ኤምሬትስ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን በረራ ዕለታዊ አድርጎታል

Views: 192

የኤምሬትስ አየር መንገድ ከ ጥር 27 2013 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ በሳምንት አምስት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ በማሳደግ በየዕለቱ በረራ ለማድግ መወሰኑን አስታወቀ። የዕለታዊ መርሃግብር ለደንበኞች የተሻሉ የጉዞ አማራጮችን ከማቅረብ በተጨማሪም ወደ ዱባይ እና ወደ ሌሎችም የአለማችን ክፍሎች እየሰፉ የመጡ የኤምሬትስ ዓለም አቀፍዊ የአገልግሎት መረብ ተጠቃሚነትን እድል ይሰጣል ተብሏል፡፡

ከአዲስ አበባ የሚነሱና ወደ ከተማዋ ለሚመጡ በረራዎች ኤምሬትስ የቦይንግ 777-300ER አውሮፕላን የሚጠቀሙ ሲሆን የEK723 በረራ ከዱባይ ከጠዋቱ 03፡25 ሰዓት ተነስቶ በ6፡40 ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እነደሚደርስ እና የመልስ በረራው EK 724 ከቀኑ 9፡ 05 ሰዓት ከአዲስ አበባ በመነሳት ዱባይ ከምሽቱ 2፡15 ሰዓት አንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡

ኤምሬትስ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በሂደት መጠነ ሰፊ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በስድስት አህጉራት ወደ 114 መዳረሻዎች በረራ ያደርጋል፡፡
ባለፈው ሃምሌ ወር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የቱሪዝም እንቅስቃሴዋን የጀመረችው ዱባይ በተለይም በክረምቱ ወቅት በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ ከሆኑት መዳረሻዎች አንዷ መሆንዋ የተነሳ ለአለም አቀፍ የንግድ እና የመዝናኛ ጎብኝዎች ክፍት መሆኗም ተገልጿል ፡፡ በተጨማሪም የእንግዶችን ጤናን እና ደህንነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች እና በተወሰዱ ውጤታማ እርምጃዎች የዓለም የጉዞ እና ቱሪዝም ካውንስል (WTTC) ደህንነቱ የተጠበቀ የጉዞ ማህተም በማግኘት በዓለም የመጀመሪያ ከሆኑት ከተሞች አንዷ ነች ፡፡

ተለዋዋጭነት እና ዋስትና-የኤምሬትስ ደንበኞቻቸው ጉዞዎቻቸውን ለማቀድ ምቹ አማራጭ እና መተማመንን እንደሚሰጣቸው እና ሰኔ 23 /2013 በፊት የኤምሬትስ ትኬት የሚገዙ ደንበኞች የጉዞ ዕቅዳቸው ቢለወጥ ያለ ተጨማሪ ክፍያ የጉዞ ቀናቸውን ለመቀየር ወይም የቲኬት ዋጋቸውን ለ 2 ዓመታት የማራዘም አማራጮች አንዳላቸው ተግልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com