የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላዳ ታክሲዎችን ለመለወጥ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ፈቀደ

Views: 243

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት የሰጡ ትናንሾቹን ሰማያዊ በነጭ ታክሲ ወይም በተለምዶ የላዳ ታክሲዎችን በአዲስ ለመተካት ለተያዘው ፕሮጀክት ስድሰት ቢሊዮን ብር ብድር ማመቻቸቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ባንኩ የፈቀደው ብድር ያገለገሉ የላዳ ታክሲዎችን በአዲስ ለመተካት የአዲስ አበባ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች ማኀበር ከኤላአውቶ ኢንጅነሪን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመሆን ለሚሰሩት ፕሮጀክት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ የትራንሰፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ስጦታው አካለ የካቲት 10/2013 በሽራተን ሆቴል በነበረው የፕሮጀክቱ የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ኃላፊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሮጀክቱ አዋጭና ለአዲስ አበባ ከተማ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አንዳሉት በማመን የስድስት ቢሊዮን ብር ብድሩን በማመቻቸት የፕሮጀክቱ ድጋፍ ሰጭ ሆኗል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው እንደገለጹት ኤላአውቶ የሚቀርባቸው 10 ሺሕ 500 አዲስ ታክሲዎች ዋጋ በባለንብረቶች 20 በመቶ የሚሽፈን ሲሆን 80 በመቶ የሚሆነውን ከንግድ ባንክ በተገኘው ስድስት ቢሊዮን ብር ብድር ይሸፈናል ብለዋል።
የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር ከኤላአውቶ ኢንጅነሪን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመተባበር 10 ሺሕ 500 ያረጁ ላዳ ታክሲዎችን በአዲስ ታክሲ ለመቀየር የካቲት 10/2013 የላዳ ታክሲ ባለንበረቶች በተገኙበት ከአቅራቢው ኤላአውቶ ኢንጅነሪንግ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር ተፈራርሟል።

የባለ ላዳ ታክሲ ባለንብረቶቹ በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ የተወሰኑት በአዳዲሶቹ መኪናዎቻቸው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ጠቁመዋል። ይህም ለባለንብረቶቹና ለአዲስ አበባ ከተማም ዘርፈ ብዙ ለውጥ እንደሚመጣ ይጠበቃል ተብሏል።

አቅራቢ ድርጅቱ 10 ሺህ 500 የላዳ ታክሲዎችን በአዲስ ለመተካት በሚሰራው ሥራ ላይ በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ከኤላአውቶ ቢዝንስ ኢንጅነሪን ግሩፕ ጋር በጋር ለመሥራት እንድሳተፉ የኤላአውቶ ኢንጅነሪንግ ቢዝነስ ግሩፕ ሥራ አስኪጅ በቀለ አበበ ጥሪ አቅረበዋል።

የአዲስ አበባ ላዳ ታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር ኃላፊ ቢኒያም መለስ በበኩላቸው ንግድ ባንክ ያመቻቸው ስድስት ቢሊዮን ብር ብድር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንሰፖርት ቢሮና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን በኩል መሆኑን ጠቁመዋል። ንግድ ባንክ ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ለፈቀደው ብድር የማኅበሩና የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ እንደሚለው ከሆነ ፕሮጀክቱ በዚህ የሚቆም አንዳልሆነና ቀጣይነት አንደሚኖረው ነው የጠቆመው። ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮና ባለስልጣን የድርሻቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።
በዚህ ፕሮጀክት ላይ የከተማ አስተዳደሩ ትራንሰፖርት ቢሮና ባለስልጣን ኤላአውቶ አዲስ የሚቀርባቸውን 10 ሺሕ 500 መኪኖችን ቴክኒካል ድረጃ እና ተሽከርካሪዎቹ ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች ለአቅራቢው በማዘጋጅት ድጋፍ አድርጓል ነው የተባለው።
መኪናዎቹ የነዳጅ ፍጆታቸው ካገለገሉት ላዳ ታክሲዎች ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ በአካባቢ አየር ብክለትን ለመቀነስ እንደሚያስችሉም ተገልጿል።

ድርጅቱ በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ ለባለንብረቶች አንደሚደርሱ ተገልጿል። የአዲስ አበባ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች ማኅበርና አቅራቢ ድርጅቱ ወደፊትም አሪጌ ላደዎችነ በአዲስ ለመተካት በጋራ አንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 120 የካቲት 13 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com