እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ የላከችው የአንበጣ መንጋ ተከላካይ ግብረ ኃይል ሥራውን በነገው ዕለት ይጀምራል

Views: 340

የበረሀ አንበጣ ለመከላከል ወደ ኢትዮጵያ የገባው የእስራኤሉ የአንበጣ መንጋ ተከላካይ ግብረ ኃይል ከነገ ኅዳር 08/2013 ዕለት ጀምሮ እስከ አምሰት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ሥራውን እንደሚጀምር የግብርና ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉም ከነገ ጀምሮ ሥልጠናውን የሚሰጠው በሶማሌ ክልል እንደሆነም የግብርና ሚኒስቴር  የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበራ ለማ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

አበራ እንደገለጹት ከሆነም ክልሉ የተመረጠበት ምክንያት የበረሀ አንብጣ በሁሉም ክልሎች የተቆጣጠርን ቢሆንም በሶማሌ ክልል ግን መቆጣጠር ስላልተቻለ ነው።

ስልጠናው የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከማድረግ በተጨማሪ በድሮን በመታገዝ የኬሚካል ርጭት ለማድረግ እንዲሁም አንበጣው የት አካባቢ እንዳለ ለመጠቆም ይረዳል ያሉት አበራ በሥልጠናው ላይ ከ100 በላይ ሠራተኞች እንደሚሳተፉ ተናግረል።

የበረሀ አንበጣን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከእስራኤል የመጡት ባለሙያዎቹ ስልጠናውን ከመስጠታቸው በተጨማሪም ለስልጠና ይዘውት የመጡትን 27 ድሮኖችን ድጋፍ  አድርገውልን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ አበራ ገልጸዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com