10 በዓለም አቀፍ ደረጃ የገናን በዓል የማያከብሩ አገራት

Views: 297

ምንጭ፡-ወርልድ ፖፕዩሌሽን ሪቪው (World Population Review)

የገና በዓል ወይንም የአውሮፓውያኑ የአዲስ ዓመት በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ጎርጎሮሳውያን ዘመን አቆጣጠር ዲሴንበር 25 ቀን ፤ በዋነኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በመዘከር የሚከበር ዓመታዊ በዓል ነው። የገና በዓል በዓለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ የክርስትና እምነት ተከታዮችም ሆነ የእምነቱ ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች የሚከበሩት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ በዓል ነው።
በአለም አቀፍ የስነ ህዝብ ግምገማ ተቋም መረጃ መሰረት የገና በዓል በዓለም ዙሪያ በ160 አገሮች ውስጥ ይከበራል። የበዓሉ የአከባበር ስነ ስርዓትም እንደየ አገራቱ የሚለያይ ሲሆን አንዳንድ አገሮች የገና ቀን ወይንም ዲሴንበር 25 ሲያከብሩት ሌሎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት ደግሞ ከዲሴንበር 25 በኋላ ያከብሩታል።
የገና በዓል አከባበር ስነ ስርዓት እንደየ አገራቱ ሊለያይ ይችላል። በብዙ አገሮች ግን የገና ዛፍን በማዘጋጀትና እላዩ ላይ አብረቅራቂ መብራት፣ ኳሶች፣ የገና ካልሲዎች እንዲሁም የተለያዩ ስጦታዎችን በማስቀመጥ የሚያከብሩት ሲሆን፣ አብያተ ክርስቲያናት እና ቤተሰቦችም የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የሚያሳዩ የትውልድ ቀን ትዕይንቶችን ያዘጋጃሉ። ቤተሰቦችም የገና ካርዶችን ይላላካሉ፣ ስጦታዎችን ይለዋወጣሉ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ወይንም ከዘመዶቻቸው ጋር በጋራ በመሆን በደስታ ያሳልፉታል።
በዓለም ዙሪያ አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገራት የገናን በዓል በይፋ የሕዝብ በዓል አድርገው በመቀበል ያከብሩታል። ሌሎች አንዳንድ አገራት ደግሞ እንደ ባህላዊ ክስተት ብቻ እውቅናን በመስጠት በዓሉን እንደ መደበኛ የሕዝብ በዓል የማይቀበሉትም አሉ።
የዓለም አቀፉ የስነ ሕዝብ ግምገማ ተቋምም እነዚህን የገናን በዓል በይፋ አገራዊ በዓል አድርገው የማያከብሩ አገራትን ዝርዝር በቅርቡ ያወጣ ሲሆን የሕዝብ ቁጥር ብዛታቸውን መሰረት በማድረግ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ ተካተዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 114 ጥር 1 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com