የምርጫ ቦርድ ላይ ያለን ዋና ቅሬታ ኦነግ ውስጥ በተፈጠረው ጉዳይ ጣልቃ መግባቱ ነው

Views: 28

በቴ ኡርጌሳ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ናቸው።
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ውስጥም ቀላል የማይባል የትግል ዓመታትን አሳልፈዋል።
መጪውን ምርጫ በማስመልከት ድርጅታቸው ኦነግ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ እና የምርጫ ዝግጅት በተመለከተ ከአዲስ ማለዳው ዳዊት አስታጥቄ ቆይታ አድርገዋል።

ምርጫ ቦርድ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተለያዩ ጊዜያት ስብሰባ በመጥራት ውይይቶቸን እያደረገ ነው። እስከ አሁን የነበሩት ስብሰባዎችን አንዴት ገመገሟቸው?
አሁን በቅረቡ ከተደረው ውይይት ብንነሳ፣ እና እንደ ኦነግ የጠበቅነው፣ ምርጫ ቦርድ አሁን አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ገምግሞ ምርጫ ማድረግ ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለውን መልስ የሚሰጥበትን ሁኔታ ያቀርባል፣ ወይም እስከ አሁን በተደጋጋሚ እኛም ሆንን ሌሎች ፓርቲዎች እያቀረብናቸው ባለናቸው ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች ዙሪያ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ጠብቀን ነበር። እሱ ግን አለሆነም ።

አሁን በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎች አሉ፣በእስር ቤት ያሉት ትልልው የፖለቲካ መሪዎች የርሃብ አድማ እስከ ማድረግ ደርሰዋል። አሁን ላይ በጣም ተዳክመው ህይወታቸው አሰጊ ሁኔታ ላይ እንዳለ እናውቃለን።
እነዚህ የሚታወቁ የህብረተሰብ መሪ (figure )ናቸው::የእነዚህ የህብረተሰብ መሪዎች ሞት እና ምን ሊያስከትል የሚችለውን የፖለቲካ ኪሳራ ቀላል አይደለም ። አሁን እየተኬደበት ያለበት መንገድ የሚያዋጣ አይመስለኝም ስለዚህ መንግስት በማን አለብኝነት፣በአንድ ወገን ብቻ በመጣ ግፊት ወደ ምርጫ ለመግባት የቆረጠ ነው የሚመስለው።

አሁን የምርጫ ተወዳዳሪ እጩ ለመቅረብ አራት ቀናት ናቸው የሚቀሩት የካቲት 8 ድረስ ብቻ ነው ማቅረብ የሚቸላው። አራት ቀናት ብቻ እየቀሩት ስለሦስትዮሽ ውይይት ገና እያደረጉ ነው ያሉት በምርጫ ቦርድ በኩል እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች እና ስራዎች አሁን አገሪቷ ያለችበትን ነባሪዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ብለን አንወስድም። አሁን አገሪቷ በሁሉም አቅጣጫ ውጥረት ውስጥ ነው ያለችው።

እንደ ፓርቲም አሁን የኦነግ ዋና ጽ/ቤት ተዘግቶብን ነው ያለው። በመላ አገሪቱም ወደ 103 ቢሮዎች ተዘግተውብናል። አባሎችችን ብዙዎች ታስረዋል።እነዚህ ሁሉ የተደረጉት ደግሞ ያለ ሕግ አግባብ ነው ። ከሕግ የበላይነት መርህ ሁሉ ውጭ ነው። ምክንየቱም አቃቤ ህግ የለቀቃቸው እና ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበታቸው ከ እንዴም እስከ ስድስት ጊዜ እንዲለቀቁ የተፈረደላቸው አናሎቻችንን አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።

እንዲሁም ፍርድ ቤት እንኳን ሳይቀርቡ እንዲሁ በእስር ቤት ታጉረው የተቀመጡ አሉ። እስራቱ አሁንም ቀጥሏል። ማክአኞ እንኳን አንድ ሴት እና አንድ ወንድ አባሎች ኢንተር ኮንቲኔንታል የተዘጋጀ መድረክን ተሳትፈው ሲመለሱ ጠብቀው ከቤታቸው ወስደው አስረዋቸዋል።
እስራቱ በዚህ መልክ ቀጥሎም የአገሪቱ ትርምስም በዚህ መልክ ቀጥሎ ምርጫ ቦርድ ምንም አንዳልተፈጠረ በሚያስመስል ሁኔታ ምርጫ አደርጋለው ብሎ ከኔ በኩል ማድረግ ያለብኝን ስራ አጠናቅቄያለሁ ብሎ ምርጫ ለማድረግ ወስኗል።

