የእለት ዜና

የምዕራባውያን ስጋትና ኢትዮጵያ ዳግም የአፍሪካውያን ተስፋ?

Views: 912

ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች የሚለው የትራምፕ ንግግር በበርካቶች ዘንድ የስቆጣ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። በተለይም ኢትዮጵያውያንን ትራምፕ ይህንን ሲሉ ለግብጽ እንደወገኑ የተሰማንም ብዙዎች ነበር። ይሁን እንጂ ፕሬዘዳንቱ የመጨረሻዋን የስልጣን ጊዜያቸውን ተጠቅመው ይህን መልዕክት ለማስተላለፍ የተገደዱበት ምክንያት ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንብታ በጨረሰችበት ጊዜ በቀጠናው ላይ የሚኖራትን የጂኦ ፖለቲክስ ተጽኖ ፈጣሪነት የበለጸጉ ሀገራትን ጥቅም በከፍተኛ ሁኔታ የሚገዳደርጉዳይ በመሆኑ ነው። ኑሮዋቸውን በጀርመን የደረጉት ሽመልስ አርዓያ(ዶ/ር) ይህንን ጉዳይ መረጃ በማጣቀስ ያቀረቡትን ሐሳብ እንዱህ አቅርበነዋል።

አውሮፕያውያን እራስን መልሶ የሚያስተች (የሚጎዳ) ሐሳብ ሲቀርብ “Those who live in glass houses shouldn’t throw stones” የሚል ምክር ይሰጣሉ። ይህን ጽሑፍ እንድፅፍ ምክንያት የሆነኝ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አሁን የእጁ ያገኘው የወቅቱ የዓለም ልዕለ ሃያሏ መሪ “ኢትዮጵያ እኔ ያቀረብኩላትን ስምምነት አልፈርምም ስላለች ግብጽ ግድቡን በሃይልም ቢሆን ማፍረስ አለባት” ማለቱን ተከትሎ በምዕራቡ የአገራችን ክፍል ያልተለመዱ የፀጥታ ስጋቶች ላስተዋለ ፍንትው ብሎ የሚታይ ነገር መታዘቤ ነው። እንደተባለው የግብጽ መንግሥትታ ሃይል መጥቀም ቢሞክር በዘላቂነት የግብጽ ሕዝብ የደህንነት ስጋት እንደተደቀነብት እሙን ነው። በግድቡ ድርድር ውስጥ ቦታ ያላትን አገር ከሚመራ በማንአለብኝነት ይህ ንግግር የተንፀባረቀበት አንድምታ በጥልቀት ለመፈተሽምነው።

እንደሚያውቀው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ እያደረጉት ባለው የህዳሴው ግድባችን ድርድር አሜሪካ በታዛቢነት ትገኛለች። ብዙዎች የአሜሪካ በድርድሩ እንድትገኝ መቀበላችን ስህተት ነበር ይላሉ። አሜሪካ በድርድሩ ሳትሳተፍም ተጽዕኖ እንደምታሳርፍ መዘንጋትም የለበትም። እንዲያውም መድረኩን አግኝቶ መሪዋ የግል ፍላጎት በግብጽ ስም አንፀባረቀች። ከዚህ የበለጠ የሚገርመው ግን ከመነሻው የታዛቢነት ሚና የተስማማች አገር እንዴት የስምምነት ሰነድ ለማርቀቅ በቃች የሚለውን ነው። ከዚህ ተነስተን በአካባቢው በይፋ ፈቅደው እንዲጀመር ያደረጉት ጦርነት መነሾውም እንዲሁ እንቃኛለን። ከዚህ በመነሳት እውን ትራምፕ ምክሩን ያስተላለፈው ለግብጽ ወግኖ ወይስ የአገሩን ጥቅም እያስጠበቀ እንደሆነ እንመለከታለን። በድፍረት ያውም በመደበኛ ሚድያ “አንዳች ብንነካ ከውጭ የሚረዳን አካል አለ” እየተባለ ግብጽ ምን አለፋት? የግብጽና የምዕራባውያን እኩይ ሥራ የሚያከናውነው ቡድን በእቅፋችን ይገኛል። ይህ ቡድን መደምሰስ አለበት።

ጉዳዩ ከግብጽ “ታሪካዊ” የውሃ ጥያቄ ውትወታ አለፍ በማለት የክፍለ-አህጉሩ ውስብስብ የሆነው ጂኦፖለቲካዊ (Geopolitical) ጉዳዮችንም እንዲሁ መፈተሽ ይኖርብናል። ምንም እንኳን ግብጽ ኢትዮጵያን ለማወክ የማትፈነቅለው ድንጋይ ባይኖርም (ይኸው አሁን ፍሬ እያፈራላት ይገኛል) በተደጋጋሚ እንደ ሰማነው ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫ ወጥራ በማስጨነቅ ግብጾች ግድቡን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ጋር አሳሪ የሆነ (Binding agreement) ስምምነት በቶሎ መፈራረም ይፈልጋሉ። ለዚህ ምክንያቱ ግልጽ ነው።

ወደፊት የግድቡ የውሃ መጠን ስለሚጨምር በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ የመደራደር አቅሟን ከፍ ስለሚያደርግላት በሚል ፍራቻ ነው። በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ሰነድ ላይ ማስፈረም ለግብጽ መንግሥትት ትልቅ ድል ነው።

