የእለት ዜና

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በረራ በማቋረጡ ምክንያት 147 ሚሊየን ብር በላይ አቷል

የኢትዮጵያ ኤርፖርች ድርጅት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው የህግ ማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ ዘጠኝ በሚሆኑ የበረራ ማዕከሎቹ በረራ በማቆሙ ምክንያት ማግኘት የሚገባውን አንድ መቶ አርባ ሰባት ሚሊየን ስደሰት መቶ አርባ ሺሕ ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ብር ማጣቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባደረገው ምርመራ ማግኘቱን አስታወቀ።

ጥቅምት 24 የጀመረውን የህግ ማስከበር ሂደት ጋር ተያይዞ በረራ ወደ ባህርዳር ፣ ጎንደር፣ አክሱም፣ መቀሌ፣ ሁመራ፣ ኮምቦልቻ ፣ ላሊበላ ፣ ሰመራ እና ሽሬ መቋረጣቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት ከበረራዎች ማግኘት የሚገባውን ገቢ አለማግኘቱን የፌደራል ፖሊስ በመግለጫው አካትቷል።

የህወሀት ቡድን ጥር 24 ከተጀመረው የህግ ማስከበር ሂደት ጋር በተያያዘ ህዳር 5/ 2013 አመት በባህዳር እንዲሁም በጎንደር ኤርፖርቶች ላይ ሮኬት መተኮሱ የሚታወስ ነው። በዚህም የኤርፖርቱ ቦታዎች ላይ ጥቃት መድረሱ ይታወቃል። እንዲሁም በአክሱም ኤርፖርት ላይ መሰረተ ልማት በማውደም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት ሶስት ሚሊየን ሶስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺሕ ሰባት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ማጣቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው የህወሃት ቡድን በፈፀመው ጥፋት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በሚገኙ ታላላቅ መሰረተ ልማቶች ላይ በኢትዮ-ቴሌኮም ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፣ በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿአል።

በዚህ መሰረት በአካባቢው በሚገኙ የኢትዮ-ቴሌኮም መሰረተ-ልማቶች ላይ ባደረሰው ጉዳት ተቋሙ ማግኘት ከሚገባው አንድ ቢሊዮን ሶስት መቶ ሰባ ሚሊየን ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ሺሕ ስድትስ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር በላይ ማጣቱ በምርመራ ተረጋግጧል። በተጨማሪም በተቋሙ ላይ ከ39 ነጥብ ስምንት ቢሊዮን በላይ የተፈፀሙ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፍ መቻሉ ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ በሰሜን በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ-ልማቶች ላይ የህወሃት ቡድን ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ተቋሙ ከሶስት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሚሊየን አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺሕ አምስት መቶ ሃያ አራት ብር በላይ ማጣቱ ተረጋግጧል።
በዚሁ ጥቃት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወልቃይት ፣ በማይጨው ፣ በአላማጣ እና በአሸጎዳ መቀሌ ሰብስቴሽኖች ላይ ውድመት የደረሰ ሲሆን በእነዚህ ንዑስ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት የምርመራ ቡድኑ በገንዘብ መጠን አስልቶ ወደፊት አንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ላይም በደረሰው ጉዳት ከ14 ሚሊዮን ሊትር በላይሰ ነዳጅ ከመቀሌ ነዳጅ ዴፖ በህገ-ወጥ መንገድ ተቀድቶ የተወሰደ ሲሆን ድርጅቱ ማግኘት የሚገባውን ኹለት መቶ ሀምሳ ስምንት ሚሊየን አንድ መቶ ዘጠና ሺሕ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት ብር ማጣቱ በምርመራ ማረጋገጡን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በሌላ በኩል የህወሃት ቡድን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ በሚገኘው የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኛ የሆኑትን የተለያዩ ግለሰቦች በመጠቀም በወቅቱ የትግራይ ክልል መንግስት የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ በነበረው አብርሃም ተከስተ ዶክተር ትእዛዝ ሰጪነት በአንድ ቀን ብቻ በህገ-ወጥ መንገድ ስምንት መቶ ሚሊየን ብር አውጥተው የወሰዱ መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ከዚህ ባንክ የወጣው ገንዘብ የት እንደደረሰ ወደ ፊት ምርመራው ሲጠናቀቅ የሚገለጽ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በአጠቃላይ የህወሃት ቡድን በፈፀመው የሀገር ክህደት ወንጀል በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በሚገኙ ታላላቅ መሰረተ-ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ከአገልግሎት ሊገኝ የሚገባ ኹለት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ዘጠኝ ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ ሰባት ሺሕ ሁለት መቶ ሃያ ብር በላይ ተቋማቱ እንዲያጡ ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com