10ቱ አንፃራዊ ሰላም ያላቸው ከሳህራ በታች አገራት

Views: 216

ምንጭ፡-አለም አቀፉ የኢኮኖሚ እና ሰላም ኢኒስቲትዩት

አለም አቀፉ የኢኮኖሚ እና ሰላም ኢኒስቲትዩት ‹‹ሰላምን መለካት ውስብስብ በሆችው አለም›› በሚል በ2020 ባወጣው ሪፖርቱ እንዳስታወቀው በ2020 ከሳህራ በታች ያሉ አገራት የውስጥ ሰላም ማጣት እና የእርስ ግጭት በመጠኑ ከፍ ማለቱን አስታውቋል። በሪፖርቱ እንደተገለፀው ከሆነ በቀጠናው የሚገኙ 20 አገራት ሰላማቸው የተሻሻለ ሲሆን 24ቱ ደግሞ እየተበላሸ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ባለፉት ዓመታት ውስጥ በምርጫ ውጤቶች ላይ የሚነሱ የአለመግባባት ጥያቄዎች እንዲሁም ፖለቲካዊ ለውጥን መሻት በብዙ አገራት ላይ ሕዝባዊ አመፅና ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን እንዳስከተለ መረጃው አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ከሳህራ በታች ካሉት አገሮች በአንፃራዊ ሰላም ሞሪሽየስ አንደኛ ደጃን ስትይዝ ቦትስዋና፣ ጋና፣ ዙምባቤ እና ሴራሊዮን ከኹለት እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
አገራችን ኢትዮጵያም በመለኪያው መሰረት ከሳህራ በታች ከሚገኙ አገሮች 34ኛ ከአለም ደግሞ 133ኛ ስትሆን፤ 44ኛ እና የመጨረሻውን ቦታ እንዲሁም በአለም 160ኛ ደረጃን የያዘችው ደቡብ ሱዳን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰላሟ የተሻሻለ እየመጣ መሆኑንም ሪፖርቱ አመላክቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com