የመጀመሪያው የፓርላማ የምርምር ኮንፈረንስ

Views: 133

አርብ፣ የካቲት 12 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ ‹‹ፓርላማ፣ ዴሞክራሲ እና ሰብዓዊ መብቶች›› በሚል ርዕስ የተጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያው የፓርላማ የምርምር ኮንፈረንስ ዛሬ ይጠናቀቃል።
አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በመክፈቻ ንግግራቸውም በዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ውስጥ ምክር ቤቶች የዴሞክራሲ ስርዓት መገንቢያ መድረክና መሣሪያ ሆነው እንደሚያገለግሉ ገልፀዋል። በዚህ ዘመን በተለይ እያደጉ ባሉና በሽግግር ላይ ባሉ አገራት ምክር ቤቶች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከጥናትና ምርምር ተቋማት፣ ከሙያ እና ሲቪል ማኅበራት ጋር የሚያደርጉት የሰመረ ግንኙነት የአገራቱን ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በመፍታትና አገራቱን በማሳደግ በኩል ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያን የማደግ እምቅ አቅም ወደ ተግባር ለመቀየር ጥናትና ምርምር ወሳኝ ሚና አላቸው ያሉት አፈ ጉባዔው፥ የፓርላሜንታዊ የምርምር መረብ መጠናከር ምክር ቤቱ እያካሄደ ለሚገኘው ማሻሻያ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥና ፓርላማውም በጥናትና ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ እንዲሰጥ ለማገዝ ይረዳል ብለዋል።
የምርምር ኮንፈረንሱ በመደበኛነት በየዓመቱ እንደሚካሄድም ታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 120 የካቲት 13 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com