የ“እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ” ሀገራዊ ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች በይፋ ተጀረ

Views: 96

“የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይቋረጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዬን እጠቀማለሁ” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የ“እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በትምህርት ቤቶች በይፋ ተጀምሯል።
ንቅናቄው ከዛሬ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ይህም የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዳይቋረጥ እና ትምህርት ቤቶች እንዳይዘጉ በትምህርት ቤት ውስጥ እና ከትምህርት ቤት ውጪ ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን በአግባቡ እንዲጠቀሙም በፕሮግራሙ ላይ ተብራርታል::
የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ሐረጓ ማሞ በበኩላቸው በህብረተሰቡ ውስጥ መዘናጋት እየተስተዋለ እና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ በመሆኑ ሁሉም አካል የኮቪድ መከላከያዎችን በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል ብለዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ፣ የጤና ሚኒስቴር፣የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት እንዲሁም የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ፤መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት በዳግማዊ ሚኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት በይፋ አስጀምረውታል።
ከዛሬ ጀምሮም በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ ልምድ ሊሆን እንደሚገባው በፕሮግሩሙ ላይ ተገልጿል። ንቅናቄውን የጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com