ማክሲማ ዚ የተሰኘ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ተመረቀ፤

Views: 265

በዓመት 30 ሺሕ ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎችን ይገጣጥማል

በኦሮሚያ ክልለ አዳማ ከተማ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ መዋእለ ነዋይ የፈሰሰበት ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎችን የሚገጣጥም ፋብሪካ  ወደ ሥራ መግባቱ ታወቀ፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ 100 ኪሎ ርቀት ላይ በምትገኘዋ አዳማ ከተማ ከሦስት ዓመታት በፊት በተረከቡት 50 ሺህ ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ የተገነባው ፋብሪካ ሶስት የማምረቻ እና አንድ መጋዘን ያለው ሆኖ እያንዳንዳቸው በ 7 ሺሕ 500 ሜትር ስኬር ቦታ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በየካቲት ወር 2015፣ የሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ አባል   የሆነው ሆራ ትሬዲንግ ከሕንድ አገር ከሚገኘው ግዙፉ  8AJAJ አውቶ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ  ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም መፈራረማቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አደም፡፡

ኩባንያቸው በ56 ደቂቃ 23  ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ መገጣጠም እንደሚችል ምንተስኖት ተፈራ የሞተር ዘርፍ ምክትክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

በአገራችን የተለመደው አንድን ንግድ ከጅምላ እስከ ችርቻሮ ድረስ በቤተሰብ ብቻ  ይዞ ከመነገድ  ወጣ ብለን ተደራሽ በምንሆንባቸው እያንዳንዱ ወረዳዎች ላይ በአካባቢ ነዋሪ የሆኑ አከፋፋዮችን መመልለላችን ልዩ ያድገናል ብለዋል አደም፡፡

እነዚህ አከፋፋች በቅድመ ሽያጭም ሆነ ከሽያጭ በኋላ በተመሳሳይ ደረጃ ወጥ የሆነ አገልግሎቶችን በሁሉም ወረዳዎች ላይ ለደንበኞች እነዲያቀርቡ ከማድረጋቸውም በላይ  አከፋፋያችንን በጂፒኤሰስ  በማገናኘት ተናብቦ እነዲሰሩ የሚያስችን አሰራር መዘርጋቱን አደም አንስተዋል፡፡

እንደዚህ አይነት አሰራር መዘርጋቱ ደንበኞች  የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባሻገር በስምንት ወራት ውስጥ ገንዘባቸውን ሊመልሱ የሚያስችል አሠራር መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ተገጣጥሞ ለገበያ የሚቀርበው ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ ባጃጅ ማክሲማ ዚ የተሰኘ ሲሆን ገበያ ላይ ከነበሩ ሌሎች ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች  ከመሬት ባለው የከፍታ መጠን ልዩ እንደ ሚያደርገው በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ተገልጻል፡፡

ከመቶ ሚሊየን በላይ በክምችት ያሉ መለዋወጫዎች አሉን ያሉት የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ከሽያጭ በኋላ የሚኖሩትን እንደ በአገር ውስጥ ከ220 በላይ ወኪል አከፋፋዮች እንዳሉ እና የአገሪቱን የባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪም 68 በመቶ የሚሸፍን እንደሆነ እና ከሽያጭ በኋላም አስፈላጊውን ጥገና የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጻል፡፡

የኢንዱስትሪ እና ማምረቻን ከማስተሳሰር አንጻር ከአዳማ ቴክኒክ ዩንቨርሲቲ ጋር በመነጋገር ምንም ልምድ የሌላቸውን ተማሪዎችን መልምሎ  ሕንድ አገር ለሦስት ወራት በማሰልጥን ወደ ሥራው እንዳስገባም የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ለአዲስ ማለዳ ተነግሯል፡፡

በዚህም ወደ 4ሺ የሚጠጉ ‹ፍራንቻይዝ› መካኒኮች ያሉት ሲሆን ለሥራው የሚያስፈልጉ ሁሉም መሣሪዎች በአለም ዓቀፍ ደረጃ የሚሰራባቸው እነደሆኑም ምንተስኖ በቀለ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በአገር ውስጥ ማምረት የሚቻሉ እንደ ወንበር፣ካንዴላ እና ሌሎች ጥቃቅን ግብአቶችን እዚሁ ለማምረትም እና የውጭ ምንዛሬን ለማስቀረትም እየሰሩ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

መገጣጠሚያ ፋብሪካው ከ350 በላይ ቋሚ እና 200 ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በዓመት እስከ 30 ሺሕ ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎችን የመገጣጠም  አቅም እንዳለውም ተገልጿል፡፡

 ከኩባንያው የምናስመጣቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንደሆኑ እና ለአገር ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለው አበርክቶ እንዲኖር ለማድረግ  ስመ ጥር የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም በአገር ውስጥ ለመገጣጠም ፍላጎት እንዳለው  አደም ተናግረዋል፡፡

ለገበያ የቀረበው አዲሱ ምርትም ከአገልግሎት ጥራት እና ከጥገባ ወጪ አንጻር የተሸሉ ምርቲች መሆናቸው ታወቋል፡፡ በተጨማሪም የአካባቢን ብክለት ከመቀነስ አንጻርም ዥቅተኛ የሆነ የብክለት መጠን እንዳለው ታውቋል፡፡

ሆራ ኮርፖሬት ኩባንያ ባለ ሦስት እና ባለ አራት እግር ተሸከርካሪዋችን ከመገጣጠም ባሻገር  ሦስት ትውልድን የተሻገረ የቡና ወጭ ንግድ ፣ ትራንዚት እና እቃዎችን በማስተላለፍ ፣በሪል እስቴት   እና በማምረቻ ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያ እነደሆነ ታውቋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com