የእለት ዜና

በእንባ እና በምሬት የደመቀው የምክር ቤት ውሎ

Views: 703

የጥቅምት 24/2013 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ፣ በምክር ቤቱ አባላት ዘንድ በተለየ ድባብ የተከናወነ ነበር። ለምክር ቤቱ የሚቀርበውን መግለጫ በማንበብ የጀመሩት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በምእራብ ወለጋ ዞን ቃንቃ ቀበሌ ውስጥ በጸረ ሰላም ኀይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከሰብዓዊ ፍጡር የማይጠበቅ አሰቃቂ ተግባር ነው ሲሉ አውግዘዋል።

እነዚህን ሕዝብ ያነወራቸው እና ዘመን የሻራቸው ዕኩይ ኃይሎች እንዲሁም በፖለቲካ ስልጣን ሱስ የተጠመዱ በመሆናቸው ከነሰንኮፋቸውን ተነቀቅለው እንዲወገዱ መንግሥትን ጠይቆ ምክር ቤቱም መንግሥት ከሚወስወዳቸው እርምጃዎ ጎን አብሮ እንደሚቆም ገልጸዋል።

መግለጫውን ተከትሎ አስተያታቸውን የሰጡት የምክር ቤት አባላትም መግለጫ ብቻ በቂ አለመሆኑን እንስተው አቋም መያዝ እንደሚገባ አንስተዋል።
ለእለቱ በተያዙ የመወያያ አጀንዳዎች ዙሪያ ለመምከር ሲያመሩ ከምክር ቤቱ አባላት መረር ያለ ተቃውሞ አስተናግደው በንጹሃን ዜጎች ሞት አስፈጻሚው የመንግሥት አካል እያሳየ ባለው ቸልተኝነት ለመንቀፍ ከሦስት ቀናት በፊት የተቀረጹትን የመወያያ አጀንዳዎችን ወደ ጎን በመተው ክምንም በላይ አንገብጋቢ ጉዳይ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ማንነት እና ብሔርን መሰረት ባደረገ ጥቃት የንጹሀን ዜጎችን መቀጠፍ አስመልክተው ሐሳባቸውን በእንባ፣ በቁጭት እና በንዴት ለኹለት ሰዓታት ተወያይተዋል። የአዲስ ማለዳው ዳዊት አስታጥቄ በእለቱ በምክር ቤት አባላቱ አንደበት የተነገሩ ዋና ዋና ሃሳቦችን እንደሚከተለው እቅርቦታል

“ከለውጡ በኃላ ማንነትን እና ብሔርን መሰረት ባደረገ ጥቃት አገራችን አኬልዳማ እየሆነች ነው”
የተከበሩ ወ/ሮ ብርቱካን ሰብስቤ
ዛሬ የገጠመን ማንነትን እና ብሔርን መሰረት ያደርገ ጥቃት ለረጅም ጌዜ ሲሰራበት የቆየ ትርክት ነው።በየጊዜው መቻቻል እየተባለ ታግሰን አልፈናል ግን ከመቻቻል አልፈን ሕዝብ እያለቀ ነው። መቻቻል ሲበዛ እንደ ሶሪያ እና ሩዋንዳ የማንሆንበት ሁኔታ አይታየኝም።
እኔ ተስፋ እየቆረጥኩ ነው እኔ የመናግር ሞራል አሳጥቶኛል በድርጅት መክረን ብናውቅም ለውጥ እያመጣ ነው።
እኔ የሚገርመኝ በሌሎች አገራት ሠላም በማስከበር የሚታወቀው መከላከያ ሰራዊታችን እውን ምን እየሠራ ነው? አይ ኤስ አይ ኤስን እና አልሻባብን ድባቅ የመታ ሰራዊት እውን ኦነግ ሸኔ አሸንፎት ነው? እውን ህወሓት አሸንፎት ነው?
ሰላም ሚንስቴር በግማሽ ቀን ብሔራዊ መግባባት እያለ ሰብስቦ እየበተነ የትኛው መግባባት ነው የተፈጠረው? ተቃዋሚዎችም እኮ ምርጫ አታካሂዱ መጀመሪያ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንድረስ እያሉ ነው
የእርምጃ አወሳሰዳችን ደካማ ስለሆነ ነው፣የውስጥ ኃይላችንን አጠናክርን መመከት ካልቻልን ነገ እንዴት ነው የውጭ ጠላት መመከት የምንችለው?

