የሕክምና ባለሙያዎች ቅጥር

Views: 125

ለከፍተኛ ትምህርት በሚላኩ ጠቅላላ ሐኪሞች ምትክ አዲስ ተመራቂዎች ቅጥር የሚመደበው ወጪ በየአመቱ ከሚመረቁ ግማሽ ያህሉን ለመቅጠር ያስችላል ሲሉ የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተግባር ይግዛው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታወቁ።
በየዓመቱ ቁጥራቸው አንድ ሺሕ የሚደርስ ጠቅላላ ሐኪሞች ለስፔሻላይዜሽን ትምህርት ወደየተለያዩ የዩንቨርሲቲ ሆስፒታሎች ይላካሉ፤ በእነዚህ ሐኪሞች ምትክ አዳዲስ ሐኪሞች ሲቀጠሩ ደግሞ በየአመቱ በኢትዮጵያ ከሚመረቁ ጠቅላላ ሐኪሞች ግማሽ ያህሉን ለመቅጠር ያስችላል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ጋር በመሆን ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚላኩ ጠቅላላ ሐኪሞችን ደምወዝ እየከፈለ በምትካቸው የክልል ሆስፒታሎች ሐኪም መቅጠር የሚችሉበትን አሰራር ከዘረጋ ሦስት ዓመታን ቢያስቆጥርም አሁንም ድረስ ሙሉ በሙሉ በሚባ ደረጃ ቅጥር ያልፈፀሙ የክልል ጤና ቢሮዎቸዎች እንዳሉ ነው አዲስ ማለዳ ከጤና ሚኒስትር የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክተር ከሆኑት አሰግድ ሳሙዔል ለማወቅ የቻለችው።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ጠቅላላ ሐኪሞችን ወደየ ክልልሎች ድልድል ካደረገ በኋላ ክልሎች ቅጥር ይፈፅማሉ። ነገር ግን እነዚህ ጠቅላላ ሐኪሞች ለስፔሻላይዜሽን ትምህርት ወደየተለያዩ የዩንቨርሲቲ ሆስፒታሎች ሲላኩ የእነሱ የሥራ መደብ ክፍት ስለሚሆን እንዲሁም ሥራ የሌላቸው ሐኪሞችን ለመቅጠር ሲባል እንደመፍትሄ የተወሰደ ተግባር ነው ብለዋ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com