እየተመራን ያለነው 20 ዓመት በፊት በነበረ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ስርዓት ነው

Views: 109

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለግብርና ምርት እና ምርታነማነት እድገት እስተዋጽዖ ለማድረግ እና ለዘመናዊ እርሻና አግሮ ኢንዱስትሪ መስፋፋት መሰረት የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እና ግብአቶችን ተደራሽ ለማድረግና ኢንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ አገራዊ እድገት ለማፋጠን ተልእኮ ወስዶ በ2008 የተቋቋመ ኮርፖሬሽን ነው።
የአምስተኛ ዓመት ምስረታን በዓሉን እና የኮርፖሬሽኑን የ2013 የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ዳዊት አስታጥቄ ከኮርፖሬሽኑ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ክፍሌ ወልደ ማርያም ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተቋቋመበት ዓላማ እና የ 5 ዓመቱን ጉዞ ምን እንደሚመስል ይንገሩን?
የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲቋቋም አምስት የራሳቸው ህጋዊ ሰውነት የነበራቸው፤ የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣የግብርና ግብዓት ፣የተፈጥሮ ሙጫና ደን ውጤቶች፣ የእርሻ መሳሪያዎች አክሲዮን ማህበር፣ የጎዴ ሜካናይዜሽን በአንድ ላይ በማድረግ የአገሪቱን የእርሻ ግብአቶች እንዲሟላ ታስቦ የተቋቋመ ኮርፖሬሽን ነው።
ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ለአርሶ አደሩ እና ለሰፋፉ እርሻዎች በአንድ ማእከል የእርሻ ግብዓቶችን ለማቅረብና ተደራሽ ለማድረግ፣አንዲሁም የአገሪቱን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ ታስቦ ነው።
ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ታህሣስ 12/2008 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመበትን ተልዕኮውን ከግብ ለማድረስ ከወቅታዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች(Dynamisms) የሚሄዱ በርካታ ተግባራት እየከናወነ ይገኛል።
ኮርፖሬሽኑ ሥራውን የጀመረው በብር 2.440 ቢሊዬን የተፈቀደ ካፒታል እና በብር 610 ሚሊዬን በገንዘብና በዓይነት በተከፈለ ካፒታል ነበረ,ነዚህ ብቻ መቀጠሉ ድርጅቱ የተሰጠውን ግዙፍ ተልእኮ ላማሳካት እንቅፋት የመሆን ጉዳይ ነበር፣ ለመበደርም በቂ ዋስትናም ለማግኘት አይቻልም ።

በመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር አዋጅ 25/1984 የተጣሉ ግዴታዎች አንዱ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በሚያደርጋቸው ሥራ እንቅስቃሴዎች የተፈቀደ ካፒታል በኮርፖሬሽኑ ሁኔታ ብር 1.83 ቢሊዬን ወይም የተፈቀደን ካፒታል 75 መቶኛ ማሟላት ይጠበቅበታል፤ማሟላት ባይቻል የተፈቀደ ካፒታል በተከፈለ ካፒታል መጠን ብቻ ሆኖ እንዲስተካከል ይደረጋል። ይህ ደግሞ ከኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ ግዝፈት እና የገንዘብ መግዛት አቅም ጋር ተያይዞ የምርትና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም የመወዳደር አቅም የሚፈታተን ይሆናል። በዚሀ ግዜ ውስጥ ይህን ማሳካት ችለናል።

ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበት ተክዕኮ ከግብ ከማድረስ አንጻር ምን ስኬታማ ሥራዎች ሰርቷል?
በአምስት ዓመት ውስጥ በመላው አገሪቱ ባሉን 24 ቅርንጫፎች በተጨማሪ፣ በስትራቴጂ ዘመኑ ወደ 31 ቅርንጫፎች ለማደግ እሰራን እንገኛለን። የአገራችን አርሶ እና አርብቶ አደሮች እና በአሁኑ ሰዓት እየቋቋሙ ላሉ ኢንዱስትሪዎች በቂ ግብዓት እንዲያገኙ ፣መነሻ የሆነ ምርጥ ዘር እና እናቀርባለን።