ይሄ እንግዲህ ወዴት እንደሚወስደን ቀጥለን የምናየው ነገር ነው። ነገር ግን እንደ ኦነግ ከዚህ በፊትም ብዙ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥተናል፣ አገሪቱ ችግር ውስጥ ናት ብለን ከምርጫ በፊት መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዩች Even የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነትንም ጭምር እንዲፈተሸ እና ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የሚዲያ አካላት ገለልተኝነት መረጋጋጥ ስለሚችልበት እና እንዲሁም ከሁሉም በላይ ሰላም እና መረጋጋት ስልሚሰፍንበት ጉዳይች ቅድሚያ ሰጥተን ብንሰራ ብለን መክረናል።

ለምርጫ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጭምር በነጻነት ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ መደረግ መቻል አለበት።
ለምሳሌ ምርጫ ቦርድ እዚህ አንድ ነገር ይላል፣ወረዳ ስትሄድ ሌላ ነገር ይባላል፣በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው እየሰሩ ያሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ልብ ተንቀሳቅሰው እንዲያደራጁ፣ ቢሮዎችን እንዲከፍቱ ይህንንም ሁኔታ የሚያደናቅፉ ማንኛውንም አካል፣ የመንግሥት አካላትንም ጨምሮ በማያሻም ሁኔታ መናገር እና ሥርዓት ማስያዝ ሲገባው ምርጫ ቦርድም እሽሩሩ ነው የያዘው። ምርጫ ቦርድ በድፍረት እየተናገረ አይደለም፤ የሚቀርቡ ቅሬታዎችንም በጊዜ መፍትሄ እየሰጠ አይደለም።
በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ተገፍቶ የሚገባባትም ምርጫ ወደ ብጥብጥ እና ሁከት ከመክተት ባለፈ ትርጉም ስለማይኖረው ቆም ተብሎ እንዲታብበት እያስጠነቀቅን ነው። አንሰማም ብለው ከሄዱበት እንግዲህ ውጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል።

የምርጫ ቦርድን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ምን ጉዳዮችን ታዘባችሁ ?
አንዱ ቅሬታዎችን የምንቀርባቸውን ቅሬታዎች በቶሎ ተቀብሎ ማስተናገድ አለማቻሉ ነው። ከምንም በላይ ዋናው ቅሬታችን ኦነግ ውስጥ በተፈጠረው ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሞከረበት ሁኔታ በመኖሩ ነው። አሁን ግን እነሱ እራሳቸው አምነው አስተካክለዋል።
በሶሰተኛ ደረጃ የሚጽፉት እና የሚናገሩት ነገር የማዛባት ነገር አለ። ቃለ ጉባዔ አቅርበን እያለ አላየነውም ብለው መልስ ይሰጣሉ።የቀረቡ ሰነዶችን በሚገባ አለማየት አስተውለናል። ይህ በተደጋጋሚ አቅርበናል።

ለምሳሌ ተዘጉብም ያላቸውን ቢሮ በስም ጠርታችሁ የቤት ቁጥር ጠቅሳችሁ አልተናገራችሁም ያላሉ። በሚዲያም ሲቀርቡ እውነተኛውን ጉዳይ አለመናገር ያስተዋላል፤ ኦነግ አባላቶቼ ታሰሩብኝ ይላል እንጂ በስም ጠቅሶ የት አንደታሰሩ አያውቅም ብሎ መናገር የመሳሰሉት ምርጫ ቦርድ ምን ዓላማ አለው የሚያስብል ሥራ እየሰራ እንደሆነ ማሳያ ነው።

እኛ ሁሉንም ገልጸናል ‹‹በኦሮሚያ ፣ ቤንሻንጉል ፣በአማራ ክልል ያሉ በወረዳ እና በከተማ ጭምር ለይተን አሳውቀናል የተዘጉ ቢሮዎችንን አሳውቀናል ። ግን ተናግረን ስናበቃ የዞኑን እና ወረዳውን ጭምር ጠቅሳችሁ ካላተናገራችሁ ይላሉ። ቀበሌ ወርደን ቢሮ ለመክፈት ስንፈልግ ከተማ ላይ ነው ፈቃድ የምንወስደው። በወረዳው ላይ የምናቀርበውን ቅሬታ መፍታት ከፈለገ ከተማ አስተዳደሩን መጠየቅ ይችላል።

