በሁሉም ባንኮች 2.5 ሚሊየን አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች ተከፍተዋል

Views: 296

45 ቢሊዮን ብር ገቢ ተደርጓል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲሱን ገንዘብ መቀየር ከተጀመረ በኹለት ወር ጊዜ ውስጥ ኹለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን አዳዲስ የባንክ የቁጠባ ሒሳቦች በሁሉም ባንኮች የተከፈቱ ሲሆን በተከፈቱት ሒሳቦችም 45 ቢሊየን ብርገቢ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
ገንዘቡ ሲቀየር የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ ዶ/ር እንደገለጹት የእኛ አገር ኢኮኖሚ ጥሬ ገንዘብ ግብይት የሚፈፀምበት እንደሆነ እና በዚህም ምክንያት ከባንኮች ውጪ ያለው ገንዘብ ብዛት እንዳለው አስረድተው ነበር።

በጉዳዩ ላይ አዲስ ማለዳ ያነጋገራቸው የኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት ዋሲሁን በላይ እንዳሉት የተከፈተው የባንክ ደብትር የተቀመጠው ገንዘብም የሚበረታታ እና ከባንክ ውጪ ያለውን ገንዘብ ወደ ባንክ መግባቱ ጥሩ ጅማሬ ነው ብለዋል።

ነገር ግን የባንክ ደብተር ባለቤትነት እና ቆጣቢ መሆን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። የገንዘብ መለወጥን እና የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ለመገደብ በማሰብ ማንኛውም የገንዘብ ዝውውር ከአካውንት ወደ አካውንት መሆን እንዳለበት በሚያዘው እና ከአምስት ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ ለመለወጥ አካውንት እንዲከፈት በሚያዘው መመሪያ መሰረት በርካታ ሰዎች አዲስ የቁጠባ ሒሳብ ለማውጣት የተገደጉበት ሁኔታ መፈጠሩ ለዚህ ከፍተኛ የደንበኛ ቁጥር መጨመር ምክንያት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ይህንን መመሪያ ተከትሎ ከሚሊዮን በላይ አዳዲስ (የውዴታም ሆነ የግዴታ) የባንክ ደብተሮች ሲከፈቱ ፤የባንክ ደብተሮቹ መከፈታቸውን እንደስኬት ለመቁጠር ተቀማጩ ገንዘብ በባንክ በማቆየት ብሩ ተመልሶ በፍጥነት እንዳይወጣ ቢደረግ እና ተቀማጩ ገንዘብ ተመልሶ በብድር መልክ ለባለሀብቶች ተሰጥቶ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ ካልተቻለ የባንክ ደብተር መክፈት እና ቁጠባ ጥቅም ምንም ነው ብለዋል።

ይሁን እና የዜጎች የገቢ መጠን፤ በባንክ የማስቀመጥ የወለድ መጠን፤ የዋጋ ንረት መጠን፤ ስለቁጠባ ያለ አመለካከት፤ በመጪው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሚኖር መተማመን ከፍና ዝቅ ማለት እና ሌሎች ምክንያቶች የተከፈቱ አዳዲስ የባንክ ደብተሮች ፋይዳ እንዲኖራቸው የማድረግ ዕድል ይኖረዋል ሲሉም አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ።
በዚህ ወቅትበሚሊዮንየሚቆጠር የባንክ የቁጠባ ሒሳብ ደብተር ተከፈተ ማለት በኢኮኖሚው ውስጥ ተጨማሪ ሚሊዮን አዳዲስ ቆጣቢዎች ተፈጠሩ ማለት አይደለም ፤የገንዘብ ለውጡ አስገዳጅ ቁጠባን ለግዚያዊነት ቢፈጥርም፤ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲኖረው ከተፈለገ ግን ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች በመሰረታዊነት ሊሰራባቸው እና ዜጎች ለረጅም ጊዜ ሊቆጥቡት የሚችሉት የኢኮኖሚ ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ሊፈጠር ይገባል ባይናቸው።

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ውስጥ ምንም ብር የሌላቸው ብዙ የባንክ ደብተር ያለበት የባን ሴክተር እንዳይኖረን ያሳስበኛል ምክንያቱም ያለፍላጎት የተከፈተ አካውንት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ምንም ብር የማይኖረው ከሆነ ደብተሩ የታተመበትን ወጪ መሸፈን እንኳን የማይች ልሊሆ ንይችላል ሲሉም ባለሙያው ይናገራሉ።
ከዚህም አገራችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ምንም ገንዘብ የሌላቸው የባንክ ደብተሮች ሳይሆኑ የሚቆጥቡ ሰዎች ነው የሚያስፈልጓት ይህ ካልሆነ ግን የባንክ ደብተር ማስከፈቱ ምናልባት ከባንክ ጋር የማይተዋወቁትን ሰዎች ከባንክ ጋር ከማስተዋወቅ የዘለለ በኢኮኖሚው ላይ ጥቅም ለውም ሲሉም ይጨምራሉ።
ባንኮች ገቢ ሚያገኙት በብድር ከሚሰጡት ወለድ ነው፤ ያሉት ዋስይሁን ወለድ ለማግኘት ማበደር ለማበደር ደግሞ የተቆጠበ ገንዘብ ያስፈልጋል ይህ ሲሆን ኢኮኖሚው ላይ የሚስተዋለውን ችግር ማቃለል ይችላል ብለዋል።

“በገጠር አካባቢ ብዙ ገንዘብ አለ” ያሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ባንኮች በብዛት ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩት ከተማ አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው በወረዳ ከተሞች እና ወደ ገጠሩ አካባቢ ከፍተኛ የባንክ መስፋፋት ችግርን በመቅረፍ ባንኮች ገጠር አካባቢ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው።
በመጨረሻም ብዛት ያለው የባንክ ደብተር ሳይሆን በቋሚነት ቆጣቢ የሆኑ ሰዎችን ማፍራት ላይ በትኩረት ሊሰራበት ይገባልሲሉም ምክረ ሐሳባቸውን አስቀምጠዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com