መንግሥት በቸልተኝነት እየደ ነው ያለው
መሃሪ ዘለቀ
የኢትዮጵያ ህዝብም ተሸክሟቸው እነደከረም እናውቃለንከመንግሥት በኩል ግን አንድ ስህተት አለ
የሚወሰዱ እርማጃዎች አጥጋቢ አለመሆናቸው የታገቱ ተማሪዎች አድራሻ እኮ ዛሬም አይታወቅም ስልካቸው ግን ይሰራል ያሉበትን ሁኔታ እንኳን ተከታትለው በየጊዜው አያሳውቁንም
ኦነግ ሸኔ በሚሊዮን የሚቆጠር የመንግሥትን ባንክ ዘርፎ ለሽብር ተግባሩ ማዳበሪያ ሲያደርግ ለምን ዝም ተባለበየቀኑ የማይታወቁ ሰዎች የማይታወቁ ሰዎች እየተባለ የሚባለው እነዚህ ሰዎች መናፍስት ናቸው ለምንድነው ተወግዘው በአሸባሪነት የማይፈረጁት?
ከታች ባለው የመዳከም ሁኔታ አመራሮቹ እራሳቸውን እንጂ ሕዝቡን እየጠበቁት አይደለምይህም በአሰራር መስተካከል አለበት እኛ በምንፈጥረው የፖለቲካ ቀውስ መከላከያ በየስርቻው እየገባ አገር መጠበቅ ሲገባው መንደር እየጠበቀ ይገኛል።

“አመራር ሆኜ እዚህ መቀመጤን የጠላሁበት ወቅት ነው”
ሽታዬ ምናለ (ምክትል አፈ ጉባኤ)
አማራን ለማጥፋት ከዛሬ ሰላሳ ዓመት ጀምሮ ሲሰራበት የቆየ ተግባር ነው። በ 1983 ጀምሮ ኦሮሞው አማራው ላይ እንዲነሳ እና እርስ በእርስ እንዲጋጭ በሕገ መንግሥት ጭምር አስቀምጦ አማራን ለማጥፋት እና ለማዳከም ሲሰራ የቆየ ተግባር ነው አናሳ ቁጥር ያላቸውን ሕዝቦች የማይከላከል ሕገ መንግሥት ነው ሕገ መንግስቱን እስከ ማሻሻል ድረስ መድ አለብን ይን ስልጣን ላይ እያሉም ከሥልጣን ወርደውም እየሰሩት ያለው ሥራ ነው ይቺ አገር የምትኖረው በሁላችን ኢትዮጵያውያን ትከሻ ነውአንዱ ጠፍቶ ሌላው ሊኖርባት የምትችል አገር አትኖረንም::

የዛሬ ኹለት ዓመት ስንጀም የነበረን ሞራል አሁን የለንም እኔ በግሌ የዛሬ ኹለት ዓመት ወደ ለውጥ ስንገባ የነበረኝ ተስፋ አሁን የለኝም በየጊዜው እየተዳከምን፣እየሞትን፣ የወገኖቻችንን ሞት እየሰማሁ መቀጠል አልችልም

ከዚህ በፊት እንደነበረው ተሳስተን ነበር ማለት ኹለተኛ አልፈልግም አሁን ነው እያስተካከልን መሄድ ያለብን።
በዓለም የሌለ ሰላም ሚንስትር ብለን አቀቁምን እያለን ምን እየተሰራ ነው? ዛሬ አንድ አናሳ ብሄር ያለቸው ቦታዎች ላይ ነው ጥቃት የሰነዘሩት፣ ሌላ ጊዜ ላይ ደግሞ ሌላ አናሳ ብሔር ያለባቸውን ቦታዎች ማጥቃታቸውን አያቆሙም ሰዎቹ አሁን ሌላ ሥራ የላቸውም ለዚህም ምንም ጠርጥር የለኝም ምክንያቱም ‹ታርጌታቸውነ› አራት ኪሎ መግባት ነውእሱን እንደ ቀልድ ሳያስቡት ጥለውት የሔዱት ስለሆነ ነው።

ሰው መሆኔን የጠላሁነት ወቅት ነው፤አመራር ሁኜ ዛሬ እዚህ መገኘቴን የጠላሁበት ወቅት ነው፤ ምክንያቱም ሕዝብ ወክለን ተቀምጠን ሰላም እና ደህንነት ካላስጠበቅን መንግሥት ምክር ቤት መኖራችን ምንድነው የሚጠቅመው?ልማት እድገት ብልጽግና ወዘተ ከሕዝን ደህንነት በኋላ ነው የሚመጣው፣መሬቱ አይደለም ብልጽግና ሕዝብ ነው።

