የእለት ዜና

ጥር እና ሠርግ

እሷስ ሎሚ ናት የአባይዳር
እኔስ መሸብኝ የት ልደር
ሎሚ ናት የአባይ ዳር
የኛማ ሙሽራ የእኛማ ሙሽራ
እጹብ ድንቅ ስራ
በሆታ በእልልታ እንቀበላቸው
ሙሽሪት ሙሽራው ዛሬ ነው ቀናቸው

ይህ ሙዚቃ የታደሰ ዓለሙ ነው። ይህን ሙዚቃ ጨምሮ ስለ ሠርግ የተዘፈኑ ሙዚቃዎች ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ የሚደመጡበት ወቅት ላይ እንገኛለን -ወርሃ ጥር ላይ ።በአገራችን በተለያዩ ወራቶች ላይ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል ነገር ግን እንደ ጥር ወር ብዙ ጥንዶች በአንድ ጣራ ሥር ለማኖር የጋብቻ ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ተመራጭ ወር አለ ብሎ ደፍሮ ለመናገርም አዳጋች ይመስላል። ለዚህም አይደል? ጥር ‹የሙሽሮች ወር› ተብሎ ስያሜ የተሰጠው።

ሠርግ በአገራችን እንደ የአካባቢ ባህልና እምነትን መሠረት አድርጎ የሚፈጸም ሥርዓት እንሆነ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ዋና ዋና በሚባሉ ከተሞች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የሠርግ ሥነ ሥርቶችም ከጊዜ እና ከወቅቱ ጋር አብሮ እየተቀየረ እንደሆነ በስፋት መመልከት ይቻላል።

ሔርሞን ተከስተ ትባላለች ።ጥር 08 ቀን ነበር ከአሁኑ ባለቤቷ ከቀድሞ ፍቅረኛዋ ሙላለም መንግስቱ ጋር የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን የፈጸሙት። ሔርሞን ለአዲስ ማለዳ ስትናገር ‹‹ሠርጋችን ያው በጣም ቀለል ባለ መንገድ ነበር የፈጸምነው።›› አክላም ስለ ሠርጋቸው ሥነ ሥርዓት ይህንን ብላለች ‹‹ጠዋት ላይ ሽምግልና ተላከ ከሠዓት ደግሞ ባለቤቴ መጥቶ ቤተሰብም መርቆን ጨፍረን ደስ በሚል እና ቀለል ባለ መንገድ ነው የተጋባነው›› ስትል ከወጪም አንጻር ብዙ ያልወጣበት እንደሆነም ነው ያስረዳቸው።

‹‹ይህ ከመሆኑ በፊት ግን በጓደኞቼ ‹bridal shower› የቅድ ሠርግ ፕሮግራም አዘጋጅተውልኝ ሰርፕራይዝ አድርገውኛል›› ስትልም አስታውሳለች።
ደጀኔ ሞገስ እና ወርቅነሽ ጌታሁን ኑሯቸው በአዲስ አበባ ካደረጉ ብዙ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ከትውውቅ የዘለለው ግንኙነታቸውም አድጎ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ አንድ ብለው የጋራ ኑሯቸውን ጀምረዋል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ወደ ወርቅነሽ ሽምግለና የተላከው በመስከረም ወር እንደነበር ሙሽራው ሞገስ ያስታውሳል። የሙሽሪት ቤተሰብም ልጃቸውን ለሞገስ ለመስጠት ከተስማሙ በኋላ ‹መልስ› ብለው ለጥር 23 ጠርተዋቸዋል። መልስ ተብለው ይጠሩ እንጂ ነገሩ ከሠርግ ምንም የሚለየው ነገር የለም ይላል ሞገስ።

ወርቅነሽ የተወለደቸው ወደ ቡታጅራ አካቢ ሲሆን የዛ አካቢን ባህል መሠረት በማድረግ ሞገስ ሽምግልና ሲልክ ለቤተሰቦቿ ማር፣ የተለያዩ አልባሳት እና ውስኪም ልኳል ። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ገና ብዙ ወጪ እንደሚጠብቃቸው ይናገራል። ቤተሰቦቻቸውን ጠርተው ለማስተዋወቅ ያሰቡት ሞገስ እና ወርቅነሽ ሃሳባቸው ተቀባይነት ባለማግኘቱ የግድ ወደ ቤተሰቦቻቸው አካባቢ ማቅናት ግድም ሆኖባቸዋል። በዚህም ምክንያት ገና ብዙ ወጪ እንደሚጠብቃቸው ሲናገርም የትራንስፖርት፣ለእናት እና አባት እንዲሁም ለቅርብ ቤተሰብ የሚሰጥ አልባሳት፣ ለሠርግ የሚደገስበት ብር ለቤተሰቦቻቸው መስጠት፣ሙሽራው እና ሙሽሪት ከሚለብሱት ልብስ ውጪ ጥቃቅን የሞባ ነገሮች ግን ተጨማሪ ወጪዎች እንደሚጠበቃቸው በመግለጽ ይህንንም የምናደርገው ቤተሰቦቻችንን ለማስደሰት እና የእነሱን ምርቃት ለመቀበል እንደሆነም የሚያስረዳው ሞገስ ነው።

