይቅርታ መጠየቅ  አለባቸው›› በማለት ፤‹‹ የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በአገራችን በተለያዩ ክልሎች በአማራው ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላውም በተደጋጋሚ ተፈጽሟል። ለዚህም ምክንያቱ ሕገ መንግሥቱ የፈጠረው አግላይ መንግሥታዊ ሥርዓት መሆኑ ቢታወቅም ሕገ መንግስቱ መሠረታዊ ማሻሻያ እስከሚደረግበት ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት መከላከል የሚችል እና በሚኖሩበት አካባቢ የአናሳ (Minority ) ሕዝብ የፖለቲካ እና አስተዳደር ውክልና እንዲኖራቸው የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ እንዲወጣ እና ይህንኑም የሚያስፈጽም ተቋም እንዲቋቋም እንጠይቃለን ።›› ብሏል።

በተጨማሪም ‹‹ ለፌደራል መንግሥት፣ለክልል መንግሥታት እና ለብልጽግና ፓርቲ በዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ማንም ያቀናብረው ማን ይፈጽመው የመከላከል የቅድሚያ ኃላፊነቱን የእናንተው ነው።›› በማለት በመግለጫው ላይ አስፍሯል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com