ከያዝነው ወር ኀዳር 22 ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም የማይቻል መሆኑ ታወቀ

Views: 141

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 /2013 እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስታወቀ ሲሆን  ከያዝነው ወር ህዳር 22 ጀምሮ ደግሞ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም የማይቻል መሆኑም ተጠቁሟል።

ከመስከረም 6/2013 አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም ይታወሳል።

ከዚህ ቀን በኋላ በባንኮች አሮጌ የብር ኖት እንደማይኖርም ገልጿል።በዚሁ መሰረት የተፈቀደው የብር መቀየሪያ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 25 ቀናት ብቻ እንደቀሩት ይፋ መደረጉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com