ኹለት የቆዳ ፋብሪካዎች ታሸጉ

Views: 92

በአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃና ልማት ንብረት ኮሚሽን ኹለት የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካዎችን በትክክል ፍሳሽ ባለማስወገዳቸው ምክንያት ማሸጉን አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች።

ኮልፌ ቀራኒዮ የሚገኘው አዲስ አበባ የቆዳ ፋብሪካ እና በአቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው ዋልያ የቆዳ ፋብሪካ የተባሉተን ድርጅቶች የሚለቁትን ፍሳሽ ወደ ወንዝ ሲለቁ ታክሞ መለቀቅ ያለበት እንደሆነና ነገር ግን እነዚህ ኹለት ፋብሪካዎች ሳያክሙ ሲለቁ እንደነበር ስለተደረሰበት መታሸጉን ለማወቅ ተችሏል።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአዲስ አበባ አካባቢና ጥበቃ አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የኮሚንኬሽን ዳይሬክተር ሙክታር ሰኢድ እንደተናገሩት አንደኛ እና ኹለኛ ደረጃ የሚባል ኹለት አይነት የፍሳሽ አወጋገድ ስርአት እንዳለና ፋብሪካዎች የሚያስወጡት ፍሳሽ ቀጥታ ወደ ወንዝ እንደሚገባ ተናገረወል።

ይህ ፍሳሽ ሳይታከም መለቀቁ ደግሞ በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል።ከፋብሪካዎች የሚወጡ ፍሳሾችን የሚያክም ወይም ኹለቱንም ደረጃዎች የሚያከናውን መሳሪያ እንዳለ ተናግረዋል።

ነገር ግን አሁን የታገዱት ኹለቱ ፋብሪካዎች አዲስ አበባ የቆዳ ፋብሪካ እና ዋልያ የቆዳ ፋብሪካ ይሄ መሣሪያ እንደሌላቸው በዚህም ምክንያትሥራ እንዳቆሙ አረጋግጠናል።

በአገራችን ሰባት የሚሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎች እንዳሉ እና ከዚህ በፊት በ2010 ዓመት በዚሁ ምክንያት ስድስት የሚሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎች ሥራ እንዲያቆሙ እንደነበር አስታውሰው የስድስት ወር ቀነ ገደብ ተሰጥቶአቸው በስድስት ወር ውስጥ አስተካክለው ወደ ሥራ እንዲመለሱ ተደርጎ እንደነበር ነግረውናል።

ከወንዙ የሚወጣውን ውሃ የሚጠቀሙ እንዳሉ የጠቆሙት ኃላፊው መሣሪያው ሲገጠም ዝቃጩን ያስቀርና ፍሳሹን ለይቶ ጎጂ የሚባሉትን ኬሚካሎች አስወግዶ አክሞ እና መርዛማ እንዳይሆኑ አድርጎ ወደ ወንዝ እንደሚያስተላልፍ ነግረውናል።

እነዚህ ፋብሪካዎች በተሰጣቸው መመሪያ ያለባቸውን ችግር እስካልቀረፉ ድረስ እንደማይከፈቱ እና አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉም ተናገረዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com