10 በዓለም ውስጥ ከፍተኛ ምንዛሬ ያላቸው ገንዘቦች

Views: 432

ምንጭ፡-የተባበሩት መንግሥታት፣ ናይጄሪያን ኒውስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግሥታት በዓለም ዙሪያ በ 195 አገራት ጥቅም ላይ የዋሉና እውቅና ያላቸው 180 ገንዘቦች አሉ። የአሜሪካ ዶላር ፣ ዩሮ እና የጃፓን የን በቅደም ተከተል በምድር ላይ በጣም የታወቁ የገንዘብ ዝርዝርን ይይዛሉ። ነገር ግን በምንዛሬ ዋጋ ደረጃ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ምንዛሬዎች የተለያዩ የልውውጥ እሴቶች አላቸው። የምንዛሬ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ምክንያቶች መካከል አንዱ የአንድ አገር የኢኮኖሚ እድገት ነው። የምንዛሬ ዋጋ ቋሚ አይደለም፣ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠ የሚሄድ ነው።
በዚህም መሰረት በዓለማችን ከፍተኛ ምንዛሬ ካላቸው አገራት ውስጥ ኩዌት፣ ባህሬን እና ኦማን ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ሲይዙ ስዊዘርላንድ እና አሜሪካ ደግሞ ከአስሮቹ የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ በዘጠነኛና አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 112 ታኅሣሥ 17 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com