የትራምፕ የግድቡ ማፈርስ እቅድ የሚጠቁመው ቢኖር ለዘመናት በአፍሪካ ላይ የተንሰራፋው የምዕራባውያን መንግሥትታት ሴራ አካል ነው። ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት በዓለም ገበያ ላይ የጥሬ እቃ አቅራቢ ከመሆን ባለፈ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ሚና እንዲጫወቱ ሰለማይፈለግ (የወቅቱ የኢትዮጵያ አያያዝ ይህንን የምዕራባውያን የዘመናት ክፋት በአፍጢሙ የሚደፋ በመሆኑ) ለዚህ እኩይ አላማቸው ግብጽና ተላላኪዎቿ ተባባሪ እንዲሆኑ ነው። ይህንንም በዝርዝር እንመለከተዋለን። የሚገርመው ነገር ግን እንደ ተባለችው ግብጽ ግድቡ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የማንም ምክር አትጠብቅም ነበር፤ እውነታው ግብጽ ይህን በቀጥታ ከሞከረችው እራሷ ጠፊ መሆኗ ነው። እንዴት የሚለውን ቀጥለን እናያለን።

“በመስታወት ቤት ውስጥ…” የምትኖረው ግብጽ
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከኢንተርኔት ላይ ፈለግ በማድረግ የግብጽ ስጋት ማግኘት ይቻላል። በመሆኑም የተለየ ምስጢራዊ መረጃ የለውም ለማለት ነው። ይኸውም የግብጽ የመሬት ቆዳ ስፋቷ ከአንድ ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር ቢልቅም፣ ለመኖር ተስማሚው የሆነው ክፍል ከሦስት በመቶ በታች ነው። በዚህም ዘጠና ዘጠኝ ከመቶው የሆነው ሕዝቧ የአባይ ወንዝን ዳር ተከትሎ ከሰሜን እስከደቡብ ሰፍሮ ይገኛል። ለማነፃፀር ያህል የጋምቤላ ብሔራዊ ክልል በሚያክል ቦታ ላይ (ሰላሳ ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር ያክል መሆኑ ነው) ወደ መቶ ሚሊዮን የሚጠጋው ሕዝቧን አከማችታለች። አባይ ወደ ሜድትራንያን ሲቃረብ ትልቅ የደለል ክምችት (Nile Delta) የፈጠረ ሲሆን እንደአሌክሳንድሪያ ያሉ የግብጽ ትላልቅ ከተማ ማዕከላት በዚህ ስፍራ ሲገኙ ከዚህ ደለል ክምችት በስተደቡብ ዋና ከተማዋ ካይሮ ተዘርግቶ ትገኛለች። ይህ የደለል ክምችት በዓለም በግዝፈቱ የሚስተካከለው የሌለ ሲሆን የአገሪቱ የግብርና ምርት ማዕከልም እዚሁ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም በዚህ ውስን መሬት ሁሉንም መሠረተ ልማቶቿና የሚታረስ መሬቷ ተከማችቶ ይገኛል። የግብፅ እምብርትም እዚሁ እንደሚገኝ ይገለፃል። በመሆኑም አብዛኛው የፖሊሲ ትኩረቷም ለዚህ ቦታ ተብሎ የሚቀየስ ነው።

የአባይ ወንዝ ለማምረት እንጂ ለንግድ አገልግሎት አይውልም። ይኸውም ለመጓጓዣ ሳይሆን ለመስኖ የሚስማማ ወንዝ ነው። የወንዙ ፀባይ የተነሳ በመሠረተ ልማት ግንባታዋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሮባታል። በዚህም የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወነው በየብስ ትራንስፖርት ብቻ ስለሆነ ወጪው የኑሮ ውድነት በማስከተሉ ህብረተሰቧ እንደተማረረባት ይገኛል። በእርግጥ በኢትዮጵያም ቢሆን የትራንስፖርት ወጪ የዋጋ ግሽበት በማባባስ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው በሚወጡ መረጃዎች ተገልጿል። ግብፃውያን የአባይን ወንዝ ተከትለው ስለሚኖሩ በወንዙ በኹለቱም አቅጣጫ የሚገኙትን መንደሮችና ከተማዎች ለማገናኘት ከሰሜን እስከ ደቡብ በኹለቱም በኩል የመሠረተ ልማቶችን መገንባት ይጠበቅበታል። ይህም የመሠረተ ልማት ወጪን በእጥፍ ጨምሮባታል። ባለሙያዎች በዓለም ላይ ይህን የመሰለ የመሰረተ ልማት ችግር (infrastructure dilemma) የተጋረጠበት ሌላ አገር የለም እስከ ማለትም ደርሰዋል። ምክንያቱም እያደገ ከመጣው ሕዝቧ እና ውስን ከሆነው ተስማሚ መሬቷ ትይዩ የሆነ የመሠረተ ልማት ግንባታ ለማካሄድ መገደድ እውነትም እርግማን ነው።

