10 በ2021 በጠቅላላ አገራዊ ሀብት የሚያድጉ ታዳጊ አገራት

Views: 172

ምንጭ፡-የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ጽህፈት ቤት(UN DESA)

የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች መምሪያ መረጃ ትንበያ ከሆነ በተያዘው የፈረነጆቹ 2021 ዓመት በአጠቃላይ አገራዊ ሀብታቸው ያድጋሉ ብሎ በቀዳሚነት ካስቀመጣች አገራት መካከል ጉያና በአንደኝነት ስትቀመጥ ኢትዮጵያ በኹለተኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከኢትዮጵያ በመቀጠል ሴኔጋል፣ ረዋንዳ፣ ብንግላዲሽ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማይናማር፣ ኮትዲቫር፣ ካምቦዲያና ቤኒን በቅደም ተከተል ከሦስተኛ አስከ አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ምስራቅ አፍሪካ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለች ንዑስ ክፍል ሆና የቀጠለች ሲሆን በአገር ውስጥ ፍላጎት እና በመሰረተ ልማት አውታሮች ሕዝባዊ ኢንቬስትሜቶች የተደገፈ ኢኮኖሚያዊ አመለካከቱ ምቹ ሆኖ ቀጥሏል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ በተጨማሪም በቅርቡ በጅቡቲ ፣ በኤርትራ ፣ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ የተፈፀመው የሰላም ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ፣ ንግድንና የንግድ ዕድሎችን ያስከፍታል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com