ነቢል አልመድ ይባላል የ‹ሀይሎጋ› ዌዲንግ ፕላነርስ (የሠርግ ዕቅድ አውጪ) ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ነው። ነቢል እንደሚናገረው የሠርድ ዕቅድ ማውጣት ሥራ ሠርጉን ከማቀድ እንስቶ የቅድመ ሠርግ ላይም ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ለአዲስ ማለዳ ይናገራል። ሥራው ሙሽሮች (ተጋቢዎች) እና ቤተሰቦቻቸው ሠርጋቸውን እንዴት አድርገው ቢያከናውኑ የተሻለ ሊያደርጉት እንደሚችሉ ፤ እንዲሁም ድካማቸውን፣ ገንዘባቸውን ከመቆጠብ ባሻገርም ፍላጎታቸውንም ባሟላ መልኩ ከሠርግ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን እንደሚሰሩም ገልጿል።

አጠቃላይ የሠርጉን ቀን ቀማቀድ ጅሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ ለውን ፕሮግራም ያካተተ ነው። ብዙ ሥገኞችም ይሁኑ ቤተሰቦች ሲቸረጉ ስናይ ወደዘህ ስራ እንድነገባ አስገድዶናል የሚለው ነቢል ለብዙዎች አሁን ላይ ምፍትሐየ እየሆኑ እንደሆነ የሚጠቅሰው በተለይም ይላል ውጭ አገር ያሉ ተጋቢዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሲስቡ ጉዳያውን የሚከታተል ላይኖር ይችላል እኛም አነሱን ወክለን በደንበ|ኞቻን ፍላት መሠረት የተለያዩ ሥራዎችን እንሠራለን ሲል ይናገራል።

‹‹ከአዳራሽ መረጣ ጨምሮ ቪዲዮ እና ፎቶግራፍ፣ኬክ ማዘጋጀት፣ አበባዎ፣ መኪናዎች እና ለሰርጉ የሚስያፈልጉ ግብዓቶችን በማዘጋጀትም ከሙስሮች ጋር እበረናቸው በመሆን ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት እንሰራለን›› ሲልም ይናገራል

የተለያዩ ሠርጎች ላይ የተዛበውን የሚናገረው ባለሙያው ‹‹የሠርግ ዕቅድ አውጪ ያለመኖሩ ትልቁ እንደ ችግር የሚታየው ድካሙ ሲሆን በተለይም ዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ሠዎች ቤታቸው ውስጥ ደክመው ካልሰሩ የደገሱ አይመስላቸውም አሁን ላይ ያሉ ልጆች ግን ይህን ባለመፈለጋቸው ምክንያት የተወሰነ መሻሻል ይታይበታል›› ይላል።

ባሙያዎቹ መኖራቸው ስላቀቀሉት ነገር የሚገልጸው ነቢል ፤ የተጋነነ ዋጋ አስቀርቷል። ለምሳሌ በዲኮር ወይም መስጌጥ ላይ ሊሆን ይችላል ሌላው ደግሞ በፎቶ እና ቪዲዮ ሥራም የዋጋ ግነት የሚያጋጥም በመኖሩ ይህንም የሚፈታ ነው።

ሌላው መዘንጋት የሌለበት ነገር የሠርግ ሰዓት አጠቃቀምንም እንደሆነ በምሳሌነት ያነሳው ቢላል በእኛ አገር ሙሽራ በጊዜ አለመምጣቱ እንደ ባህል እየታየ መምጣቱ ተከልተሎ የሠርጉ ሥነስርዓት ሰዓትን ጠብቆ እንዲኬድም ያግዛል ብሏል።