እውነቱ ይሄ ሆኖ ሳለ እንደ ማምለጫ አድረገው የቤት ቁጥር አላቀረባችሁም በማለት ሰበብ ይሰጣሉ። ለምሳሌ ሞጆ ፖሊስ ጣቢያ አንድ ነው። የት ምን እንደሆነ ይታወቃል ችግሩን ለመፍታት ካሰቡ እና ቁርጠኝነት ካለቸው ቀላል ነው። ነገር ግን የምርጫ ቦርድ የሞራል ስብእና ሁሉ አጠያያቂ የሚያደርግ ሥራ እተሰራ ነው።

ሌላው የቦርዱ ሰባሳቢ ጭምር የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ የነበሩ እንደሆኑ እናውቃለን ። መሪ የነበሩ ቢሆንም ዛሬ ግን የተቀመጡበት ወንበር የተለየ ስብእና የሞፈልግ መሆን እነዳለበት እናምናለን። በልባቸው የሚደግፉት ፓርቲ ቢኖር እንኳን ቢያንስ ‹በፕሮሲጀር› ገለልተኛ ይሆናል ብለን አናስባለን። ማንም ልሙጥ ወረቀት የለም ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ስብእና አለው ።

ምርጫ ቦርድንም በዚሁ ቁመና ይመራሉ ብለን ጠብቀን ነበር ግን እየሆነ ያለው ሌላ ነው። ‹ኢማጅን› ኦርሚያ ውስጥ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)ን አቤቱታ እያየን ነው ይላል። በእውነት በጣም ያሳፍራል። እውነት ነው ኦሮሚያ ክልል ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩት ክልል ነው። አብንም፣ ኢዜማም ቢሮ ከፍተው ይንቀሳቀሳሉ። እኛ እንደ ኦነግ ቅሬታ አስገብተን ለእኛ ምላሽ ሳይሰጡ፣ ከአንገብጋቢ መጀመር ሲገባ ኦነግ ያቀረበውን አቤቱታ ወደ ጎን ብለው ለአብን ቅሬታ ቅድምያ ሰጥተው እያዩ መሆኑ ላሰበ ሰው፤ የቦርዱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ተግባር ነው ብሎ ቢያስብ ሊፈረድበት አይገባም።

ሌላው ገለልተኝነታቸውን ቅሬታ ውስጥ የሚያስገባው በተለያዩ ዞን እና በወረዳ ስለተዘጉብ ቢሮዎች አቤቱታ ስናቀርብ ፣ የቤት ቁጥር አልተናገራችሁም ብለው ምላሽ ሲነፍጉን ማየታችን ነው። ዋናው መስሪያ ቤት መዘጋቱን እያወቁ ምንም መፍትሄ ያላመጡ እንደዚህ ብለው ሲመልሱ ሰበብ ከመደርደር ያለፈ መልሽ እንደማይዘል ይገባናል።

በተለምዶው ጉለሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያለው ዋናው ቢሮ ከተዘጋ 6 ወራት ተቆጠሩ፣አሁን ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው?
የዋናው ቢሮ ጉዳይ ፣ሊቀመንበሩ በኃይል እንዲወጡ ተደርገው ቢሮችን ከተዘጋ 6 ወራት አለፉ ፣መረጃዎቹ ላይ እንዲቆለፍባች ተደርጎ፣ የቢሮ ኪራይ ውሎች እና ሌሎች ሰነዶች ቼክ ሳይቀር እንዳናቀጣ ተደርጓል።እኛም እራሳችን ገብተን ስራ መስራት አልቻልን። ለምርጫ ሂደት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እንኳን በግል በዲጅታል ያስቀመጥናቸው መረጃዎች ነው እየተጠቀምን ያለነው። እንግዲህ ከዚያን ቀን ጀምሮ ዋናው ቢሮ በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል። ምርጫ ቦርድ ይሄን እያወቀ ታች በዞን እና በወረዳ የተዘጉብንን ቢሮዎች ለማስከፈት ቅሬታ ስናቀርብ ቤት ቁጥር አምጡ ይሉናል ለዚህም መፍትሄ አልሰጠን።

ለእጩ ምዝገባም ቢሆን ፋይሎች እናዳናቀርብ ቢሯችን ተዘግቶብናል። እንደ እነዚህ ያሉ ጉዳዮች በርካታ ችግሮችን አቤት ብንልም፣ ምርጫ ቦርድ ለአቤቱታችን ጆር ዳባ ልበስ በማለት ገለልተኝነቱን አንድናጠይቅ እየስገደደን ያለው።