የግብጽ መንግሥትት ሕዝቡ እንዳያምጽበት ከፍተኛ ድጎማ በማቅረብ ያባብላል። እነዚህ ድጎማዎች የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 10 በመቶው ድርሻ እንደሚይዝ ይነገራል። ይህ ከባድ ሸክም ነው። መንግሥትት ይህን ድጎማ የሚያቀርበው የፖለቲካ አለመረጋጋት ይፈጠራል በሚል ፍራቻ ነው። ውጤቱም ዘላቂ ድህነት ማስከተሉ ላይ ነው። በዚህም የግብፅ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ እንደገናናነቷ የገዘፈ አይደለም። ግብጽ ውስጣዊ የፖለቲካ መረጋጋት የራቃት አገር ናት። ግድባችን በተመለከተ ሚድያው የማስጮኻቸው ምስጢር ይህ በመካከላቸው የሌለውን አንድነት ለማምጣት ነው። ዘመናዊቷ ግብፅ የእህል ምርቷን ወደ ጥጥ በመለወጥ የተነሳ ይህ የኤክስፖርት ገቢዋ ቢያሳድግላትም ግብጽ አብዛኛው ምግቧ ከውጭ የምታስገባ ሆናለች።

ሌላው የግብፅ ፖለቲካዊ ውጥንቅጥ የሥልጣን ጠቅላይ ገዢነት (authoritarianism) የሰፈነበት ነው። በግብፅ በታሪኳ አምባገነን በሆኑ መንግሥትታት ስትመራ ቆይታለች። አሁንም ያለው ከዚህ የተለየ አይደለም። ወታደራዊ ኃይሉ እራሱን የሕዝቡ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሾሟል። በግብፅ ውስጥ ሁሉም ነገር የሚሠራው በወታደሩ ተቋማት ሲሆን ግቡም በዋናነት ለአገዛዙ ጥቅም መጠበቅ ነው። የውጭ ንግድ፣ የባንክ ተቋማት እንዲሁም የግብርና ኢንቨስትመንት በወታደራዊ ባለሥልጣናት ቁጥጥር ስር ያለ ነው። በመሆኑም ሀብቱ በሙሉ ወደልሂቃኖቹ ኪስ የሚገባ ነው። ለዚህ ዝርፊያው እየተጧጧፈ ያለው ለሕዝቡ ሁሌም በጠላት ተከበሃል እያሉ በማስፈራራት ነው። የተካረረው የህዳሴው ግድብም ጉዳይ የዚህ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያውያን እንደጀመሩት መጨረሳቸው ለማይቀር ሁሌም አካባቢው ውጥረት የሰፈነበት ያስመስሉታል። በመንግሥትታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ጭምር እንዲታይላቸው ጠይቀዋል። የሚገርመው ነገር ግን በግድቡ ግንባታ የተነሳ “ጉልህ ጉዳት” እንደማይደርስባቸው ማወቅ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነትም ተጠቃሚ እንደሆኑ እያወቁ እንኳን ለጂኦፖለቲካዊ ፉክክር (geopolitics competion) በመሯሯጥ ላይ መገኘታቸው ነው።

ከግድባችን በላይ ግብጽ በሊብያ ምድረ በዳ እና በሜዲትራኒያን ባህር በኩል በቱርክ እንደዚሁም በሲናይ በረሃ በራሷ ታጣቂዎች ተሰንጋ የተያዘች ስትሆን በተደቀነባት የደህንነት ስጋት ራስ ምታት ሆኖባታል። የግድቡን ወሬ ማራገቡ የዚህ ውጥረት ማስተንፈሻ መሆኑ ነው። የሲናይ በረሃ የራሷ ግዛት ቢሆንም የምትመካበት ወታደሯ ይህንን መቆጣጠር አይችልም። በመሆኑም የግብፅ ዋና ተጋላጭነት በኢትዮጵያ በኩል ሳይሆን በሰሜን ወይም ከምዕራቡ በኩል ነው።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአንካራ እና የካይሮ ባለሥልጣናት ፍጥጫ ላይ ይገኛሉ። ቱርክ በሊብያ በሚደረገው ጦርነት ከግብጽ በተቃራኒ ቆማ ሰንጋታለች። የደህንነት ስጋት ስለደቀነችባት ፕሬዚዳንት አልሲሲ ከቱርኩ መሪ ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ የሚገኙትን የፈረንሳዩን ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ወዳጅ መስሎ ከጎኑ ለመሰለፍ እየተጣጣረ ነው። የሚገርመው አልሲሲ እስላም ቢሆንም ቋማርተኛ የሆነ መሪ መሆኑ ነው። በምስራቅ ሜዲትራኒያን በኩልም ፉክክራቸው ጦፏል። በዚህም ግብጽ አፍንጫዋ ስር አደገኛ የጂኦፖሊቲካ እሽቅድምድም በቱርክ ተጋርጦባታል ማለት ነው።

የኢትዮጵያ በአባይ ላይ የሚሰራው የሀይል ማመንጫ ግድብ ለሱዳን ቀጥተኛ የሆነ ጥቅም የሚያስገኝላት በሆነበት ለግብጽ ሕዝብ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት አይደቅንም። የአሜሪካው መሪ እንዳለው “ውሃው የሚቆም” ሳይሆን ሃይል አመንጭቶ ለዘመናት በተለመደው አኳኋን የሚፈስ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለዓለም የምታስተጋባው “ከግማሽ የሚልቀው ሕዝቤ መብራት አያገኝም በመሆኑም ግድቡ የምገነባው ለዚህ ዓላማ ነው” ተማፅኖዋ ብቻ ከጥቃት ይከላከልላታል ማለት ግን አይደለም።

