በኦሮሚያ ክልል የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩ አሳሳቢ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ

Views: 163

ኮሚሽኑ ዛሬ የካቲት 18/2013 ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከየካቲት 6/ 2013 ጀምሮ በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኘውን ሙሃመድ ዴክሲሶ በተመለከተ የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የካቲት 16/ 2013 በዋስ እንዲለቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ ከእስር አለመለቀቁ እንዳሳሰበው ገልጾ፣ ሙሃመድ ዴክሲሶን ጨምሮ ሌሎችም በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተከብሮላቸው በእስር ላይ የሚገኙ እስረኞች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ አሳስቧል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር ) ጉዳዩን አስመልክቶ “በኦሮሚያ ክልል ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣው የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበር እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ አፋጣኝ ትኩረትና እልባት ይሻል” ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com