በእናንተ ግምገማ መንግሥት ምርጫ እንዳንሳተፍ እየገፋን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?
እውነት ነው የብልጽግና መንግሥት ኦነግ ምርጫ አንድንሳተፍ አይፈልግም። መንግሥት ምርጫ እንዳንሳተፍ በግልጽ ቋንቋ አግዶናል ማለት ይቻላል። ቢሮ ከተዘጋ፣ የሚንቀሳቀሱ አባሎቻችንን ካሰረ ምር ቀረ? አሁን ለይስሙላ አሉበት ለማለት ያክል ብቻ አንደዚህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይ አንድንካፈል ያደርጋል አንጂ በተጨባጭ እንድንወዳደር አይፈልግም።

እናም ቢያንስ ያሉንን ቅሬታዎች ለማስተላለፍ እድል ይሰጣል ብለን እንናገራለን እንጂ ነገሮች አስቸጋሪ እየሆኑ ነው።እኛን ለገጽታ ግንባታ ሆን ብለው እያሳተፉን አንደሆነ እናምናለን። ‹ሊትራልይ› መንግሥት ምርጫ እንድንሳተፍ አይፈልግም። በየወረዳው እና ዞን ያሉ የሚገኙ አባላቶቻችንን እያሰረ ምን አይነት ምርጫ ነው? ይሄን ደግሞ ታሪክ ምስክር ይሆነናል።

ምርጫ ቦርድ እንደሚሉት ምዝገባውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ የሚያጠናቅቁ ከሆነ ያሰሩብንን አባላት የሚለቁ ይሆናል። እሱንም በታሪክ የምናየው ይሆናል። ምክንያቱም የተፈለገው ይሄ ምዝገባ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ምርጫ ውስጥ የሚሳተፉ የኦነግ አባላትን እንዳይሳተፉ ማድረግ ነው።

ምርጫ ቦርድም ሆነ ሌሎች ገለልተኛ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ነግ በኔ ብለው እንደዚህ ያለውን ሂደት ካልተቃወሙ፣ ተቀናቃኛቸው እንዲገፋላቸው እንደፈለጉ ብቻ አይተው ቸል የማለታቸው ጉዳዩ እነሱም ጋር አንደሚደርስ አለመገንዘባቸው ያሳያል፣ይህም ያስተዛዝባል። ለሁሉም በየተራ የሚደርስ ተራ እንደሚሆን አልጠራጠርም።

ኦነግ ለሁለት እንዲከፈል የመንግሥት እጅ አለብት ብላችሁ ታባላችሁ?
እሱ የታወቀ ነው ።ቀለብ እየተሰፈረላቸው ለእንቅስቃሴያቸው መኪና ተሰጥቷቸው፣ ቤት እየተሰጣቸው ጭምር ኦነግ እንንዳከም እየተሰራ ነው።እነዚያን ሰዎች ጥበቃ እያደረገላቸው ያለው መንግሥት፣ እኛን ቢሯችንን ዘግቶ ነጻ እንቅስቃሴ እንዳናደርግ ከልክሎናል። እነሱ ግን በመንግሥት ጸጥታ ቢሮ በተሰጠ በጀት ጭምር፣ ሂልተን ሆቴል መግለጫ እንዲሰጡ ከጸጥታ ቢሮ በተጻፈ ወረቀትእንዲስተናገዱ እየተደረገ ነው። ለዚያም እኛ መረጃ አለን አውነቱን ማጣራት ትችላላችሁ።

እንዴ! ጠቅላይ ሚንስትሩ ጭምሮ እኮ ኦነግን አላሻባብብ ከቀጠናው ካጠፋን ብሎ እስከመናገር ተደርሷል
እኮ!. . . እኛ አንድ እና ኹለት ሆነን እንዳንቀሳቀስ የሚያግደው አካል፣ የብልጽግናን አጀንዳ ይዘው እንዲቀሳቀሱ ማድረጉ በራሱ ወንጀል ነው። እነዚሀ ሰዎች እንደዚህ ዓይነት ወንጀል እየሰሩ በፓርቲዎች ሕገ ደንብ መሰረት መቀጣት ሲገባቸው የሌላን ፓርቲ አጀንዳ እያፈጻሙ፣ ሚዲያ ላይ ሁሉ ወጥተው መናገራቸው ከፓርቲ አባልነታቸው መሰረዝ ሲገባቸው ዝም መባሉ ያሳዝናል። ጭራሽ በእየ አዳራሹ ወኪል ናቸው ብለው ይጋበዛሉ።