በመሆኑም የምዕራባውያን ሴራ በአፍሪካ እንዲሁም የግብጽ ጂኦፖለቲካዊ እሽቅድምድም ያልተቀደሰ ጋብቻ የፈፀሙ በመሆኑ ለዚህ እኩይ ግብ ኢትዮጵያን ለመቅበር ከውጭ ጠላት ጋር በማበር የምዕራባውያን ሴራ አስፈጽማለሁ የሚሉ የውስጥ ጠላቶች በቅድሚያ አይቀጡ ቅጣት መቅጣት እንደምትችል ማሳየት አለባት። እንደዚያ ሲሆን ነው ኢትዮጵያና ግብጽ ተከባብረው ፈጣሪ ያደላቸውን ተዝቆ የማያልቀው ሀብት ለቀጣይ ዘመናት መቋደስ የሚችሉት።

በዚህምኢትዮጵያጥልፈውሊጥሏትላሰፈሰፉየውስጥናየውጭጠላቶቿየሞንጎሊያውያንድንቅአባባልየሆነው“ብርድልብስህእስከሚዘረጋድረስብቻእግሮችህንዘርጋ – Only stretch your legs as far as your blanket extends” ልታስታውሳቸውይገባል።እንዲህሲሆንብቻሁሉምከወንዙየድርሻውንተከባብሮመጠጣትይችላል።

እውነተኛው የዶናልድ ትራምፕ ፍላጎት ምንድነው?
ትራምፕን እንደዛ ብግን፣ እርር፣ ድብን ብሎ ኢትዮጵያ ላይ ዘለፋ ያቀረበው በዋናነት ለእኔ እንደተባለው ለግብጽ አዳልቶ አይመስለኝም። ለግብጽማ ፈተና ሆነባት። ትራምፕን ጅላጅል እንደሆነና የሚናገረውን የማያውቅ አድረገው የሚመለከቱት ብዙ ናቸው። እውነታው ግን የተዋጣለት የፖለቲካ ነጋዴም ጭምር መሆኑ ነው። በመሆኑም ጥርሱን የነቀለበት የቢዝነስ ልምዱን በመጠቀም የአሜሪካ ሕዝብ ምን አይነት ሐሳብ ቢቀርብለት ተደስቶ እንደሚሸምት ስለተረዳ ለፍላጎታቸው የሚመጥናቸውን አስተሳሰብ በማቅረብ በምርጫ እንዲሸምቱት አድርጓል። ቀጣይነቱም ወደፊት የምናየው ይሆናል። ኢትዮጵያን ነክቶ ግን የተሳካለት የለም።

እንደሚታወቀው ሰውዬው “አሜሪካንን እንደገና ወደገናናነቷ እመልሳታለሁ” የሚል አይደለም ነው። እንግዲያውስ “የአሜሪካ ገናናነት ዳግም የሚገነባው በማን ላብ ላይ ተመስርቶ ነው?” ብለን መጠየቅ አለብን። ታሪክ እንደሚያሳየው አፍሪካ (በተለይ ከሰሃራ በታች ያለው የአፍሪካ ክፍል) ለሃብታም ሃገራት ብልጽግና መሰረት ነው። በዚህም አፍሪካ የጥሬ እቃ አምራችነት ሚና ብቻ እንዲኖራት ይፈለጋል። አፍሪካ ከዚህ እንድታመልጥ አልተፈቀደላትም። በመሆኑም አሁን ያለው የአለም የኢኮኖሚ ስርዓት እንዲቀጥል ሀብታም ሀገራት ሁሉንም ከማድረግ አይመለሱም። ምክንያቱም የአፍሪካ መድማት ለእነሱ ምቾት አስፈላጊ ነው።

የዓለም አቅፍ የኢኮኖሚ አወቃቀር፣ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ተቋማት እና መደበኛ የኢኮኖሚክስ የማስተማሪያ ዘዴዎች (ርዕዮተ-ዓለም) አፍሪካን አሁን ባለችበት ለማቆየት የተቀየሱ መሣሪያዎች ናቸው። የአፍሪካ ድህነት አብዝቶ ይፈለጋል ስልህ! በዓለም ባንክ በኩል ይመጡና ደግሞ “የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም – poverty alleviation programme” ይሉሃል። አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት የተለየ ነገር ማድረግ ከጀመረች የአውሮፓ፣ የሰሜን አሜሪካ እና አሁን የኤስያ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ያሽቆለቁላል ብለው ያስባሉ። በዚህ መሠረት ምዕራባዊያን አፍሪካ ቀና እንድትል አይፈቅዱም። የርዕዮተ ዓለም አምራች ስለሆኑ አፍሪካውያን አሁን ባሉበት ብቻ እንዲቀጥሉ በማሳመን ላይ ናቸው። የምዕራቡ ዓለም የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አፍሪቃውያን ትኩረታቸውን ወደሌላ እንዳያዞሩ አጥብቀው ይነግሯቸዋል። እምቢ ሲሉም እንደትራምፕ “ኢትዮጵያ የተመደበላት ገንዘብ በአይኗ አታየውም” በተጨማሪ ሃይል ለመሞከር ይከጅላሉ። የፈረንሳይ ተንኮል በምዕራብ አፍሪካ የቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿ ላይ ማንሳት ለዚህ አስረጂ ነው። የትራምፕ እውነተኛው ምሬት መነሻ የቱ እንደሆነም አሳብቆባቸዋል።