ቢላል ብዙ ሰዎች ይህንን ነገር እንዲገነዘቡለት ይፈልጋል።‹‹እኛ አገር በዙ ሠው ለአገልግሎት (Service) የሚከፈል አይመስለውም ። ሥራውንም እንደ ፕሮቶኮል (በአንድ አስተባባሪ ግለሰብ) ብቻ የሚሰራ አድርጎ በማሰብ ለዚህማ ጓደኛዬ አለ በማለት ብዙ ሰዎች ይቀርብኝ ይላሉ።›› ሲል የሚያረዳው ነቢል ቀጠል አድጎም ነገሩን በምሳሌ ሲያስራድም ‹‹ለምሰሌ አንድ ሠርግ የሚደረገው በግንቦት ወር ሊሆን ይችላል። የሠርግ ዝጅግቱ የሚጀመረው ደግሞ ከመስከረም ወር ጀምሮ ሊሆን ይችላል።
ለዚህም ሲባል ከሙሽሮች ጋር አብሮ ዕቃ መግዛት ይኖራል። እንደነዚህ ዓይነቶች ነገሮች ላይ ብዙ ወጪዎች አሉት። እኛ ቢሮ ተከራይተን ነው የምንሰራው። የሠራተኞቻችንም ወጪ አለብን። ለእኔ እንደውም በጣም ዝቅተኛ ክፍያ ነው እየተከፈለን ነው ያለው ብዬ ነው የማስበው ።›› በማትም ነገሩን ያብራራል።
ለዌዲንግ ፕላነር በብዛት የሚከፈለው ክፍያም ከ10 እስከ 50 ሺ ይሁን እንጂ ብዙ የሚስገኘው ጥቅም እንዳለ የሚገልጸው ነቢል ፤ ደጋሾችን ብዙ ከመክሰር መታደግ መቻል በራሱ ትልቅ ሥራ እንደሆነም ነው የሚናገረው።

‹‹አላስፈላጊ ወጪን፤ አላስፈላጊ ድካምም እንዲቀንስ ለረዳ እና ለገዘ ባለሙያ ለሆነ ቡድን ቢከፈል ጥቅሙ እንጂ ኪሳራው አይታየንም›› በማለት ሙያውን አስፈላጊነት እና በዚ ሰዎች ዋጋቸው ውድነው ከሚለው ሃሳብ ጋር አያይዞ ነው የገለጸው።ከዚህ በተጫመረም አንድ ሠው በበጀተው በጀት አልያም እንደ አቅሙ ሥራውን ማሰራት የሚችል አጋጣሚ እንዳለውም ይጠቅሳል።

የኮቨድ 19 ወረርሽ ወደ አገራችን መግባቱ ተከልተሎም ‹‹ኮቪድ ከእቅድ ውጭ ነው ያደረገን። ይህ ይመጣል ብለን ባለማሰባችንም ነገሮችን ለመቆጣጠር ከባድ ሆኖብን ነበር ። ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጭ የሆነበት እና ተጠባባቂ እቅድ (ፕላን ቢ) እንኳን ያልነበረን ጊዜ ላይ በመሆኑ አሁን ላይ ትምህርት አግኝተንበታል›› ሲልም ያስረዳል የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አሁንም መላ ያልተገኘለት በመሆኑ ዳግም ቢከሰት እንከረርን እንዴት ነው መስራት የምንችለው የሚለውን ነገር እንደናስብ እረድቶል የሚለው ነቢል በአሁን ወቅትም ከደንበኞቻችን ጋር እየተናበብ እየሠራን እንገኛለን ችግሩ ይበልጥ የሚጎዳው እዚህ ዘርፍ ላይ ላለን ሰዎች በመሆኑ ጥንቃቄ ከራሳችን ጀምሮ ማድረግ ያስፍልጋል መንግስትም ቢሆን ጥርት ያለ መረጃ መስጠት እና መመሪው በብዙዎች ዘንድ እንዲዳረስ ግንዛቤ መስጠት እንደሚያስፍል መልዕክቱንም አስተላልፏል።

እንደ አሁኑ የሰርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ብዚ ሠዎች እየተዘጋጁ ከመሆናቸው በፊት አዲስ ማለዳም በቅጽ 2 ቁጥር 5 ‹‹ኮቪድ የቀየረው የሠርግ ሥነ ሥርዓት›› የተሰኘ ርዕስ ያለው እትመቷ ላይ ብዙ የሠርግ ሥነ ሥዓቶች በመስክ እንዲሁም በስቱዲዮ ፎቶዎች ላይ መገደባቸውን ባለሙዎችን በማናገር የሠራቸው ዘገባውም የሚታወስ ነው::

ቅጽ 2 ቁጥር 117 ጥር 22 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com