መንግሥት አሁን በእኛ ላይ እያደረገው ያለው ነገር ከምርጫ 97 በኋላ በቅንጅት እና በኦፌኮ ላይ የሰራው ድራማ ቀጣይ ክፍል ነው። ታስታውስ እንደሆነ ኢፌኮን ከ እነ ፕ/ረ መራራ ነጥቆ ለእነ ቶሎሳ ተስፋዬ ሰጠ፣ የቅንጅት አመራሮችንም እስር ቤት ካጎረ በኃል ቅንጅትን ለአየለ ጫሚሶ ህጋዊ ተወካይ እሱ ነው ብሎ እንዲሰጥ አደረገ። በሁለቱም ፓርቲዎች ላይ የተፈጸመው በእኛ ላይ ተፈጽሟል።

አንደኛ ዋና ዋና የኦነግ አማራሮችን ከሕግ አግባብ ውጪ አስሮ አስቀመቀጧል። ክስ ሳይኖርባቸው አቃቤ ሕግ በነጻ ያሰናበታቸውን ሳይቀር።
ሁለተኛ ቢሯችንን ወርረውታል።በወረሩም ሰዓት ሊቀ መንበሩን ጃል ዳውድን በኃይል አስወጡ ፣ከዚያም እንሰረው አንሰርው በሚለው ጉዳይ ላይ 45 ደቂቃዎችን ከአጠፉ በኃላ በአራት የፖሊስ መኪና አጅበው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ተደረገ።ከቤታቸውም እንዳይወጡ አገቷቸው ።ይሄ ወረራ ነው።

ከዚህም ሌላ 26 የሚደርሱ የዋና ጽህፈት ቤት አባላት በእስር ላይ ይገኛሉ።እንዚህ በተለያዩ እርከኖች ማለትም በሴቶች ፣በወጣቶች፣ በፖለቲካ ጉዳዮች አና በሌሎች ኃለፊነቶች ላይ የሚሰሩ መሪዎች ናቸው የታሰሩብን ።
በአንድ ጊዜ ወረራ ብቻ ሳይሆን ለ 6 ወራት ጊዜ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ዋርድያ ሆነው በእየቀኑ እየጠበቀ ይገኛል።ይሄ በኦፌኮ ላይ የተፈጸመ ነው እስካአሁም እየታገለን ነው፣ ስለዚህ እኛ ላይ ጫና በማብዛት እና በቃን ብለን ጥለን ስንወጣ ፓርቲውን ለእነሱ ለመስጠት እና ኦብኮ እና ቅንጅት ላይ የተሰራውን ድራማ ለመድገም ያሰቡ ይመስላል።

አምስትም ሆነ ስድስት ሰው ከዚያ ወስደው ሌሎችን ደግሞ ከራሳቸው ከብልጽግና ወስደው ምርጫ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ እና በኢህአዴግ አንድ ሲደረግ እንደነበረው የተለመደውን ድራማ ለመስራት ያለሙ ይመስላል፣ ያውም ከበፊቱ በባሰ እና አይን ባወጣ ሁኔታ ሚዲያ እያየው ሕዝብ እየተመለከተው።

ወይ እንደ ድሮው ሥርዓት ሁላችንንም አስሮ ምርጫውን ቢያደርግ አንድ ነገር ነው። በአንድ ጎን አቶ ዳውድ ይንቀሳቀሳሉ ለማስባል ፣ በሌላ በኩል ሌሎችን በር ከፍተው ይለቃሉ። አብዛኛውን የድርጅቱን መዋቅሮች የሚያንቀሳቅሱትን አማራሮች ግን አስረዋል።

በዳውድ ኢብሳ የሞመራው እና በእነ አራርሳ ቢቂላ የሚመራ በሚል ለሁለት መከፈል በአባላቶቻቸሁ እና በደጋፊዎቻችሁ መካከል የፈጠረው ልዩነት እና መከፋፈል የለም?
በፍጹም በአባላቶቻችንም ሆነ በደጋፊዎቻችን መካከል የፈጠረው ልዩነት የለም።አንተም በራስህ መንገድ ማረጋገጥ ትችላለህ። መቶ በመቶ ላረጋግጥልህ እችላለሁ። ድራማው ወዲያውኑ እኮ ነው የታወቀው።
በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ሰዎች ቀድሞውኑ ይጠረጠሩ የነበሩ ናቸው። ነገር ግን ለድርጅቱ እና ለትግሉ አንድነት እና ለህዝቡ ሞራል ብለን ፣ ለእነሱም ስብእና እና ሞራል አይመጥንም ብለን ነው የታገስነው እንጂ የተለያዩ ዓይነት ግንኑኝነት እንዳላቸው ቀደሞውኑ ይሰማ ነበር። ይህንን ደግሞ ከእና ቀድሞ ሕዝቡ ያውቅ ነበር። የፓርቲውን ዓላማ የሚጻረር ሃሳብ በየመድረኩ ሲያቀርቡ ሕዝብ ያውቅ ስለነበር፣ ጉዳዩ ለህዝብ አዲስ አልበነበረም። ለአባላቱም አዲስ አልነበረም ፤ስለዚህ በዚህ ምክንያት የተፈጠረ አዲስ ነገር አልነበረም።
ድርጅቱ ሕግ አለው የአስፈጻሚ አባላት መሰብሰብ የሚችሉ በወር አንዴ ነው። በተለያየ ምክንያት ግን በተለይ ትግል ላይ በነበርነት ሰዓት ግን በደንቡ መሰረት ሊቀመንበሩ አስፈጻሚ ነው ስለሚል በዚያ አካሄድ ነው የሚሰራው።

