ዲጅታል መታወቂያ በፍጥነት እየተሰራጨ ነው

Views: 158

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ዲጂታል ነዋሪዎች መታወቂያ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ ።
በከተማዋ የሚሰጠውን የነዋሪነት ምዝገባ አገልግሎት በዲጂታል በታገዘ መልኩ እየሠራ ያለው ኤጀንሲው ደህንነትን ለማስጠበቅ የመታወቂያ አሰጣጥን ዲጂታል በማድረግ አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረገ ሲሆን በጥቅምት ወር 2013 ብቻ ከ16 ሺሕ700 በላይ የሚሆኑ የዲጂታል መታወቂያ አትሞ ለተገልጋይ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክር አቶ ዮናስ አለማየሁ ገልፀዋል።
የዲጂታል መታወቂያ ሥራ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙት 98 ወረዳዎች በተቀላጠፈ መልኩ እየተሠራ እንደሆነም አስታውቋል።
ኮሚሽነሩ እንዳሉት የኤጀንሲው ሠረተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው ከሠሩ ባጭር ጊዜ ውስጥ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ ዲጂታል መታወቂያ እንዲይዝ ማድረግ ይቻላል ብለዋል ።
ተቋሙ የሚሠራውን ሥራ ካለማወቅ በአመራሩ ትኩረት ተነፍጎት መቆየቱን የገለፁት ኮሚሽነር አዱኛ አሁን ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤን ጨምሮ ሌሎችም ልዩ ትኩረት በመስጠታቸው አደረጃጀቱን ለማስተካከል እና ምቹ የሥራ ቦታ እንዲኖር ለማድረግ ፣ብሎም ኤጀንሲውን ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ተጠቅሞ የሕዝብ አገልግሎቱን እንዲያሰፋ ከፍተኛ በጀት እንደተመደበም አስታውቀዋል።
የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ታከለ ነጫ በበኩላቸው የተቋሙን የሰው ኃይል እና ግብአት ሙሉ ለሙሉ ለማሟላት ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ዲጂታል አገልግሎትን በሚመለከት ባለሙያዎች ዲጂታል ቴክኖሎጂውን ያለመጠቀም ፍላጎት መኖሩን እና የነዋሪዎችን አገልግሎት ጨምሮ ከሲስተም ጋር የማይገናኝ አግልግሎትን ሲስተም የለም በማለት ባለጉዳይን የማመላለስ ችግሮች እንዳሉ በግልፅ ይታያል ያሉት ዳይሬክተሩ እነዚህ ችግሮች ለመፍታ እና ለማስተካከል ክፍለ ከተማው በመናበብ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com