የአሰብ መዳረሻ የሆነው የሜሎዶኒ መገንጠያ – ማንዳ- ቡሬ የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጀመረ

Views: 59

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የአሰብ መዳረሻ የሆነው የሜሎዶኒ መገንጠያ – ማንዳ- ቡሬ የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጀመረ።
78 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የዲቾቶ – ጋላፊ መገንጠያ- በለሆ የኮንክሪት መንገድም ግንባታው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል።
የመንገድ ማስጀመሪያውንና ምርቃቱን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የመንገዶች ባለስልጣን ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ በተገኙበት ነው።
የመንገዱ መገንባት ከወደብ መዳረሻነት ባለፈ ከኤርትራ ጋር ለሚኖረው የንግድና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመጠናከር ረገድ አይነተኛ ሚና አለው ተብሏል።
መንገዱ አዲሱን የታጁራ ወደብ ለመጠቀም የሚያስችል ሲሆን በነባሩ ጅቡቲ ወደብ ይፈጠር የነበረውን የትራንስፖርት ጫና እንደሚያቃልል ተነግሯል። መንገዱን ለመገንባት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታልም ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለጂቡቲና ኤርትራ ወደቦች አማካኝ ቦታ የተገነባው በአፋር ክልል ‘የዲቾቶ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቆያ ተርሚናል’ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ አስታውቀዋል።በአፋር ክልል በ63 ሚሊየን ብር የተገነባው የዲቾቶ ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎች ተርሚናል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተመርቋል። በአፋር ክልል ዲቾቶ በሚባል አካባቢ ጋላፊ ከተማ አቅራቢያ ላይ የተገነባው የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቆያ ተርሚናል ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በወቅቱ እንዳሉት፤ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች መገንባቱ የኮሮናቫይረስን ከመከላከል ባሻገር አይነተ ብዙ ምጣኔ ሀብታዊ አበረክቶት ይኖረዋል።
ከ750 እስከ 800 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችለው የዲቾቶ ተርሚናል ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ክፍሎችና የኮሮናቫይረስ ምርምራ አገልግሎት መስጫዎች እንዳሉት ገልጸዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 116 ጥር 15 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com