የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ ሳባት የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ

Views: 64

የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱን ጨምሮ አገርን በመክዳት ወንጀልና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ በማሰብ ወንጀል የተጠረጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገለጸ።

የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ፣ የመከላከያ ሰራዊት ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረመድህን፣ የደቡብ ዕዝ ሰው ኃብት ልማት አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ገብረዮኃንስ ሳርሲኒዮስ፣ የሰሜን ዕዝ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ኢንሱ ኢጳጆ ረሾን ጨምሮ ሰባት አገርን በመክዳት ወንጀልና ህገመንግስትና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ማሰብ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ፣መቅረባቸው ተገልጿል።

የፌደራል ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ መንግስትና ሕዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው መቀመጫውን ትግራይ ክልል ካደረገ የፀረ ሰላም ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በመከላከያ ጦር ውስጥ ሴሎችን በማደራጀት ጥቅምት 24/ 2013 የሀገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ሬዲዮ ግንኙነት ማቋረጣቸውን ገልጿል።
በዚህም ሰራዊቱ እርስ በርስ እንዳይገናኝና እንዳይቀላቀል፤ በጦሩ ላይም የሞት፣ የአካል ጉዳትና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም አድርገዋልም ብሏል።

እንዲሁም በአገር ውስጥና ከውጭ የሚቃጣበትን ጥቃት እንዳይከላከልና የሰሜን ዕዝ ጦር እንዲፈርስ በማድረግ በተቀናጀ መልኩ ኦነግ ሸኔ ከተባለና ከሌሎች የፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር በመተባበር በተለያዩ ክልሎችም ሐይማኖትን ሽፋን አድርገው የብሄር ግጭት በማስነሳትም አገርን ለመበተን ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ ገልጿል።

ፍርድ ቤቱም የወንጀሉን ክብደትና በአገር ደህንነት ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ወንጀል መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀን መፍቀዱ ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 106 ኅዳር 5 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com