አሁን ምርጫ ቦርድ ላይ ገብቶ እየተሰራበት ያለው በዚያ ላይ በተቀመጠው ይህ አሰራር ሕግ መሰራት ነው። አሁን ላይ ሊቀመንበሩ እንደልብ እንደይንቀሳቀሱ ሆነዋል። አሁን በርካታ የስራ አስፈጻሚ አባላት ታስሯል። ከዓላማ ውጪ ሶስቱ ክደዋል ፣አንድ ሰው ከእርሳቸው ጋር አለ፣ሌሎች አገር ውጪ ያሉት እንዳሉ አሉ።ሰለዚህ በህጉ መሰርት እንዚህን ሁሉ አስተባብሮ አመራር እየሰጡ ያሉት ሊቀመንበሩ ዳውድ ኢብሳ ናቸው።

በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይም ድርጅቱን ይወክላሉ፣አመራር ይመድባሉ። በህዝብ ግኑኝነት ስብሰባዎች ላይ ፋይናንስ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ አመራር ይወክላሉ። የኦፊሰርነትንም ምደባም ቢሆን ድሮም የሚመድበው ሊቀመንበሩ ነው። እንኳን ይሄን የስራ አስፈጻሚዎችን የስራ ድርሻ የሚወስነው ሊቀመንበሩ ነው።

ልክ ጠቅላይ ሚንስትሩ ምንስትሮችን እንደሚመድበው ሁሉ ፣ሊቀመንበሩ የፈለገውን ሰው ነው የሚመድበው። በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ያሉ ሰዎችን መድቦ የሚያሳውቀው ሊቀመንበሩ ነው። ይሄ ድሮም ያለ አሰራር ነው።
ስለዚህ አሁንም በእዚያ ሥልጣናቸው ድርጅቱን እየመሩ ነው ድርጊቱ ‹ኢንታክት ›ነው። አንድም የኦነግ አባል የትኛውም ወረዳ ላይ አልተከፋፈለም።

ስለዚህ በዳውድ ኢብሳ እና በእነ አራርሳ ቢቂላ መካካል የተፈጠው ልዩነትን አንጃ ሊባል ይችላል? ወይስ ምን ተብሎ ነው የሚነሳው?
የእነ አራርሳ ቢቂላን ነገር አንጃ ብሎ መጥራት አይቻልም ። ምክንያቱም አንጃ ብንል እንዳንል በስብሰባ ሃሳብ አቅርቦ ፣ከርክር አካሂዶ ፣በተናጠልም ይሁን በጋራ እራስን አደራጅቶ የሃሳብ ልዩነት ተነስቶ ያንን ሲያራምድ አንጃ ልንል እንችላለን።የሆነው ግን ከድርጅቱ ህገ-ደንብ ውጪ፣ሌሎች ያልተካፈሉበት እራሳቸው ብቻ የተካፈሉበት ስብሰባ አደረገው ሊቀመንበሩን አውርደናል ፣እኛ ሥራ አስፈጻሚ ነን፣ ይሄን ውሳኔ ወስነናል አሉ።

ሥራ አስፈጻሚ ሲሰበሰብ ደንብ አለሁ። አስቸኳይ ስብሰባ እንኳን ማድረግ ካስፈለገ 1/3 አባላት ማሟላት ያገባቸዋል፣ከዚያም ሊቀመንበሩ በተገኙበት ግምገማ ተደርጎ ነው የመወሰነው። አሁን ግን ሊቀመንበሩ በፖሊስ ከቤታቸው እንዳይወጡ ከተደረገ በኃላ ፣ሌሎች አመራሮችም በታገቱበት ሁኔታ ከማህበሩ ህገ ደንብ ውጪ በመንግሥት ድጋፍ የመንግሥትን ሚዲያ ጠርተህ ስብሰባ አድርገን ሊቀ መንበር መርጠል ብሎ ነገር ከድርጅቱ ማእቀፍ ወጪ ነው።

