የ25 ቢሊዮን ብር ፈገግታ

Views: 408

ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኀሙስ፣ ጥር 13/2013 የድርጅቱን የግማሽ ዓመት ሪፖርት በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኀን በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።
ድርጅቱ በ2010 (እ.አ.አ) ከኢትዮጲያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን፤ ኢትዮ ቴሌኮም ተብሎ እንደ አዲስ ሲቋቋም ካፒታሉ 40 ቢሊዮን ብር እንደነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስታውሰው፤ ባለፈው ሳምንት በሚኒስትሮች ም/ቤት በጸደቀው ማሻሻያ ደንብ ወደ 400 ቢሊዮን ብር ማደጉን አስታውቀዋል፡፡
በተሻሻለው ደንብ መሠረት በ‹‹ሞባይል መኒ›› እና ሌሎች ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች እንዲሰማራ፤ ተያያዥ ሥራዎችን የሚሠሩ ኩባንያዎች እንዲመሰርት እና በአገር ውስጥና በውጭ ባሉ ኩባንያዎች ላይ አክሲዮን መግዛት እንዲችል እንደተፈቀደለት አስረድተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም የኮቪድ-19 እና በየቦታው የተፈጠሩ ግጭቶችን ያሳደሩትን ተጽእኖ ተቋቁሞ 25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገባቱን ይህም ከእቅዱን 95 በመቶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 116 ጥር 15 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com