አፍሪካ ለዓለም ገበያ ከፍተኛ መጠን ያለው የግብርና እና የማዕድናት ሸቀጥ ብታቀርብም፣ የገበያ ዋጋው በጣም ትንሽ ስለሆነ የልፋቷን ያክል ተጠቃሚ አልሆነችም። ይሄ ዝም ብሎ የሆነ ከመሰለን ተሳስተናል። በዚህም አፍሪካ ለፍታ መና እንድትቀር አሲረውባታል። ይህንን መረዳት “አፍሪካ ለምን ደኸየች” ብሎ ኢንተርኔት ፈለግ ፈለግ ማድረግ ነው። በታሪክ እንደሚታወቀው ያለማኑፋክቸሪንግ መስፋፋት በዓለም ላይ ያደገ አንድም አገር አለመኖሩን ነው። በግብርና ብቻ ብልጽግና ማረጋገጥ አይቻልም ለማለት No Vegetarian Tiger የሚል አስረጂ ገለፃ አለ። በመሆኑም የግብርና ጥሬ ዕቃዎችን በማምረትና በመሸጥ ተወዳድረን የትም አንደርስም። በተሰራው እኩይ ሥራ በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ምርት ከጠቅላላው የአገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ እያሽቆለቆለ ይገኛል። በደንብ እንዲገለፅልን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (Foreign Direct Investment) ስም ወደኢትዮጵያ ገብተው ከመንግሥትት ባንክ ግዙፍ ብድር ወስደው የሚሰወሩት አካላት ግባቸው እስካሁን የተገለፀልን አይመስልም። የሚያሳዝነው ግን ለዚህ የውጭ ዝርፊያ የሚያመቻች የነበረው አገሪቷን እመራለሁ የሚለው እኩይ ቡደን ነበር።

የምዕራባውያን የምጣኔ ሀብት ምሁራን እና ፖሊሲ አውጪዎች አፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት ማካሄድ እንደሌለባት ይወተውታሉ። ጥሬ እቃዎችን ብቻ በማቅረብ አፍሪካ የተረጋጋ የኢኮኖሚ እድገት እንደማታሳይ ጠፍቷቸው አይደለም። ከታሪክ እንደምንረዳው የአፍሪካ እድገት የበለፀጉ አገራት የኢኮኖሚ ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ ነው። የኤሽያ አናብስት የኢንዱስትሪ ልማት ሲያካሂዱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ አስደናቂ ስኬት አስመዝግቧል። ለዚህ ምክንያቱ በእነዚህ አገሮች የኢንዱስትሪ ልማት ሂደት ላይ አፍሪካ ከፍተኛ የጥሬ አቅርቦቷ ከፍተኛ በመሆኑ ነበር። እነዚህ አገራት የእድገት ጫፍ ሲደርሱ በአፍሪካ እድገት ማሽቆልቆል ጀመረ። አሁንም በአፍሪካ እየታየ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ቻይና ከአፍሪካ በገፍ በምትወስደው የጥሬ አቅርቦት ገበያ የተነሳ ነው። በቀጣይነት እንዲሁ ቻይና ስትቆም አፍሪካም ባለችበት ትረግጣለች ማለት ነው።አፍሪካ በወጪ ንግዷ መዋቅራዊ ችግር የተነሳ ከፍተኛ የክፍያ ሚዛን መዛባት (Balance of Payment Imbalances) አለባት። ከአይኤምኤፍ እና ከዓለም ባንክ የተውጣጡ የኤክስፐርቶች የወጪ ንግድን ለማሳደግ በዚህም የንግድ ሚዛንን ለማሻሻል የገንዘብ ምንዛሪ ቅነሳ (Currency devaluation) እንዲደረግ ይወተውታሉ። ይህንን ምክር ተቀብሎ ያልተገበረ የአፍሪካ ሀገረ ማግኘት ያዳግታል። ነገር ግን ይህ “ምክር” ለአፍሪካ አገራት ጉዳት እንጂ ጥቅም የሌለው መሆኑ ነው።

ስለዚሁ ጉዳይ “የዐብይ መንግሥትት የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Abiynomics) “ስኬቶች” በሚል ርዕስ በዚሁ ጋዜጣ ከጥቂት ወራቶች በፊት ባወጣሁት አጭር ጽሁፍ የገንዘብ ህትመና መቀነስ የሚያስከትለው ጉዳት አመላክቻለሁ። ለዚህ አፍሪካ ላለባት የንግድ ሚዛን ጉድለት ማሟያ ከፍተኛ የሆነ ብድር እና እርዳታ ያቀርቡላታል። አዝነውላት ሳይሆን ማሰሪያ ናቸው። እነኚህ ኹለቱም የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ለመረዳት የፈለገ ዛምቢያዊቷ ኢኮኖሚስት Dambisa Moyo “Dead Aid” እንደዚሁም John Perkins የተባለ ፀሐፊ “Confessions of An Economic Hit Man” የተሰኘውን መጽሐፍ ፈልጋችሁ እንድታነቡት እመክራለሁ።