እንደ ቀልድ የሞቱት ሞተው አሁንም ፍርሃት አለን፣ ስጋት አለን እያሉ ነው፣ እንደ ምክር ቤትም የህዝብን ደህንነት ማረጋግጥ አለብን። ከዚህ በኃላ መርዶ መስማት አልፈልግም።

በጋራ እናልቅስ
አቡዱላሂ ግንቢቴ
ዛሬ አማራ ላይ መጣ እንጂ በብሄር ለይቶ መግደል ቀድሞ የተጀመረው ነው።ኦሮሞ ፣ሶማሊያ እና ሉሎች ብሄሮች ላይ ተፈጽሟል፣ መስኪዶችን እና ቤተክርስቲያኖችን አቃጥለዋል ግድያ እየተፈጸመ ያለው በአንድ ብሄር ላይ ወይም ሐይማኖት ላይ አይደለም በሚለው እንስማማ።

እንደ ምክር ቤት አንድ ሆነን ለሁሉም ነው ማልቀስ ያለብን፣ እኔ የተመረጥኩበት ሁሉም ብሄርብሄርሰቦች መርጠውኛል ብዬ ስለማስብ ለይቼ አላለቅስም ለይተን ማልቀስ ከጀመርን በኃላ አንወጣውም።
ለውጥ ይመጣል ብለን ነው ዝም ያልነው እንጂ፣በአሸባሪነት መፈረጅ ካለበት ግን ግለሰብም ሆነ ድርጅት ይፈረጅ የውሳኔ ሃሳብ ይቅረብ እንወስን።

ሕወሐት በሽብርተኝነት መፈረጅ አለበት
የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ዳባ
በየአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን የንጹሃን ጭፍጨፋ በተመለከተ ማየት ያለብን፤ ቁጭ ብሎ እያቀደ፣ እያስታጠቀ፣ እያሰለጠነ፣ የሚልከውን እና አገርን እያፈረሰ ባለው ኃይል ላይ ማነጣጠር አለብን መንግሥት ይህንን ጉዳይ አጣርቶ አቅርቦ በሽብርተኝነት መፈረጅ አለብን ከዚህ በፊት መንግሥት እነ ኦብነግን እዚህ ምክር ቤት ላይ አቅርቦ ሲያስወሰን ድርጅቶቹ የዚህን ያህል ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፈው አይደለም። ድርጅቱን በአሸባሪነት ለመሰይም የሚቋቋሙ ‹ኤለመንቶች› ተመሳሳይ በመሆናቸው ለመፈረጅ አዳጋች አይደለም መንግሥት በዚህ ላይ ላይ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማዳንም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወሰድ ይገባል
ላይ ላይ የሚሮጠውን ብቻ ሳይሆን ‹በማስተር ማይንድነት› ደረጃ እየመሩ ያሉትንም ግለሰቦች በሽብርተንነት ፈርጆ እርምጃ መውሰድም ይገባል
መከላከያ ሰራዊቱም ሕዝቡ ስጋት እያለው አካባቢውን የለቀቀበት እና ክፍተት የተፈጠረበት ሁኔታ ብሎም ደህንነቱም ምን ይሠራ እንደነበር እዚህ ምክር ቤት ቀርቦ መገምገም አለበት።

