ዳሸን ባንክ 25ኛ ዓመቱን ለስድስት ወራት እንደሚከብር አስታወቀ

Views: 137

ባንኩ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡
የባንኩ 25ኛ ዓመት ክብረ በዓል በይፋ የሚጀመረው ነገ የካቲት 18/2013 መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚከበረው የዳሸን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በ25 ዓመት ያጋጠሙ ችግሮችንና መልካም አጋጣሚዎችን በመፈተሽ፣ ደንበኞችን፣ አጋር ድርጅቶችንና የባንኩን ሰራተኞች በማመስገን እንደሚሆን የባንኩ ፕሬዝዳንት አስፋው አለሙ ተናግረዋል፡፡
በነገው እለት በይፋ በሚጀመረው የባንኩ 25ኛ ዓመት ክብረ በዓል ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ፣ 20 የከተማ አውቶብሶችን ለከተማዋ ነዋሪዎች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ አንደሚጀመርም የባንኩ ፕሬዝዳንት ጠቁመዋል፡፡ እንዲሁም በቀጣይ በሚደረጉ ዝግጅቶች የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይት እንደሚኖርም ተመላኳቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 67 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስፋው ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com