ሂደቱን በሥራ አስፈጻሚ ላይ አምጥተው አላቀረቡም፣በማእቀፉም መዳኘት አልፈለጉም ።ከማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባም ሆነ በስነ-ስርዓት እና ቁጥጥር ኮሚቴ አጥንቶ ባቀረበው ሃሳብም ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም። ስለዚህ አንጃ ሳይሆን አፈንጋጭ ነው የሚባሉት።

ታዲያ እናንተ አፈንጋጭ ብላችሁ ካላችኋቸው አባላት ጋር በተያያዘ ከምርጫ ቦርድ ላይ ያላችሁ ቅሬታ ምንድነው?
የእኛ ክርክር ምርጫ ቦርድ እንደዚህ ያለውን ያፈነገጠውን ቡድን አስተናግዶ እነሱን እሹሩሩ ማለቱ ላይ ነው። የድርጅቱን ሕገ ደንብ አለማክበርም ነው ። ‹ፕሪንስፕል ኦፍ ኤግዞሽን› የሚባል ነገር አለ። ለምሳሌ ከባላዳራስ የተጠየቀውን ጥያቄ ብናይ የምትሰጡንን ውሳኔ በጽሁፍ አድርጉልን ሄደን ፍርድ ቤት አንድንጠይቅ አሉ። ይሄ ምን ያሳያል በምርጫ ቦርድ ‹ኡክዞስት› ማድረግን ነው። ለብዙ ጉዳዩች መፍትሄ እየሰጠ ስለአይደለ ነው።

በአሁኑ ወቅት የውጪ ግንኙነቱን እና ሌሎች ሥራዎችን የሚሰራው ማነው ?
ማህተሙ ያለው ‹ኦፉሺያል› ንኙነቶች የሚካሄዱት፣ኦፊሺያል የማህበራዊ ትስሰር ገጹ ያለው፣የድረርጅክርክር አንስተቱ ልሳን የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ልሳን የሚባለው ጭምር ሁሉን ሥራዎች እያከናወነ ያለው በዳውድ ኢብሳ በኩል ነው። ለዚህ ነው ምርጫ ቦርድን የምንወቅሰው።
ያው ግን ይሄንን መጨረሻ ላይም ቢሆንም አስተካክሏል። ባለፈው ሳምንት ጉዳዩን በህገ ደንባችሁ መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ ፍቱት ብሎ እኮ ውሳኔ ሰጥቷል። እኛ እኮ አስቀድመን ስንል የነበረው ይሄንኑ ነው።
እዚህ ጋር ግን ምርጫ ቦርድ ያወጣውን መግለጫ እንኳን ብንመለከት አዛብተው ነው ያወጡት። ለእና ደብዳቤ ሲጽፉ ግን ስመምግባር ባለው ሁኔታ የገለጹት ይሄን ይሄን ነገር ከሰማን ቀን ጀምሮ ጉዳዩን ለመፍታት ጥረት አድርገናል። በዚህም ጥረታችን ላይ ኦነግ ጣልቃ ገብነት ነው ብሎ አምርሮ ተቃወመ።

ቦርዱም ሰብስቦ ሊያናግር አስቦ ሁለቱን ወገኖች ሲጠራ ይሄም የቦርዱ ኃለፊነት አይደለም ብሎ አምርሮ ተቃወመ። ስለዚህ እኛ ይሄንንም ያደረግነው ለማግባባት ስንል ስለሆነ ይሄ ማለት “ህጋዊ ሆነን አይደለም” ማለታቸው ነው፣(ማይንድ ዩ) እኛ ለህግ ነው እነሱ ደግሞ ለማግባባት፣ይህ ቀድሞውኑ ‹ማንዴታችሁ› አይደለም።

ዋናው ቢሮ ተዘግቶ እያለ ፣ እና ቢሮ ማከፈት ማስከፈት ሲቀድም ኑ እና እኔ ቢሮ ልሰብስብ ማለት፣ጣልቃ ገብነት ነው። ቀነቀ እና ሰዓት ቆጥሮ መጥራት የሊቀመንበር ስራ አንጂ የሌላ አካል አይደለም እያልን ስንሟገት ከርመን ትክክል እነዳለጆኑ ስለገባቸው ነው ቦርዱ ችግሩን ለመፍታት ጥረት አድርገናል፣ ከዚህ በኋላ በራሳችሁ ሕገ ደንብ ፍቱ ብሎ ለስለስ ባለ ቋንቋን የተናገሩት ።