የኮርፖሬሽኑ በመንግሥት የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የስትራቴጂክ አቅጣጫ ማመላከቻ ጥናት በግብርና ትራንስፎርሜን ኤጅንስ(ATA) በማስጠናት ትኩረት ሊደረጉ ይገባል የተባሉ መስኮችን መሠረት ያደረገ ከ2013-2017 የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ ለማሳካት በ2013 በጀት ዓመት ውጤት ተኮር ዕቅድ በማዘጋጀት የስትራቴጅክ ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን ማሳከት የሚችሉ የብር 735.33 ሚሊዬን በላይ ካፒታል የሚጠይቁ ከአስር በላይ የስትራቴጂክ እርምጃዎች(ፕሮጅክቶች) አዋጭነት ጥናት በማድረግ በሚመለከተው አካላት በማፀደቅ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

እነዚህ ፕሮጅክቶችን በማከናወን በቀጣይ አስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ የድርጅቱን ፣በሥራ ግብር፣በንግድ ትርፍ ግብር፣በትርፍ ድርሻ ክፍያ የመንግሥት በጀት ጉድለት ብር 3.01 ቢሊዬን የሚደግፍ እና ምርታማነት በማሳደግና ብክነት በመከላከል አጠቃላይ የሀገሪቱን ምርት ዕደገት የብር 3.36 ቢሊዬን በድምሩ ብር 6.37 ቢሊዬን ጠቀሜታ የሚያስገኝ ፕሮጀክት ተነደፎ በመከናወን ላይ ይገኛል።

የኮርፖሬሽኑ ሥራዎች የልማትና ቢዝነስ ዓላማ ያላቸው ቢሆንም በልማታዊ ተልዕኮ ምክንያት የሚያጋጥሙ ኪሳራ (ወጪዎችን) በመሸፈን በአምስት ዓመታት (2008-2012) ከተገኘ ትርፍ ብር 756.7 ሚሊዬን እና የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ሪፖርት (IFRS) ትግበራ ሙሉ ለማድረግ በተደረገ ዳግም ቋሚ ንብረት ትመና የተገኘ ብር 1.073 ቢሊዬን Revaluation Surplus በድምሩ 1.830 ቢሊዬን የተፈቀደን ካፒታል አስመዝግቧል።

ኮርፖሬሽኑ ከመቋቋሙ በፊት የማዳበሪያ ግዥ ይፈፀም የነበረው ቀጥታ ከአምራቹ ኩባንያ ሳይሆን በወኪሎች ይፈፀም የነበረውን በማስቀረት ግልጽ የዓለም አቀፍ ጨረታ ሥርዓት በመከተል ቀጥታ አምራች ኩባንያዎች ማሳተፍ የሚችል ጨረታ ሥርዓት በመዘረጋት የዋጋ ቅናሽ እንዲገኝ ተደርጓል።

በዚህ መሠረት የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት በ2008 በጀት ዓመት ከነበረበት 8.5 ሚሊዬን ኩንታል በ2013/14 ምርት ዘመን ወደ 18.1 ሚሊዬን ኩንታል ወይም 113 በመቶኛ ዕድገት አሳይቷል።
ኮርፖሬሽኑ አሠራር ሥርዓት ማሻሻያ ባያደርግ በ2008 ምርት ዘመን የአንድ አሜሪካን ዶላር ከነበረበት ምንዛሬ ብር 21.77 በ2013 ምርት ዘመን ከደረሰበት ብር 40.42 ወይም 85 በመቶኛ Devaluation አንፃር የወኪሉ አስተዳደራዊ ወጪና ትርፍ ህዳግ ተጨምሮ የአንድ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የት ይደረስ እንደነበረ እና በዚህ ምክንያት በምርታማነት ላይ ሊፈጥር የሚችለው ተጽዕኖ ግልጽ ነው።

በምርጥ ዘር አቅርቦት በኩልም በ22 ሰብል ዓይነቶች እና በ69 ዝርያዎች ጥራት ያለው ምርጥ ዘር እያዘጋጀ ለአገራችን ግብርና ምርታማነት መጨመር ከፍተኛ አሰተዋጾ በማድረግ ላይ ይገኛል።በተመሳሳይ በመንግሥት የተያዘ የኩታ ገጠም እርሻ በሜካይዜሽን አገልግሎት የተለያዬ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራክተሮች፣መለዋወጫዎች እንዲሁም ጥገናና የሥልጠና አገልግሎት በመሰጠት የግብርና ቴክኖሎጂ ተደራሽ ለማድረግ የአገልግሎት መሰጫ ማዕከላትን በማስፋፋት ላይ ይገኛል።

