10ቱ በዩኔስኮ በርካታ ቅርሶችን ያስመዘገቡ አገራት

Views: 211

ምንጭ፡-ምንጭ፤ ዩኔስኮ 2019/2020

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ትኩረት ያሻቸዋል፤ ድንቅ ናቸውና እንክብካቤ ይደረግላቸው፣ ይጠበቁ ደግሞም ጎብኚዎችም ይጎብኗቸው ሲል ቅርሶችን ይመዘግባል። በዚህ መሠረትም የዓለም አገራት በተፈጥሮ የታደሉትንም ሆነ በባህል የተቸሩትን ቅርስ ያስመዘግባሉ።
በዚህ መሠረት ጣልያንና ቻይና በዐስርቱ ዝርዝር እያንዳንዳቸው 55 ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆነዋል’ ይህም በቱሪዝም ዘርፍ የሚያገኙትን ገቢ ቁጥር ሳይጠራ መገመት የሚያስችል ነው።
በብዙ ሀብት የታደለችው አገራችን ኢትዮጵያ ቁጥር ስፍር የሌለው የሚዳሰስም ሆነ የማይዳሰስ እንዲሁም መልክዓ ምድራዊ ሀብት አላት። ሆኖም ዩኔስኮ ተመዝግቦ የሚገኘው ቅርስ ብዛት ከ13 የላቀ እንዳይደለ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል።

ቅጽ 2 ቁጥር 118 ጥር 29 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com