በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ ሊደረግ ነው

Views: 386

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የፋይናንስ እና የቴክኒካል ድጋፍ ለማግኘት ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን በዚህ መሰረት የኤሌክትሪክ አውቶብስ በከተማው ላይ የሙከራ ትግበራ ለማከናወን ተቀማጭነቱ እንግሊዝ አገር  ካደረገው C40 Cities ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል።

ቢሮው ከC40 Cities ጋር በመተባበርም የኤለክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ በከተማ ፈጣን አውቶብስ (BRT) ኮሪደር ላይ እንዴት እንደሚተገበር በተመለከተ አለማቀፋዊ የኹለት ቀናት ቨርቹዋል አውደ ጥናት ማካሄዱም ለማወቅ ተችሏል።

የከተማ ፈጣን አውቶብስ (BRT) የሚጠቀምባቸውን በናፍጣ የሚሰሩ እና ሌሎቹን አዉቶቡሶች በቀጣይ ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር እቅድ እንደተያዘም ተነግሯል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com