ከሕግ ማእቀፍ አንጻር እንቅፋት የፈጠረባችሁ እና ድጋፍ ያስፈልጉናል ብላችሁ የምታነሷቸው ጉዳዮች ምንድናቸው?
ከሕግ ማዕቀፍ ድጋፍ አንጻር የምንፈልጋቸው አንደኛ የአፈር ማዳበሪያ ግብይት ሥርዓቱ ነው። እስከ አሁን ባለው ሁኔታ ከሃያ ዓመታት በፊት በወጣ በማዳበሪያ ግብይት ሕግ ግዢ ሕግ ነው እየተመራን ያለነው። ይሄ አሁን ከደረስንበት የእደገት ደረጃን የሚመጥን አይደለም።
አንደኛ ከውጪ አገር ማስመጣት ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ማዳበሪያ በአገር ውስጥ ማምረት አለብን። በማዳበሪያ ግዢ ላይ የሚሳተፉት ሌሎች ባለድርሻዎችም አሉ፣ለምሳሌ ክልሎች አሉበት፣ ግብርና ሚንስትር በዋናነት በማስተባብር ይሰራል፣ የሚያጓጉዝ እና የሚገዛ ሌላ ባለድርሻም አለ።

አንዳንድ ክልሎች ማዳበሪያን በብድር ወስደው እየከፈሉ ስላልሆነ እና ገንዘቡ በጊዜ ካለመግባቱ ጋር ተያይዞ በተለይ ወጥ የሆነ የገንዘብ ፍሰት እነደዳይኖር አድርጎታል። በመሆኑም ፣ኤል ሲ ከፍቶ ለመቆየትም ጭምሮ ማነቆ እየሆኑ ስለሆነ አሁን ከደረስንበት የእድገት ደረጃ ጋር የሚመጥን የሕግ ማእቀፍ ማሻሻያ ያስፈልጋል።

የግብርና ሚንስትር የሕግ ማእቀፉን ሰርቶ ለሚንስትሮች ምክርቤት ሰጥቷል። እሱ በፍጥነት እዲያልቅ የምንፈልገው።
ሁለተኛው ከገቢ ግብር ጋር የነበረው ነው። ይህም የማዳበሪያ ግዢ ሥርዓቱ ኤል-ሲ ሲከፈት የነበረው የውጪ ምንዛሪ ተመን እና ኤል-ሲ ሲዘጋ የነበረው የውጪ ምንዛሪ ተመን አንድ አይደለም።የማዳበሪያ ግዚ ሥርአት የበጀት ካላንደር እና ምርት ዘመን ካላንደር የተለያየ ነው ፣ይኸውም ኢትዮጵያ በጀት ካላንደር ሰኔ 30 ነው የሚዘጋው፣የኢትዮጵያ ግብርና በጀት ደግሞ እስከ ጳጉሜ 5 እና 6 ድረስ ይሻገራል። ይሄ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚሻገር ስለሆነ፣የተሸገረውን ገቢዎች፣ የገቢ ግብሩ ስለማይፈቅድልን አንይዝም በማለት ባለፉት ዓመታት በ2011 በተደረገ ኦዲት ፍሬ ግብሩ ብቻ 548.8 ሚሊዮን ብር ተወስኖብናል።

ቅጣት ብቻ ደግሞ 917 ሚሊዮን በድምሩ ውደ 1.5 ቢሊየን ብር እንድንከፍል ነው የተወሰነው፡፤ ይሄን በገቢ ግብር ሕግ ማዕቀፍ ተጠቅመን ቅጣቱ እንዲነሳ በማድረግ ፍሬ ግብሩን በአንድ ዓመት ውስጥ ውል ገብተን እየከፈልን ነው ያለነው።
548 ሚሊየን ስንከፍል ወይም 1.5 ቢሊየን ብር ስንከፍል በእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ማዳበሪያ ላይ ጭማሪው እንዲደረግ ይሆናል። በእያንዳንዱ ምርጥ ዘር ኪሎ ግራም ላይ እንዲንጻባረቅ ይሆናል።
አርሶ አደር ፈጋር የዋጋ ጫና ይሄዳል ይሄ አርሶ አደሩን ግብይቱ እየቆመ አይደለም እየቀጠለ ስለሆነ በፍጥነት ይህ እንዲፈቱ እንፈልጋለን። ስለዚህ እነኚህ ጉዳየች የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ ተደርጎላቸው በፍጥነት አንዲፈቱልን እንፈልጋለን።

