የአማራ ክልል ከማዕድን ዘርፍ ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ እያጣ ነው

Views: 58

በህገ ወጥ ክሬሸሮች ብቻ ከዘርፉ በዓመት ከ94 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚባክን የክልሉ የማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ገልጿል።
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) በማዕድን ሃብት ዙሪያ የሚታየውን ብክነትንና ህገወጥ አሠራር ለመከላከል ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በአማራ ክልል የኮንስትራክሽን፣ የኢንዱስትሪ፣ የጌጣጌጥ የማዕድን ሃብቶች በስፋት እንደሚገኙ በኤንጀንሲው የማዕድን ምርት ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክተር አለነ ፈንታ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ የተደራጀና የተጠናከረ ቅንጅታዊ አሠራር አለመኖር ክልሉ ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያገኘ አለመሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።
አጋር አካላት ሃብቱን ለመጠበቅ ትኩረት አለመስጠት፣ ሴክተሩ ለሙስናና ኢ-ፍትሐዊ አሠራር የተጋለጠ መሆን፣ በህገወጥ መንገድ ሃብቱን መዝረፍ ለብክነቱ በምክንያትነት ተቀምጠዋል።
በህገወጥ ክሬሸሮች ብቻ በዓመት ከ 94 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚባክን ለአብነት ተነስቷል። በቀጣይ ሃብቱን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም ተቋሙ ሀብቱን ማስተዳደር በሚችልበት ቁመና ማደራጀት፣ ህገወጥነትን ለመከላከል በሚደረገው ሂደት የፍትህ ተቋማት እና ሌሎች አጋር አካላት እገዛ እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።
በማዕድን ሃብቱ ላይ የሚታየውን ህገወጥ እንቅስቃሴ ማስቀረት ከተቻለ የክልሉ የማዕድን ገቢ አሁን ካለበት 35 ሚሊዮን ወደ 200 ሚሊዮን ብር ማሳደግ እንደሚቻል ተመልክቷል።
ሃብቱን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ከኦፓል ማዕድን ብቻ በርካታ የሥራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ተብሏል።
ባለፉት 6 ዓመታት ከዘርፉ 75 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉን አቶ አለነ ነግረውናል።
በአማራ ክልል በዘርፉ በዓመት በአማካይ ለ35 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ እንደተናገሩት የማዕድን ዘርፉን ለማልማት ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ጥናት ተካሂዷል።
ሃብቱን እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ማምጣት የሚችሉ ድርጅቶች የልየታ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ላይ ተወዳዳሪ አምራቾችን ካልፈጠረች የአገራት ሸቀጦች ማራገፊያ ልትሆን ትችላለች ተባለ።


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com