Perkins እንዳለው ዓለም-አቀፍ የኢኮኖሚ ስርዓትን ለማስቀጠል በአፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ አህጉራት የሚገኙ አፋኝ አገዛዞች በሥልጣን እንዲቆዩ ለማድረግ በብድር ተብትቦ የመያዝ ስትራቴጂ ነው። ለዚህ የምዕራባውያን የተፈጥሮ ሀብቶች የማጋበስ ስግብግብነት ግዙፍ ብድሮች ቅልፍ ሚና ይጫወታሉ። በማዕድን የበለፀገችው ኮንጎ ለዘመናት ትርምስ ውስጥ የገባችው በዚህ ምክንያት ነው። የእነዚህ አገራት መሪዎች ብድሩን ለመውሰድ አሻፈረኝ ካሉ እንደሆነ ምን እንደሚከተላቸው የPerkins መፅሐፍ የሚለው አለው። ዓላማው በዓለም ላይ ሀብትን በማጋበስ የአሜሪካ ልዕለ ሃያልነት መገንባት (Building American Empire) ነው። ጉዳዩ ይህ መሆኑን ትራምፕ አይኑ ኢትዮጵያ ላይ ቀይ የሆነበት ምክንያት አሁንም አልተገለጠልኝም የሚል የዋህ አይጠፋም። በሚቀጥለው ክፍል ሰፋ አድርገን እናየዋለን።

ጂኦ-ፖለቲካዊ (geopolitical) ጉዳይ
ይህ በአጭሩ ሲገለፅ የጂኦስትራቴጅ፣ የጂኦ-ኢኮኖሚክስ እና የጂኦ-ቴክኖሎጂ መስተጋብር ነው። ጂኦ-ቴክኖሎጂ ሚናው በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ተፅእኖውን ለመቆጣጠር እና ለማስፋፋት የሚያስችልው ማንኛውም ቴክኖሎጂ ማለት ነው። ንግድን በገፍ ለማቀላጠፍ የባቡር ትራንስፖርት መስፋፋት ለጀርመን እድገት መነሻነት ነበረው። ኢትዮጵያም እድገቷን ለማፋጠን ከምዕራባውያን ፍላጎት በተፃረረ መልኩ እንድትታይ ያደረጋት በተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች (የሃይል ማመንጨት፣ የባቡር፣ የፋብሪካዎች…ወዘተ) ሥራ ላይ ትገኛለች። በተለይ ወንዞቿን ተጠቅማ አገሪቷን ብርሃን ለማልበስ ደፋ ቀና ማለት ከጀመረች ውሎ አድሯል። የአገራት የልማት መጠን የሚጠቁም Night Light Data የሚባል ነገር አለ። ይህ በGoogle Map አማካኝነት በማታ ብርሃናማ የሆኑ አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም እንዳላቸው ይቆጠራሉ። ኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦት እጥረት ስላለባት ጨልሞባት ይገኛል። የሃይል አቅርቦቱ ለኢንዲስትሪ መስፋፋትም የሚያበረክተው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው። የኤሌክትሪክ ሃይል በሌለበት ኢንዱስትሪ ብሎ ነገር የለም። እንግዲህ የምዕራባውያን ድንጋጤ የሚጀምረው እዚሁ ጋር ነው።
ጂኦስቴራጂ በመሠረቱ በዓለም ኃይል ስርጭት (Power Distribution) ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የፀጥታ ሃይል የመጠቀም ችሎታ ነው። እንደሚታወቀው በኢኮኖሚ እዚህ ግባ የሚባል አቅም ባይኖረንም በአካባቢያችን ላይ እንደኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚችል ሃይል የለም። ጂኦ-ኢኮኖሚክስ በመሠረቱ ኢኮኖሚያዊ ጡንቻን ያመለክታል። በአካባቢው ላይ አንድ አገር ለዓለም ኢኮኖሚ እስትንፋስ የሆነ ጉዳይ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ከቻልች ሌላኛው ጥንካሬ ነው።

ኢትዮጵያ ግድቧ ለዚህ ዋነኛ መሣሪያዋ ይሆናል። በተጨማሪም የኢኮኖሚው የማምረት አቅምና መረጋጋት እንደዚሁም የሰው ሃይልና በመሬቱ ላይ የሚመረተው ምርት ጉዳይ ዋነኛው ነው። በመሆኑም ጠንካራ ጂኦስትራቴጂ እና ጂኦ-ኢኮኖሚክስ ጥምረት በማጠናከር ኢትዮጵያ በአለም ስርዓት ውስጥ ተፅዕኖ ለመፍጠር እየተጋች ነው ተብሎ ተፈርቷል።

በዓለም የእሽቅድምድም ስርዓት ውስጥ ለመጫወት የሚያስፈልገው የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህኅበራዊ አቅሞችን ማዳበር ከተቻለ በሌሎች ተዋንያን ድርጊቶች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ወይም እነሱኑ መልሶ መቆጣጠር አቅም ይፈጥራል። በመሆኑም የአቅም መገንባትና ሌሎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ብቃት እርስ በርሳቸው ይደጋገፋሉ። ስለዚህም የኢኮኖሚና የሚሊታሪ አቅም እየተገነባ ሲመጣ በአለም አቀፍ የሃይል አሰላለፍ ስርዓት (global power distribution) ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን ብቻ ሳይሆን የሃያላኑ ቁጥጥርም መቃወም ያስችላል። ስለሆነም የአንፃራዊ አቅም የማሳደግ አንድምታው በዓለም አቀፍ ስርዓት ውስጥ ያሉ ሃያላን (ተዋናይ) ተጽዕኖ መቀነስ ያስችላል። በግለሰብ ደረጃ ብዙ ተምረህ/ሽ አቅም ስታጎለብት/ቺ ከበላይህ የሚኖሩት አለቃዎች ሰንሰለት እንደምትቀንሰው/ሺው እንደማለት ነው። ተፈላጊው ኃይል ለማዳበር በአካባቢው ላይ የሚኖረው ተሰሚነት መጨመር አስፈላጊ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ያለ ወታደራዊ አቅም የሚታሰብ አይደለም። ይህ በኢኮኖሚ አቅም ላይ የሚመሰረት እንደሆነ ግልፅ ነው።

