መኢአድ በጎንደር ምርጫ ቅስቀሳ ችግር ገጥሞኝ ነበር አለ

Views: 127

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ምርጫ ቦርድ የካቲት 8 ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግ ቢፈቅድም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በፀጥታ አካሉ ክልከላ ደርሶብናል ሲሉ ከሰዋል።
ፕሬዜዳንቱ በጎንደር የምርጫ ቅስቀሳ ችግር አጋጥሟቸው እንደነበር ገልፀዋል።
ችግሩ የተፈጠረው በጸጥታ አካሉ ከህግ የወጣ ድርጊት ነው ሲሉም ለኢትዮጵየ ፕሬስ ድርጅት አሳውቀዋል።
የጸጥታ አካሉ መኪና እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል፣ ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል እገዳ አድርጓል ፣ የጸጥታ አካሉ ሥራ የህዝብ ጸጥታ ማስከበር እንጂ የተላለፈን ህግ መጣስ አይደለም።
የጸጥታ አካሉ ከማንም በፊት በምርጫ ቦርድና በመንግስት በኩል መረጃው ደርሶታል።ይህ ሆኖ እያለ ደግሞ ይህንን መፈጸሙ ምርጫውን ከማደናቀፍና ጥላሸት ከመቀባት አይተናነስም ብለዋል።
ከዚህ በኋላ አልሰማንም አላየንም እንዳይሉ ፤ ይህንን ድርጊታቸውን ዳግም እንዳይፈጽሙ፤ ፓርቲው ህጋዊ ሆኖ እየተንቀሳቀሱ ድረስ ምንም አይነት እንግልት እንዳይገጥማቸና በየጊዜው የሚያስፈቅዱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ምርጫ ቦርድና መንግስት ወጥ መመሪያ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የጸጥታ አካሉ እምዲሁም አመራሩ የማያገባው ውስጥ እንዳይገባ የሚመለከተው አካል አደብ ሊያስገባው እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ደረጃ ውጤታማ ቅስቀሳ ማድረጉን መኢአድ አሳውቋል። ከአዲስ አበባ ውጪ በደብረብረሃን፤ በባህርዳርና መሰል የአማራ ክልል ከተሞች ላይ የምርጫ ቅስቀሳው መካሄዱንም ጠቁሟል።


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com