የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖችን ማዘጋጀቱን አስታወቀ

Views: 33

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖችን ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና ሎጂስቲክ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፍጹም አባዲ ለኢዜአ ገልጸዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነም የኮቪድ-19 ክትባትን ለማከማቸት የሚያስችል መሰረተ ልማት ተሟልቷል ብለዋል።
ዳይሬክተሩ ጨምረው ሲናገሩም ማጓጓዙንና ማሰራጨቱን ስኬታማ ለማድረግም አሰራር መነደፉን ጠቁመዋል።
ክትባቶቹ በባህሪያቸው ቀዝቃዛ ስፍራ የሚፈልጉ በመሆናቸው ይህንን ለማሟላት በቂ የሆነ የመሰረተ ልማት መዘጋጀቱን የጠቆሙት ፍጹም ፤ የተዘጋጁት 21 አውሮፕላኖችም የክትባቱን ደህንነት በአግባቡ የሚጠብቁ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ በማሰራጨት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወቃል።

ቅጽ 2 ቁጥር 106 ኅዳር 5 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com