ከላይ እንዳየነው ጂኦ-ኢኮኖሚክስ በዓለም አቀፍ ተዋንያን የኃይል ስርጭት ላይ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚያገለግል ነው። ፈረንጆች Economic Wafare ይሉታል። ጂኦ-ቴክኖሎጂ ኹለቱንም ደግፎ ይይዛል። ጂኦስቴራጅካዊ እና ጂኦ-ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ሊኖር የሚቻለው ከተፎካካሪ በቴክኖሎጂ ልቆ በመገኘት ብቻ ነው።

የህዳሴው ግድባችን ህልውናችን ነው
ጠቅላይሚንስትርዐብይጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተገኝተው ማብራሪያ ሲያቀርቡ ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው የፀጥታ ስጋት የሚመለከት ነበር።እሳቸውም ሲመልሱ አሁን እየታየ ያለው የፀጥታ ስጋት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጋር የተገናኘ እንደሆነ “ከሕዳሴጋርይገናኛል።የሕዳሴን መንገድ መቁረጥ ጋር ይያያዛል” ሲሉ ተደምጠዋል።ቀጥለውም “ችግሩአሁንምከምንጩካልደረቀዳግምይከሰታል” ሲሉ የተሰሙ ሲሆን መንግሥታቸው ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንደሚሰራም ተናግረዋል። ከዚያ አጥንት ድረስዘልቆ ከሚገባው የወገኞቻችን ጥቃት ህመም ብዙ ምሳንቆይ እንዳሉትም በዚያው በምዕራቡ አዋሳኝ (በወለጋ) በድጋሚ ለሰሚውም የሚከብድ ዘግናኝ ጥቃት በአማራብሔር ተወላጆች ላይ ተፈፀመ። ይህንን ደምረን ስናየው በዋናነት የምዕራቡ የአገራችን ክፍል የማተራመስ ተልዕኮ ያነገበበው ሃይል ጭምር የሚታገዝ ስለመሆኑ በቀላሉ መረዳት እንችላለን።በዚህ ከቀጠልን ውሎአድሮ አደጋው የከፋ እንደሚሆንና ሃገሪቷ ለውጭ ሃይሎች መፈንጫ እንዳትሆን የግድቡ 360 ዲግሪከአደጋ ነፃ ማድረግ የግድ ነው።

ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ አደጋ ለማድረስ ኢትዮጵያ ድረስ በአካል መጓዝ አይጠበቅባትም። የግብጽና የምዕራባውያን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉ “የእናት ጡት ነካሾች” አሉ። እነዚህ የአፍሪካንም ተስፋ ለማጨለም የተሰማሩ ባንዳዎች ናቸው። አፍሪካ በቅኝ ገዢዎች እንዲጨልምባት ተደርጋለች። ኢትዮጵያ ቀድሞውንም ቅኝ ገዢዎችን አሳፍራ በመመለስ ለአፍሪካ ብቻም ሳይሆን ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች ብርሃን ፈንጥቃለች። ኢትዮጵያ ዳግም ለአፍሪካውያን መንገድ እንድትሆን አይፈልጉም። ይሄ ሀቅ ነው።

በመሆኑም ሀገራችን በአካባቢው ለሚኖራት የጂኦፐለቲካዊ ጉዳዮች ሚና ለመጫወት በምታደርገው ጥረቷ ላይ እንቅፋት እየሆኑባት ያሉት የአገር ውስጥ ዕኩያንን መከላከያችን የገቡበት ገብቶ መደምሰስ አለበት። እነዚህን መምታት ቁልፍ የጂኦ-ስትራቴጂክ ስኬታችን አካል ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ የማይፈለግ የሰውም የንብረትም መስዋዕትነት መከፈሉ የማይቀር መሆኑ ግልፅ ነው። ኢትዮጵያ ሰንኮፉን ለመንቀል ተገዳ የገባችበት ጦርነት ነው። የግድቡ ተደራዳሪና አደራዳሪዎች ተቀናጅተው የእጅ አዙር አደጋ እንደደቀኑብን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም። ለዚህ ተልዕኮ “የእናት ጡት ነካሾቹ” የቅጥረኝነት ሚና እየተወጡ ነው።
በዚህ ዘመን የግል ጦር (Mercenaries) በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ንግድ እንደሆነ ይገለፃል። በዚህ ሕገ-ወጥ ገበያ ውስጥ የሚተላለፈው የገንዘብ መጠን ባይታወቅም ቢዝነሱ እያደገ መምጣቱ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዋናነት በመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ አገራት የቅጥረኛ ወታደሮች እንቅስቃሴ በሰፊው እየታየ ነው። የእነዚህን አገልግሎት ለማግኘት መንግሥትታት የተጠየቁትን ገንዘብ ከመክፈል ወደኋላ አይሉም። የውጭ ቅጥረኞች መጠቅም የተለያዩ ጥቅሞች እንደሚያስገኙ ቢገለፅም ዋነኝው ቅጥረኞችን መጠቀም የሚያስገኘው ጥቅም አስተማማኝ ክህደት (deniability) መፈፀም የሚያስችል መሆኑ ነው። ጦርነት ሁሌም የድርድር ቀጣይነት ሲኖረው እናም የግል ተዋጊዎችን በመቅጠር መንግሥትታት ጥቅሞቻቸውን ያስጠብቃሉ። ከዚያም እኔ አልፈፀምኩትም ብለው ሽምጥጥ አድርው ይክዳሉ። እንግዲህ ወታደር በማከራየት ልምድ ያካበተ ቡድን ለእነዚህ አካላት “ቅጥረኛ” አይሆንም ማለት አይከብድም?
ግብፅ የኢትዮጵያን ግድቡን ለማደናቀፍ ከዲፕሎማሲያዊ ጫናዋ በተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንድትወስድ በተደጋጋሚ ብትዝትም እስካሁን በቀጥታ የተሳተፈችበት ጥቃት የለም። ለዚህ ብዙ መላምቶች ይቀርባሉ። ለዘመናት የነበረው ዛቻ የተጧጧፈው ገና የመሠረት ድንጋዩ እንደተቀመጠ ነበር።