በሌላ በኩል ድርጅቱ አመራር የለውም አባላት ተነስተው ጉባኤ ማድረግ አለባቸው ይልሉ። ይሄ ነው አንዱ ገለልተኝነታቸውን እንድንጠረጥር የሚደርገን። እኛ ኦፊሻል ተፈርሞ የተሰጠን ነው ብለን ዝም ብለናል። በዚህ በኩል ግን ፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አሉባልታ፣ የአንድ ወገን ‹ሪሂቶሪክ› በሚመስል ሁኔታ የሞጽፉት።አንደዛ የሚጽፉ እነሱ ውስጥ የተሰገሰጉ፣ገለልተኛ ያልሆኑ የኦነግ መፈራረስ የሚፈልጉ፣የኦነግን ገጽታ ማበላሸት የሚፈልጉ አሉ። አነግን ኢንታክት እንደሆነ ያውቁታል፣ስለሚያውቁት ነው ዛሬም የሚጋብዙን። ድርጅቱ አንድ መስመር ላይ ኢንታክት አንደሆነ ያውቁታል።

አሥር ሺህ ፊርማ ሲባል እኮ እኛ ነን ፊርማዎቹን ሰብስበን በየወረዳው ያለውን መረጃ አጠናቅረን ፋይናላይዝ ያደረግነው።
መንግሥት ኦነግ ለማጥፋት በሚያደርገው ዝስትራቴጂ ውስጥ ምርጫ ቦርድነረ አንደ ማስፈጸሚያ እየተጠቀመ ነው።ቢሯቸን ተዘግቶ፣ሰነዶች ተቆልፎባቸው፣ቼክ ሳየረቀር ተቀልፎብን ለአባሎቻችን የምንከፍለው ገንዘብ ስለሚያስፈልገን ብለን፣ እየሆነ ያለውን በግልጽ እየገለጽንላቸው ቢያንስ አንድ እንኳን መግለጫ አላወጡም ። የድርጅት ሊቀመንበር ከቢሮ ተንጠልጥሎ ከቢሮ ተገፍቶ ሲወጣ እንኳን ምንም አላለም። በተቃራኒው አብን ደግሞ አንዲህ ተባልኩ ብሎ ቅሬታ ሲያስገባ በማግሥቱ መግለጫ ይሰጣል።
እኛ ላይ እየሆነ ያለው በአንድ በኩል ህጋዊ ናችሁ ተብለን እንደንቀሳቀስ ፣በሌላ በኩል ደግሞ ሌላ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይነፋብናል። አንድንሻማቀቅ ቢሮ እንኳን ሚያከራን አንዳናገኝ ለማድረግ አና ሰው ፊት ቀርበን አንዳንናገር ለማድረግ የሚሊተሪ ሰዎች ሳይቀሩ ስለ ኦነግ በግልጽ የሚናገሩባት አገር ኢትዮጵያ ናት።

ለምድነው ይሄ ሁሉ ጫና የሚደረግብን ትላላችሁ?
ያለን የሕዝብ ድጋፍ እና ብቃታችን ነው ጠላታችን የሆነብን። እንድንታደን ያደረገን። ኦነግ ተከፋፍሎ ቢቻል ከምርጫ ገፍቶ ለመውጣት እና ከህግ ውጪ ላሉት ግለሰቦች ፓርቲውን ሰጥቶ ኦነግን ማፍረስ ነው።

ምርጫ የመሳተፋችሁ ጉዳይ ምን ይመስላል?
ኦነግ እና ኦፌኮን እስር ቤት አጉሮ ምርጫ ይደረግ ፣አሁን ነው ጊዜው የሚሉት እኮ ፐሮ-ፌደራሊስት ኃይሎችን አስወግደው አሃዳውያን ብቻ ምርጫ ለማድረግ በማሰባቸው ነው። አሃዳውያን እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩበት መርጫ ነው። አገሩቷን ወደ አሃዳዊ መንገድ ለመውሰድ ያሰቡ ይመስላል።

በቅርቡ ከኦፌኮ ጋር ተደረገ ያተባለው ጥምረት እስከ ውህደት ሊደርስ ያችላል?
መረጃው ስህተት ነው ። የመንግስት ተለጣፊዎች ያስወሩት ወሬ ነው።ነገር ከማንኛውም ፌደራሊስት ኃይሎች ጋር አንድ በሚያደርገን ጉዳዮች ላይ አብረን እንሰራለን የሚል ነገር አለን።

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com