በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሕገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ስድስት ሺሕ 600 ካርቶን የምግብ ዘይት ተያዘ

Views: 48

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6ሺህ 600 ካርቶን ፈሳሽ የምግብ ዘይት መያዙን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት አስታወቀ።
መንግስት በድጎማ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሰራም ህገወጦች ባቋራጭ ለመክበር የፍጆታ እቃዎችን በመደበቅና በማከማቸት ነዋሪውን ለችግር እያጋለጡ ይገኛል ብሏል የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት።
የከተማ አስተዳደሩም የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር እያደረገ ባለው ድንገተኛ ፍተሻም በዛሬው እለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6ሺህ 600 ካርቶን (132ሺህ ሊትር) የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ነው ያለው።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ከህብረተሰብና የፀጥታ ሀይሎች ህገወጦችን ለማጋለጥ ያደረጉት ክትትልና ቁጥጥር የሚመሠገን ሲሆን በህገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን የማጋለጡ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነው ሲል አስታውቋል።
ፖሊስም በጉዳዩ ዙሪያ ማስረጃዎችን ሰብስቦ ምርመራ በማድረግ ላይ ሲሆን ህብረተሰቡ በከተማዋ የፍጆታ እቃዎችን ሆን ብለው በመደበቅ እና በማከማቸት ሰውሰራሽ እጥረት በመፍጠር የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 120 የካቲት 13 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com