በተያዘው ዓመት ምን ሊሰራ የታቀዱ ሥራዎች አሉ?
የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተያዘው የበጀት ዓመት የግብርና ግብዓቶችንና የሜካናይዜሽን አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሦስት ማዕከላትን በሰሜንና በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ እነዲሁም በደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ ቦታዎች ላይ ማዕከላቱን ያቋቁማልም።
የሜካናይዜሽን አገልግሎቶች የሚቀርቡባቸውን ማዕከላት በደቡብ ምዕራብ ቦንጋ፣ በደቡብ ምዕራብ ጎንደርና በራያ አላማጣና መሆኒ በተባሉት አካባቢዎች በተያዘው የበጀት ዓመት እንደሚገነባ አስታውቋል።
የመጀመሪያው የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ ማዕከል በደቡብ ምዕራብ ቦንጋ በሁለት ሔክታር መሬት ላይ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ መገንባት ይጀመራል። ቦታውን ለማልማት የዲዛይን ሥራ እየተጠናቀቀ ነው።

ኮርፖሬሽኑ የልማት ድርጅት ነው።ትርፍም ይፈልጋል፣ ለገበሬው በተመጣጣኝ ዋጋ ግብአቶችን ማቅረብም ይጠበቅበታል ይህንን እንዴት ማጣጣም ይቻላል?
እንግዲህ የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በዋናነት ሁለት ዓላማዎችን ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው። የልማት አላማም አለው ፣የቢዚነስ ዓላማም አለው።
የልማት ዓላማ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማቅረብ ነው በኩንታል የምትከፈለን 5 ብር ናት፣ እኛ ግን ማደበሪያውን ከውጪ ገዝተን ለአርሶ አደር ለማድረስ ፣ 8 ብር ከ ሃያ አምስት ሳንቲም ነው ። አሁን እኛ የምናቀርበው በ5 ብር በመሆኑ በኩንታል 3 በር ከሓያ አምስት ሳንቲም እንከሥራለን ። ይህ ዘንድሮ ከምናስገባው 18.2 ሚሊየን ኪንታል አንጻር 60 ሚሊየን እንከሥራለን።ይህንን 50 ሚሊየን እንደ ኪሳራ አንቆጥረውም። እንደ ልማት ድጋፍ ነው የምንቆጥረው።
ነገር ግን እዚህ ላይ የሚያጋጥመንን ኪሳራ ደግሞ፣ 8 በመቶ የሚሆነውን ማዳበሪያ ለሰፋፊ እርሻዎች የምናመጣው አለ፣ ትራክተር እና ኬሚካልም እንዲሁ መለዋወጫዎች አሉ ፣ኪሳራውን ከእነዚህ እማካክሳለን ማለት ነው፡ይህንን ስናካክስ ደግሞ የሰራተኝ ደሞዝ፣ጥቅማጥቅም እና የአስተዳደራዊ ወጪዎችን ከዚሁ ነው የምንከፍለው።

ምርጥ ዘር ፣ትራክተር እና የአፈር ማዳበሪያ ልማት ላይ የሚያተኩር በመሆኑ፣ የትርፍ ህዳግ ወይንም ምጣኔያችን በጣም አነስተኛ ነው።ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የባንክ ወለድ ምጣኔ በትንሹ 11.5 በመቶ ነው። በትለቁ ደግሞ 18.5 ደርሷል። ስለዚህ እኔ ከባንክ ተበድሬ የምሰራበትን መክፈል አልችልም። ለትርፍ አለመቋቋማችን ማሳያ የሚሆነው ፣የትርፍ ህዳጋችን 5 በመቶ ብቻ በሆኑ ነው በዚህ መልክ መታየት ይኖርበታል የሚል አስተያየት አለኝ።

ቅጽ 2 ቁጥር 120 የካቲት 13 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com