ጥቃቱ ያነጣጠረው በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ነው – ኢሰመኮ

Views: 594

ከሰኔ 22/ 2012 የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተከስተዋል። 123 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፣ በሽዎች ተፈናቅለዋል። 35 ሰዎች የተገደሉት በሁከቱ ላይ በተሳተፉ ሰዎች ነው የተገደሉት ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
አጥቂዎች ሰዎች እና ቡድኖች የሰዎችን ቤት ሰብረው በመግባት አቃጥለዋል፣ ደብድበዋል፣ አርደዋል፣ እንዲሁም አስከሬኖችን በአደባባይ ላይ እንዲሆን በማድረግ ለሰዓታት እንዳይቀበር አድርገዋል ተብሏል።
በህይወት እና ንብረታቸው ላይ ባጋጠመ ጥቃት ከ6000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠሩ ችግሮች የታዩ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ መገለጫ እየሰጠ ነው
የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተከሰተ ሁከት ጥቃቱ ያነጣጠረው በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ እንደሆነ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በወቅቱ ጥቃት ሲደርስባቸው ለህግ አካላት ነዋሪዎች ቢያስታውቁም አወንታዊ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው እና የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመቆጣጠር ዝግጁነት እንዳልነበረውም በመግለጫው ተጠቅሷል።
ከአማራ ብሔር ተወላጆች ባለፈም በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይም ጥቃት እንደተሰነዘረ ኮሚሽኑ በመግለጫው አካቷል የፀጥታ አካላት በሁከት ላይ ያልተሳተፉ ሰዎችን ገድሏል
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሀጫሉ ግድያ በኋላ በተፈጠረ ሁከት እጃቸው የሌለበት እና ያልተሳተፉ ሰዎች ቤታቸው ደጅ ላይ በፀጥታ ኃይል መገደላቸውን አስታወቀ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com