ልባዊ የገና ስጦታ

Views: 150

በሳለፍነው ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 28 የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል፤ “ስጦታችሁ ለልባችን በሚል መሪ” ቃል ባዘጋጀው የአንድ ሳምንት የንቅናቄ መረሃ ግብር መዝጊያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
የልብ ሕሙማን ማዕከል የሚሠራው ሥራ የሕጻናትን ሕይወት የመታደግ ሥራ ከመሆኑ አንፃር የሕጻናትና እና ወጣቶች ሚንስቴር ከሜድሮክ ኢትዮጵያ ያገኘውን የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የገና በዓልን በማስመልከት ድጋፍ ማበርከታቸውን ሚንስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ ገልፀዋል።
የሕጻናትን ጉዳይ ሥራዬ ብሎ እንደሚመራ ተቋም በቀጣይም ማዕከሉ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ከተለያዩ ባለሀብቶችና አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ለመደገፍ ቃል እንገነባለን ብለዋል።
በዕለቱም በማዕከሉ የሕክምና ክትትል ላይ የሚገኙ ህጻናትና ወላጆች እንዲሁም ማዕከሉ የሚሰጣቸውን አገልግሎች በተመለከት ጉብኝት ተካሄዷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 114 ጥር 1 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com