ጋዜጠኛ ሉሲ ካሳ በታጠቁ ኃይሎች ጥቃት እንደደረሰባት ታወቀ

Views: 533

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን እንዳስታወቀው ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ዘገባዎችን በመስራት የምትታወቀው ሉሲ ካሳ በየካቲት 3/2013 ምሽት የሲቪል ልብስ የለበሱ እና የታጠቁ ሰዎች ወደ ቤቷ በኃይል በመግባት ጥቃት እንዳደረሱባት እና እንዳስፈሯት እንዲሁም የግል ንብረቶቿንም እንደወሰዱባት አስታወቀ።

ሉሲ ካሳ ለአልጀዚራ እና ሎስ አንጀለስ ታይምስን ጨምሮ ለሌሎች የውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን ከአዲስ አበባ እንደምትዘግብ የሚታወቅ ሲሆን በተባለው ቀን ምሽት ወደ ቤቷ ዘልቀው የገቡት እና መሳሪያ የታጠቁት ግለሰቦች መሬት ላይ ከጣሏት እና መኖሪያዋንም ከረባበሹ በኋላ ላፕቶፕ ኮምፒውተሯን፣ እና ለዜናዎቿ ግብዓት የሚሆኑ ፎቶዎችን ይዘው እንደሄዱም ታውቋል። ሉሲን ጠቅሶ ቡድኑ እንዳስታወቀው በሚቀጥለው ከባድ ድብደባ እንደሚገጥማት የዛቱባት ሲሆን የሕወሓትን ቡድን እንደምትደግፍ እና የሐሰተኛ መረጃዎችንም ታሰራጫለሽ የሚል ውንጀላም ከግለሰቦቹ ዘንድ እንደተሰነዘረባት ታውቋል። ሉሲ ባለፉት ወራት የፌደራል መንግስቱ ወሰደውን የሕግ ማሰድከበር እርምጃ ተከትሎ በስፋት ዘገባዎችን ስትሰራ መቆየቷም ታውቋል።

ቡድኑ በሉሲ ላይ የደረሰውን ጉዳይም በቀላሉ መመልከት እንደሌለበት እና ችላ እንዳይለውም አጽንኦት ሰጥቷል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com