በሞተ ሕዝብ ደም ላይ ቆሜ መወያየት አልችልም
መሓንዲስ መላኩ
ጉልበት ያለው መንግሥት ነበር የሚመስለኝ ፣ጉልበት ያለው ሕግ ነበር የሚመስለኝ አሁን ግን ጉልበት ያለው ሕገ ወጡ፣በየትም የሚጨፍረው ሕገ ውጡ ቡድን ሆኗል።
ሰውን ያህል ትልቅ ፍጡር ግማሹን በተሰበሰበበት፣ ግማሹን ተኝቼ እነሳለሁ ባለበት የሚጨፈጭፍ ቡድን መንግሥት በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ውስጥ አውሎ ማስተካከያ ካልሰጠ በየትኛውም አግባብ መግለጫ በቂ አይደለም በቂ ሊሆን የሚችለው የሰዎችን ደም በአግባቡ ማበስ ሲቻል ነው።የሰዎችን እንባ በአግባቡ መጥረግ ሲቻል ነው።
ይህ አንድ ወረዳ ላይ ብቻ የሆነ አይደለም ከኹለት ሳምንት በፊት ጃርደጋ በሚባል አካባቢ 12 ሰዎች በአንድ ጊዜ ሕይወታቸው አልፏል ምንም አልተባለም ከ አንድ ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ልጆቻቸው ጫካ ተበታትነዋል ድረሱልን እያሉ ማንም አልደረሰላቸውም መንግሥት ምን እየሠራ ነው የሚል ጥያቄ አለኝ?
ሕዝብ እኮ እንቅልፍ የሚተኛው መንግሥትን አምኖ ነው።ባያምን ኖሮማ እንደ ሌላው ‹አግሬሲቭ› መሆን ይችል ነበርማን ይከለክለዋል? ሌላው ሕገ ወጥ ሲሆን ዝም ብሎ ቆሞ የሚታረድበት አግባብ ሊኖር አይችልም የራሱ አስተዋጽኦ ማድርግ የሚችልበት እድል ስላለው ማለት ነውይህንን ዕድል ግን ለመንግሥት ሰጥቶ ነው እፎይ ብሎ ተቀምጦ የነበረው ዜጎችን መከላከል ሳይችል ቀርቶ፣ ሕግ ውጥ ቡድን ነው ፣ዘራፊ ቡድን ነው ወዘተ እያለ ሊቀጥል አይችልም የማይሆን ከሆነ በሞተ ሕዝብ ደም ላይ ቆሜ መወያየት አልችልም።
እነዚህን ቡደኖች በአሸባሪነት ዛሬውኑ መፈረጅ አለባቸው ስለዚህ ኢትዮጵያ በትክክለኛው መንገድ በአንድ ዘር ልትገነባ የታሰበ ከሆነ የተሳሳተ ነውኢትዮጵያ የሁሉም ሀገር ነችከዛሬ ጀምሮ ማስተካካያ ልንሰጥ ይገባል ጉልበት ያለው መንግሥት ነበር የሚመስለኝ ፣ጉልበት ያለው ሕግ ነበር የሚመስለኝ አሁን ግን ሕገ ወጡ፣በየትም የሚጨፍረው ቡድን ሆኗል

የአገር ሰላም አደጋ ላይ ነው ያለው
የተከበሩ ሐዋ አሊ አቡበከር

የትላንትና ሳምንት 18 ሰው በተኛበት በድቅድቅ ጨለማ በከባድ መሳሪያ የተገደሉት፣በማግስቱ ሀገር ሰላም ብለው ከትምህርት ሚንስትር ለስራ የተላኩ ሰዎች የሞቱት፣እኔ በምወክለው ሕዝብ 55 ሕጻናት እና ሴቶች የዛሬ ዓመት ተገድለዋልሞት በየወኑ እየተሰማ ያለ ጉዳይ ነው፡፤ይሔ ተግባር ሌላው ቀርቶ መከላከያ ሰራዊት ባለበት ሁሉ ነው እየተፈጸመ ያለው
የአገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በጥቅም የሚደለሉ ጥቂቶች አሉለውጡን የሚያደናቅፉይን በተጨባጭ ስለምናውቅ ነው የምንናገረውአርብቶ አደሩም እጅ ማስረጃ አለ
እንደ እነ አልሻባብ ያሉ የውጭ ኃይሎችም እጃቸው እነዳለበት ጭምብላቸው እና ፓስፖርታቸው ሁሉ አ›ስለመገኘቱ ማስረጃወች አሉስለዚህ የአገር ሰላም አደጋ ላይ ነው ያለውለውጡም ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኃይሎች እየተሳካላቸው መሆኑን አመላካቾች አሉይሳካላቸዋል ማለት ባይሆንምምክር ቤቱም ችግሩን አውጥቶ መነጋገር እና መረዳት አስፈለጊ ነው
አስፈጻሚዎቻችንስ ከዚህ ዓይነት ጥፋት ነጻ መሆናቸው እንዴት እናውቃለን በየ ሶሻል ሚዲያው ችግሩን ማውገዝ ሲገባው እያሽሞነሞነ የሚያቀርበው።

ቅጽ 2 ቁጥር 105 ጥቅምት 28 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com