ቻላቸው ታደሰ የተባሉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የገቨርናንስና ልማት ጥናት ትምህርት ቤት መምህር እ.ኤ.አ 07 ጥቅምት 2012 “የህዳሴው ግድብና የዊኪሊክስ መረጃ አንድምታ” በሚል ርዕስ ድንቅ ጽሑፍ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ አስነብበውን ነበር። ይህ ጽሑፍ አሁንም ከኢንተርኔት ላይ ፈልጎ ማግኘት ይቻላል። እንደፀሃፊው ገለፃ ወቅቱ የመለስን ዜና ዕረፍት የተሰማበት እንደነበረና ይህንን ተከትሎ ከግድቡ ጋር በተገናኘ ትኩረት የሳበው ዊኪሊክስ (Wikileaks) የለቀቀው መረጃ ግብፅ የህዳሴውን ግድብ ለማደናቀፍ የሚያስችላትን የጦር ሠፈር ሱዳን ውስጥ ለማቋቋም ፈቃድ መግኘቷን የሚያመላክት ነበር። ግብጾች የትራምፕ ንግግርን እንዳስተባበሉት ይህንንም አስተባብለዋል።

በዚህ ጽሑፍ እንደተነሳሱ በመግለጽ ደስታ ታከለ የተባሉ ግለሰብ በተመሳሳይ ጋዜጣ ላይ መረጃ ትክክል ሆነም አልሆነ ኢትዮጵያ በግዴለሽነት ማየት እንደሌለባት “ግብፅ የዓባይን ግድብ ለማጥቃት ካሰበች የኢትዮጵያስ አፀፋ ምን ይሁን?” በሚል ርዕስ እኔም የምጋራው ሐሳብ ሰንዝረዋል። እንደፀሐፊው “ለኢትዮጵያ ደኅንነት ብቸኛውና አስተማማኙ የቅድሚያ መከላከል የሚሊታሪ ዶክትሪን (Deterrance) ወይም ተያይዞ መጥፋትን ‹‹Mutual Assured Destruction (MAD)›› ፖሊሲ መከተልና ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሊታሪ አቅም መገንባት ነው። ይኸውም ግብፅ የኢትዮጵያን ግድብ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ በኃይል አደናቅፋለሁ ብላ ካሰበችና ከተንቀሳቀሰች የኢትዮጵያ የአፀፋ መልስ አስዋን ግድብን ማጥቃት መሆን አለበት” ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። አያይዘውም “አስዋን ግድብን በማውደም ከግድቡ የሚያገኙትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማጥፋት ወደ ጨለማ ልንከታቸው እንደምንችል፣ ከግድቡ ጋር በተያያዘ የሚያገኙትን የኢኮኖሚ ጥቅም እንደሚያጡ፣ ከአስዋን ግድብ ጀምሮ ያሉት ከተሞቻቸው ከዐሥር ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሚኖርባትን ካይሮን ጭምር በጎርፍ ታጥበው ሜዴትሪንያን ባህር ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ የሚያስገነዝብ ፖሊሲና ስትራቴጂ ኢትዮጵያ መከተል አለባት። ይህንም ፖሊሲ ለግብፅና ለዓለም ሕዝብ በግልጽ ማሳወቅ የግድ ነው።

ስለሆነም ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ ከሚያደርሱት ውድመት በላይ እንደሚወድሙ ማሳወቅ ለሚያደርሱት ጥፋት የሚደርስባቸው ድርጊት የከፋና የበለጠ መሆኑን ብቻ ሲገነዘቡና ሲያውቁ በሰላም ተባብሮ መሥራትን ይመርጣሉ” ብለው ሃሳባቸውን ደምድመዋል። የተነሳሁበት ርዕሰ ጉዳይም ይህንኑ ለማስመልከት ስለነበር ፀሃፊውን ከማመስገን ውጭ በግሌ ጎደለ ብዬ የምጨምረው አንዳችም የለኝም።

ሽመልስ አርአያ በጀርመን አገር ከሚገኘው ጊሰን ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስየዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት አገልግለዋል። በዚህ araya.gedam።gmail.com ማግኘት ይቻላል።

ቅጽ 2 ቁጥር 106 ኅዳር 5 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com