ለግንባታ የሚቀርቡ የሀገር ውስጥ የግብዓት ምርቶች ጥራታቸው በአግባቡ በላብራቶሪ እየተፈተሸ ወጥነት ያለው ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግባቸዉ እንደሚገባ ተገለጸ

Views: 58

የሕንጻ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ከኮንስትራክሽን ጥራት ማስጠበቂያ ላብራቶሪዎች አተገባበር ላይ በተደረገ የመስክ ዳሰሳ ሪፖርት የሀገር ዉስጥ ምርትን ለማሳደግ ጥራታቸዉን የጠበቁ እና በላብራቶሪ የተፈተሹ ምርቶችን ለገበያዉ ማቅረብ ላይ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት ማሳሰቡን የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለአሀዱ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል።
ሪፖርቱ በዋናነት ለሀገር ውስጥ ግብዓት አምራቾች ተገቢውን ግንዛቤና አረዳድ በመፍጠር በሀገራችን በፈጣን ደረጃ እተከናወኑ በሚገኙ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ታስቦ እንደተዘጋጀ ያብራሩት በሚኒስትር መ/ቤቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ማሻሻያ ቢሮ የህግ ዝግጅት ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ሰይድ ናቸው።
አቶ ብርሃኑ በሪፖርቱ እንዳቀረቡት በሁሉም የክልል ከተሞችና ዞኖች ወጥና ጥራቱን የጠበቀ የኮንስትራክሽን ላብራቶሪ ፍተሻ በሚጠበቀው ደረጃ ልክ አለመገኘቱና አለመተግበሩ ከፍተኛ ሀገራዊ ተግዳሮት በመሆኑ በየክልሉ የሚገኙ የመንግስት አካላትና ባለድርሻ አካለት ከፍተኛ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
አቶ ብርሃኑ አያይዘው የጥራት ጉድለት፣ የቅንጅት ሥራ ማነስ፣ ጥራትን ለማስጠበቅ ተገቢውን በጀት አለመመደብና የመሳሪያዎችን ደህንነት አለመከታተል፣ የባለሙያ ፍልሰት ተጠቃሽ ችግር ናቸው ብለዋል።
የደህንነትና የጥራት አጠባበቅ ዘዴን አለመከተል፤ የመረጃ አያያዝ ጉድለት፤ እንዲሁም በሥራ ቦታ ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር እንደ ችግር በሪፓርቱ ተጠቅሰዋል።


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com